ድምፀ ተዋሕዶ
11.1K subscribers
3.34K photos
85 videos
189 links
ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን
ለታማኝ መረጃዎ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዓለም አቀፍ የመነኮሳት ማኅበር ወቅታዊ ሀገራዊ እና ቤተ ክርስቲያናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጠንከር ጠንከር ያሉ አቋሞቹን በመዘርዘር መግለጫ አወጣ።

ማኅበሩ በመግለጫው ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን ፈተና ለመመከት በሚመጥን ካልተራመደ ሓላፊነቱን ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እስከማስረከብ መሔድ አለበት ብሏል።

ብፁዕ አቡነ ሉቃስንም በብርቱ ተከላክሏል። ተግሣጻቸው ነቢዩ ኤልያስ ኤልዛቤልና አክዓብን እንደገሰጸበት ያለ ነው ብሏል።

አባይነህ ካሴ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ታዟል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ አዟል።

በዋስ ጥያቄያቸው ዛሬም ውድቅ ተደርጓል።

ቀሲስ በላይ መኮንን በችሎቱ ፥ " ፖሊስ ይዞኝ ሳይሆን እራሴ ነው የሄድኩት " ብለዋል፡፡

" ብዙ የሀገር ጉዳይ በእጄ ስላሉ ጥፋ ብባል እንኳ የምጠፋ ስላልሆንኩ ፤ በጤናዬ ላይ በደረሰው እክልና በቤተሰቦቼ ላይ በደረሰው ችግር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት ይጠብቅልኝ " ሲሉ ጠይቀዋል።

የብዙ ልጆች አሳዳጊና የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሆኑ ጠቅሰው በዋስ ከእስር እንዲወጡ ጠይቀው ነበር።

ፍርድ ቤት ግን ሁሉም ተከሳሾች በፖሊስ ጣቢያ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ አዟል።

ቀሲስ በላይ መኮንን በሀሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ላይ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ አድርገዋል ተብለው አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች ጭምር መታሰራቸው አይዘነጋም።

ዶቼቨለ
ቲክቫህ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጌታችን አዲሱን የዕርገቱን ዜና ለማርያም መግደላዊት ባበሠራት ጊዜ በከፍተኛ የደስታ ስሜት ስለተሞላች ፈጥና ዜናውን ለደቀ መዛሙርቱ እንድትነግር ሲል “አትንኪኝ አላት፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።” 

ጌታችን ከዕርገቱ በፊት በቀለዮጳ ቤት ተገኝቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ማዕድን ተካፍሎአል፤ ለቶማስም የተወጋውን ጎኑን አሳይቶታል።  

በምን ምክንያት ነው ታዲያ እንዳትነካው ይከለከላት? ጌታችን ማርያም መግደላዊትን፡- “አትንኪኝ” ሲላት እርሱን አለመንካቷ ተግሣጽ እንዲሆናትም በማሰብ ነው። ጌታችን ለማርያም መግደላዊት ወደ ሰማይ እንደሚያርግ በፍጻሜ ዘመንም በዚሁ አካል እንደሚመጣ በመጣም ጊዜ ለእነርሱ የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ከሐዋርያት ጋር ሳለ አስተምሮአት ነበር።  ስለዚህ እርሱ ጌታችን እንደሆነ ስታውቅ በአእምሮዋ ዳግም ምጽአቱ የተፈጸመ መስሎአት በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ እንዳለች ቆጥራ ነበርና “ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ' አላት፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ሕዝብና ትውልድ ከተዋጡበት ከሲኦል በኵር ሆኖ ተወልዷልና (ተነሥቶአልና) በዚህ ቃሉ በእርሱ ትንሣኤ (ብቻ) አባቶች ወደ ልጆቻቸውም ልጆችም ወደ አባቶቻቸው እንዳይመለሱ ነገር ግን ሁሉም በትንሣኤ ዘጉባኤ ትንሣኤአቸው እንዲፈጽምላቸውና ወደ አባታቸውም ለማረግ የተገባቸው እንደሚሆኑ ሲያስገነዝባት እንዲህ አለ፡፡

አንድ አንባቢ “እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ" የሚለውን ቃል ሲያነብ ጥሬ ቃሉን ይዞ እግዚአብሔር አብ በምድር እንደሌለ በሰማይ እንዳለ አድርጎ እንዳይረዳ፤ እርሱ እግዚአብሔር አብ በምድርም ያለ ከሆነ ስለምን ጌታችን ወደ ሰማይ እሄዳለሁ አለ? ብሎ ይጠይቅ ይሆናል። ልጁ በሰማይ የማይሆንበት አባቱም በምድር የማይኖርበት ምንም ምክንያት የለም፡፡

ጌታችን “እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ” ዮሐ.17:11 ባለው ቃል እውነቱን ገልጦልናል፡፡ “አምላኬ” አላለውም፤ “ቅዱስ አባት ሆይ!” አለው እንጂ። እንዲህም ማለቱ እርሱ ከእርሱ እንደወጣ ለማጠየቅ ነው። መግደላዊት ማርያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲልካት ግን “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ እሄዳሉ" ብሏታል፡፡ እንዲህም ሲላት ከእርሱ ጋር በአምላክነት አንድ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ 

ጌታችን እንዲሁ በሌላ ሥፍራ “አብ ከእኔ ጋር ስለሆነ ብቻዬን አይደለሁም።”፣ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ”ዮሐ.17:36 “እኔና አብ አንድ ነን” ብሎአልና። ዮሐ.14:11

ጌታችን “ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ” ብለሽ ተናገሪ ብሎአል፡፡ “ወደ አባታችንና ወደ አምላካችን" አላለም ነገር ግን “ወደ አባቴ” አስከትሎም “ወደ አምላኬ" አለ እንጂ። በእርግጥ “ወደ አባታችንና ወደ “አምላካችን” ብቻ ብሎ ቢሆን ኖሮ ለሚቃወሙን መሠረት በኖራቸው ነበር፡፡ ነገር ግን “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ” ሲል ስለ ሥጋዌው መናገሩ ነው። “ወደ አባቴ እሄዳለሁ” ሲል ስለሥጋዌው እንጂ በእግዚአብሔር ቃልነቱ አይደለም። እንዲሁ “ወደ አባታችሁ” ሲልም ከእኛ ስለነሣው ሥጋ ስለመሆኑ “አባታችን ሆይ! በሰማያት የምትኖር”ብሎ ባዘዘን ቃሉ መረዳት እንችላለን፡፡ ማቴ.6:9

መ/ር ንዋይ ካሳሁን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እውነትም ይሁን ሐሰት ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተባለ ነገር የለም።እንዳይሆን እሚያግደው ነገር ባይኖርም፤እንዳይሆን ግን ጸልዩ።