DW Amharic
52.2K subscribers
3.76K photos
869 videos
69 files
14.5K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
የጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ዋና ዋና ዜና

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የወረዳ ባለሥልጣናትን ጨምሮ 48 ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ አስታወቀ።

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር በእገታና በዘረፋ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ክ129 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጠ።

የጀርመን የፋይናንስ ሚኒስትር ከሥልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ጥምር መንግሥት ቀውስ ውስጥ ገብቷል። ተቃዋሚዎች አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ ግፊት እያደረጉ ነው። ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር የጥምር መንግሥቱ ለገባበት ቀውስ መፍትሄ ለማምጣት ኃላፊነት የተሞላበት አካሄድ እንዲኖር ፖለቲከኞቹን አሳስበዋል።

ተሰናባቹ የአሜሪካን ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዛሬ ለሀገሪቱ ሕዝብ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ዝርዝሩን ያድምጡ፤ ያንብቡ! https://p.dw.com/p/4mlwq?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
ትክክለኛውን የዶይቸ ቬለ የዩቲዩብ ገጻችን ይከተሉ!

ውድ አድማጮቻችን ፦የተለያዩ መገናኛ አውታሮችን በመጠቀም አድማሳችንን በማስፋት ዝግጅቶቻችንን በዩቲዩብም እያቀረብን ነው ። የትክክለኛው የዶይቸ ቬለ ዩቲዩብ ገጽ አባል በመሆን ዝግጅታችንን ተከታተሉ ። በትክክለኛው በዚህ የዩቲዩብ አድራሻችን፦
https://www.youtube.com/channel/UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A አባል ይሁኑ። ለወዳጆቻችሁም ያጋሩ ።

ዶይቸ ቬለ በዓበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪቃ፣ የአውሮጳ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ የዜና ዘገባዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ትንታኔዎችን ያቀርባል ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መጽሄት እና የዓለም ዜና ከሰኞ እስከ ዓርብ በዶይቸ ቬለ ዩቲዩብ ገጻችንም https://www.youtube.com/channel/UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A ላይ ይቀርባሉ ።

የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ እና በሳተላይትም በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል።
አሁኑኑ የዶይቸቬለ የዩቲዩብ ገፅ ደምበኛ ይሁኑ!
https://www.youtube.com/channel/UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A

ዶይቸ ቬለን በዩቲዩብም ይከተሉ!
በአማራ ክልል የቀጠለው ቀውስ እና የንፁሃን ዜጎች ግድያ
በአማራ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ "አረጋውያንን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰዎችን ላይ ከሕግ ዉጭ" ግድያ እየተፈፀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ገለፀ። ኢሰመጉ ባወጣው መግለጫ "ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚደረገው እሥር" በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ሌሎችም ክልሎች መፈፀማቸውንም አስታውቋል።
https://p.dw.com/p/4mne4?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
የተስፋ ጭላንጭል የታየበት የሰላሌ ሰላም ዳግም መደፍረስ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዳግም የተቀሰቀሰዉ አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸዉ ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ ባለፈው ነሐሴ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ አካባቢዉ ላይ የሚካሄደዉ ግጭት አማሮኛል ሲል አደባባይ ከወጣ በኃላ መንግሥት በወሰደዉ እርምጃ የጸጥታ እጦት መዘዞች ቀንሰዉ እንደነበር እና አሁን ግን የፀጥታ ስጋት ዳግም መቀስቀሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
https://p.dw.com/p/4mnXa?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
በጋምቤላ የተሻለ የሠላም ሁኔታ እየመጣ ነው ተባለ
በጋምቤላ ክልል ካለፈው ነሐሴ 2016 ዓ ም ወዲህ የአመራር ለውጥ ከተደረገ ወዲህ በክልሉ የነበረው የሠላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን አዲሱ አስተዳደር፣ ተፎካካሪ የፖልቲካ ፓርቲ አመራሮችና ነዋሪዎች ተናገሩ።d ባለፈው ዓመት በጋምቤላ ክልል በተለያዩ አካባቢዎችና ጊዜዎች ግጭቶች እየተከሰቱ በሰው ህይዎት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል።
https://p.dw.com/p/4mnPg?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
የዋሊያና ቀይ ቀበሮ ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔት ተመናምኗል ተባለ
ግጭት እና ጦርነቶች በሠዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በዱር እንስሣት ላይም ስደትና ሞት እያስከተለ እንደሆነ የእንሣት ጥበቃ ባለሙያዎች ገለፁ። በኢትዮጵያ ብቸኛ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ዋሊያ አይቤክስና ቀይ ቀበሮ ቁጥራቸው ቀደም ሲል ከነበረው በግማሽ መቀንሳቸውን የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አስታውቋል።
https://p.dw.com/p/4mnKm?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት የሚታገሉት የደሴ ከተማ ወጣቶች
ገና በታዳጊ ዕድሜዋ ለዚያዉም ምክንያቱን በውል በማታውቀው ሁኔታ ለቫይረሱ የተጋለጠችው ማክዳ ቀጣዩ የህይወቷ ምዕራፍ ፈታኝ ነበር ። በቫይረሱ መያዝ የሕይወት መጨረሻ ያህል ይሰማኝ ነበር የምትለው ወጣቷ ምንም እንኳ ስለበሽታው አንብባ መረዳት የምትችል ቢሆንም ከማህበረሰቡ ከሚገጥማት የአመለካከት ችግር ራሷን እስከማግለል አድርሷት ነበር።
https://p.dw.com/p/4mn84?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
«በሴቶች ላይ የሚደርሱ ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው።»
በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ በቪዲዮ እየቀረፁ መድፈርን ጨምሮ ከሀይማኖት ፣ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ ከአሰቃቂ ጥቃቶች መፈፀማቸው ተደጋግሞ ይሰማል። ያም ሆኖ በመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የአንድ ሰሞን አጀንዳ ከማድረግ ባለፈ ችግሩን በተመለከተ መሰረታዊ እና ተከታታይነት ያለው ስራ እየተሰራ አይደለም በሚል ይተቻሉ።
https://p.dw.com/p/4moNb?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጎቤን ባህል ከመታደግ ስርዓቱን ለትውልድ ማስተላለፍ
በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በተለይም በቱለማ ኦሮሞ በጉልህ የሚታወቀው ጎቤ የሚባል የወጣት ወንድ ልጆች የሽለላና ጭፈራ ፕሮግራም ሁሌም ከመስከረም 1 እስለ 16 ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት የሚደረግ ነው፡፡
ይሁንና ወጣቶች ወቅታዊውን የፖለቲካ እና ማህበራዊ ሁናቴዎችን አይተው የሚተነፍሱበትና በማህበረሰቡ መሃል በመሄድ እያሞጋገሱ ምርቃት የሚቀበሉበት ይህ የወጣቶች ባህላዊ ጭፈራ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ያሉ 50 ግድም የኦሮሞ አርትስቶች ባህሉን ከመጥፋት ለመታደግ ማህበር መስርተዋል፡፡
ወጣቶቹ በዛሬው እለት የዘንድሮው ባህላዊ ስነስረዓት የቋጩበትን እና ባህሉን ለቀጣይ ወጣቶች ለማስተላለፍ የወጠነ መርሃግብር በአዲስ አበባ ከተማ አከናውነዋል፡፡
ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ (DW) ከአዲስ አበባ
አወቀች ስጦታው ከአንድ ወር በፊት ስለተሰናበቱት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ አስተያየት አላቸው። በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ እና አዲሱ ፕሬዚዳንት ላይ አስተያየታቸውን ያካፈሉንም በርካቶች ናቸው። እናንተም በዚህ ክፍለ ጊዜ እንዲቀርቡላችሁ የምትፈልጉት መልዕክት ካላችሁ በኢ-ሜይል፣ በደብዳቤ፣ በፌስቡክ፣ በቴሌግራም ፣በድምጽ እና በጽሁፍ መላክ ትችላላችሁ። https://p.dw.com/p/4moAt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
የጥቅምት 30 ቀን 2017 የዓለም ዜና
• ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት የሶማሊያ ተልዕኮ (AUSSOM) መታገዷን የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር ተናገሩ። በመጪው ጥር ወር ሥራ ይጀምራል ተብሎ ከሚጠበቀው ተልዕኮ ኢትዮጵያ እንዳትሳተፍ የታገደችው "የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት በመጣሷ" ምክንያት እንደሆነ አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር መናገራቸውን የሶማሊያ ብሔራዊ የዜና ወኪል (SONNA) ዘግቧል።
• በደቡብ ሱዳን የተከሰተ ኃይለኛ ጎርፍ 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ለችግር መዳረጉን፤ 379,000 ደግሞ ማፈናቀሉን የተባበሩት መንግሥታት አስታወቀ።
• በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ኬቢ ግዛት ላኩራዋስ የተባለ አዲስ የሽምቅ ተዋጊ በፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።
• በደቡብ ምዕራብ ፓኪስታን በአንድ የባቡር ጣቢያ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 24 ሰዎች ተገደሉ።
• እስራኤል እና ሐማስ ወደ ድርድር ለመመለስ ከልብ ፈቃደኝነታቸውን እስኪያሳዩ ድረስ ቃጣር በጋዛ ተኩስ እንዲቆም የምታደርገውን ጥረት እንደምታቆም አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሬውተርስ ተናገሩ።
• ኢራን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለአራት ዓመታት ሥልጣን ላይ ሣሉ ያሳደሩባትን ከፍተኛ ጫና በሁለተኛ የሥልጣን ዘመናቸው እንዲተዉት ጥሪ አቀረበች።
ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፦
https://p.dw.com/p/4mpgk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
አንጋፋው በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን እንዲሁም ዶቸ ቬለ ለረዥም ዓመታት ያገለገለው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ። ጋዜጠኛ ዜናነህ ለረዥም ጊዜያት ባደረበት ህመም ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት እስራኤል ቴል አቪቭ ዛሬ ጠዋት ማረፉን ዶቸ ቬለ ከልጁ ቢታንያ ዜናነህ ተረድቷል። ስልሳ ስምንት ዓመቱ ነበር ። አዘዞ ጎንደር የተወለደው ዜናነህ ከ1970ዎቹ እስከ ሰማኒያዎቹ አጋማሽ ድረስ በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በተለይ በዜና አንባቢነት አገልግሏል። በ1980ዎቹ አጋማሽ ወደ እስራኤል ያቀናው ዜናነህ በህመም ተዳክሞ ከሥራው እስኪርቅ ድረስ በኢየሩሳሌም የዶቼ ቬለ ራዲዮ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል ።
ይህ ዶቼ ቬለ ነው ከሚለው የዶቼ ቬለ የጣቢያው መለያ አንስቶ የተለያዩ ዝግጅቶች መክፈቻም የአንጋፋው ጋዜጠኛ ድምፅ ነው።
የዶቼ ቬለ አድማጮች ዜናነህን ከመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል አረብ ግጭት እና ጦርነቶች ብሎም በቀጣናው በሚነሱ ፖለቲካዊ ዘገባዎች ያውቁታል። የዜናነህ መኮንን የቀብር ሰነ ስረዓት ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ ያኮም መካነ መቃብር እንደሚፈጸም ልጁ ቢታንያ ዜናነህ ገልጻለች ። ዜናነህ ባለትዳር እና የሶስት ሴቶች ልጆች አባት ነበር ።
የህዳር 1 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን እንዲሁም ዴቼ ቬለ ለረዥም ዓመታት ያገለገለው አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ። ጋዜጠኛ ዜናነህ ለረዥም ጊዜያት ባደረበት ህመም ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት እስራኤል ቴል አቪቭ ዛሬ ጠዋት ማረፉን ዶቼ ቬለ ከልጁ ቢታንያ ዜናነህ ተረድቷል።

• በቻድ እስላማዊ ጂሃዲስቶች በርካታ የመንግስት ወታደሮች መግላቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ ። በቻድ ሀይቅ አቅራቢያ ከእስላማዊ ጂሃዲስቶች ጋር በተደረገ ዉጊያ በርካታ የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

• የእስራኤል ጦር በሊባኖስ እና በጋዛ ሰርጥ ቤሩት በፈጸመ የአየር ጥቃቶች ከ40 በላይ ሰዎች ተገደሉ ። ጦሩ በሁለቱ ጥቃቶች ከተገደሉት ውስጥ አብዛኞቹ ህጻናትን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው ተብሏል።

• ዩክሬን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በአንድ ክብረ ወሰን የሆነ የሩስያ የድሮን ማዕበል ማስተናገዷን አስታወቀች ። 145 የሩስያ ድሮኖች ድንበር አቋርጠው መግባታቸውን ይፋ ያደረገችው ኪዬቭ ከዚህ ውስጥ ስልሳ ሁለቱን መትታ መጣሏን ገልጻለች።

• የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአቶሚክ ተቆጣጠሪ ቡድን ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ ወደ ኢራን ሊጓዙ ነው። የፊታችን ረቡዕ ቴህራን እንደሚደርሱ የሚጠበቁት የተቆጣጣሪ ቡድኑ ኃላፊ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/4mqxq?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ዉይይት፣ የትራምፕ ድል፣ መርሐቸዉ፣ የዓለም ሥጋትና ተስፋ
ኮሚንስታዊ ሥርዓት በአብዛኛዉ ዓለም ከፈራረሰ (እጎአ) ከ1991 ወዲሕ በጦር ኃይል፣በሐብት፣ በዲፕሎማሲ፣ በፖለቲካ፣ በሳይንስና ርዳታ ከዓለም ቀዳሚዉን ሥፍራ የምትይዘዉ ዩናይትድ ስቴትስ፣ለአራት ዓመት የምትመራዉ በትራምፕ ይሁንታና ፍቃድ ነዉ።የተቀረዉ ዓለም ዩናይትድ ስቴትስ ጠላትም ሆነ ወዳጅ የትራምፕን መርሕና ርምጃ ማማተር ግድ አለበት።
https://p.dw.com/p/4moiS?maca=amh-RED-Telegram-dwcom