ድምፀ ተዋሕዶ
14.2K subscribers
3.93K photos
88 videos
190 links
ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን
ለታማኝ መረጃዎ
Download Telegram
ድምፀ ተዋሕዶ
Photo
"ባየነው ነገር ሁሉ  ደስተኞች ነን በዚህም ቤተ ክርስቲያን ክፍ ብላ ስላየናትና ኦርቶዶክሳውያን  በዝተው ስለተመለከትን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

የእንኳን ደህና መጡ አቀባበሉ  በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የቀጠለ ሲሆን በርካታ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ተኝተዋል።

በቅዱስነታቸው የእንኳን ደህና መጡ  አቀባበል መርሐ ግብር ላይ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን  ሊቃውንትና ወጣት ሰንበት ትምህርት ቤት መዘመራን  ዝማሬ  አቅርበዋል።

እንዲሁም የቅዱስነታቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚገልጽ ቅኔ የኔታ ሐረገ ወይን  የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቅኔ መምህር  አቅርበዋል።

የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ያቀረቡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት የነበራቸው ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ስለመጡ እንኳን ደህና መጡ ያሉ ሲሆን በዚህ ክብረ አበውን የጠበቀ አቀባበል የተገኙትን ሁሉ አመስግነዋል።

ብፁዕነታቸው ቀጥለው በደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት የነበራቸው ዝርዝር ሐዋርያዊ አገልግሎት ያብራሩ ሲሆን  በሆነው  ሁሉ  ደስታው የኦርቶዶክሳውያን ክብሩም የቤተ ክርስቲያን ነው ብለዋል።

በዚህም ቅዱስነታቸውን በክብር የጋበዙትንንና አገልግሎቱም የሠመረ እንዲሆን በሁሉም መልክ መደላድል ለሆኑትን ለብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የደቡብና የምዕራብ አፍሪካ የከንባታና የሐዲያ ስልጤ ሀገረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስ ምስጋና አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸውን ተከትለው ከሄዱት አበው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል  አገልግሎታቸው ምን ይመስል እንደነበር ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  ምስክርነት ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው የነበረው አገልግሎት በእጅጉ  መልካም እንደነበር አውስተው በሁሉም መልክ አገልግሎቱ የተቃና እንዲሆን  ኦርቶዶክሳዊ ድርሻቸውንና የልጅነት ተግባራቸውን ለገለጹ ለደቡብ አፍሪካ  ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ማኅበረ ካህናትና ምዕመናን ምስጋና አቅርበዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በሰጡት ቃለ በረከት "የእግዚአብሔር ቸርነት የአባቶችና የምዕመናን  ጸሎት ረድቶን በሰላም ተመልሰናል" ብለዋል።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት ኦርቶዶክሳውያን ፍቅራቸውን ያሳዩን ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ ተጎዘው  ሊቀበሉን ከመምጣት ጀምሮ ነው ብለዋል።

ከደቡብ አፍሪካ  በቅራቢያ በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራትም በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን እየተስፋፋች መሆኑንም አይተናል ሲሉ ገልጸዋል ቅዱስነታቸው።

"ባየነው ነገር ሁሉ  ደስተኞች ነን ለዚህም ቤተ ክርስቲያን ክፍ ብላ ስላየናትና ኦርቶዶክሳውያን  በዝተው ስለተመለከትን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን" ሲሉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ  ጀምሮ ክብሩ የቤተ ክርስቲያን ነው ብላችሁ ላደረጋችሁት  መልካም አቀባበል በእጅግ አመሰግናለሁ ብለዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ብፁዓን አባቶችና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓፊዎችን  በማስከተል ለሐዋርያዊ አገልግሎት  ግንቦት ፪/፳፻፲፮ ዓ/ም ወደ ሥፍራው እንዳቀኑ  የሚታወስ ነው።


የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የነዚህን ድራማ መጨረሻ ለማየት ቸኩለናል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በዩኬና አየርላንድ ሀገረ ስብከት ስር የሚኖሩ ካህናት በሙሉ ለመላው ህዝበ ክርስቲያን ያስተላለፉት ወቅታዊ መልዕክት ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ሁላችሁም በምትጠቀሙት ማኀበራዊ ገጽ እንድታጋሩ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ድምፀ ተዋሕዶ
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ከግንቦት 5-7 ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የነበሩ እና የሰርግ ስነስርዓትን ታድመው ይመጡ የነበሩትን ጨምሮ አጠቃላይ 40 ንጹሃን ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን አነጋግሮ አሻም ቲቪ ዘግቧል።

አዩ ዘሐበሻ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM