Dawit Dreams Official
24.6K subscribers
2.6K photos
54 videos
1 file
833 links
Dawit DREAMS Official Channel
Download Telegram
ሰላሳኛ ባች የፓራዳይም ሺፍት ስልጠና ተጀመረ። የቀረን ቦታ ጥቂት ስለሆነ ዛሬውኑ በ+2519 38 252525 በመደወል ይመዝገቡ። ዛሬን በጥበብ እንኑር !
ራስን መፈተሽ

ራስን መፈተሽ አንዴ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ ቅጽበታዊ ጉዳይ አይደለም። አሁንም ቢሆን ወደ ተራነት እንዳትመለስ ራስህን ፈትሽ። ሙሉ ለሙሉ ወደ ተራነት መመለስ፣ አማራጭ አይደለም። በማንኛውም የህይወት ዘርፍ ላይ ራስህን ተራ ሆነህ ካገኘኸው፣ ወዲያውኑ ራስህን በመገሰጽና በመገምገም ራስህን ወደ ድንቅነት ቀይር፣ በሕይወትህ በማንኛውም መንገድ ተራ ከሆንክ እራስህንም ሆነ ሌሎችን ሰዎች እንደማትጠቅም በማወቅ፣ ድንቅ ከመሆን ለአንድ አፍታ እንኳ ዝቅ ማለት የለብህም፣ ራስህንና ቤተሰብህን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንና አፍሪካን ድንቅ ለማድረግ መሆን ያለብህን በመሆን መስራት ያለብህን በመስራት በአለም ላይ ታሪክ ለመስራት በመወሰን፣ በሁሉም የሕይወት ዘርፎችህ ዙሪያ ራስህን በጥንቃቄ ፈትሽ።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
መልካም ቀን

ሰላሳኛ ባች የፓራዳይም ሺፍት ስልጠና
በ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ.

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
በየቀኑ ምግብ ካልተመገብን ስጋዊ አካላችን ይራባል ጨጓራችን አሲድ ይረጫል፤ ልክ እንደዚያው አዕምሮአችንም ካልተመገበ ይራብና መርዝ መርጨት ይጀምራል።

ዳዊት ድሪምስ ድንቅ የሆነ የ2 ወር የአዕምሮ ምግብ ሊሰጠን ተዘጋጅቷል፣ ዝግጁ ናችሁ? ማንም እንዳይቀር!

አድራሻ:- 22 ባታ ኮምፕሌክስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ድሪምስ ሲኒማ

እንዲሁም ለአዲሱ 30ኛ ዙር ለመመዝገብ +251938252525 ይደውሉ።

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
ቀንህን ድንቅ በሆኑ ቃላት ጀምር

ቀንህን ድንቅ በሆኑ ቃላት ስትጀምር ሕይወትህን ድንቅ ማድረግ ትችላለህ። አሁን በአካባቢህ ያለው የውጪው ዓለም በሚደብር ሁኔታ ላይ ቢሆንም፣ የውስጥህን ድንቅነት እንዲረብሽ በጭራሽ አትፍቀድለት። ሰዎች "እንዴት ነህ?" ብለው ሲጠይቁህ፣ የምትመልሰው መልስ ምን ያክል በሕይወት ላይ ተፅዕኖ እንዳለው አትዘንጋ። ከዛሬ ጀምሮ ሰዎች "እንዴት ነህ" ብለው ሲጠይቁህ፣ በመጀመሪያ በእምነትህ መሠረት "እግዚአብሔር ይመስገን"! ወይም "አልሃምዱሊላህ"! በማለት ፈጣሪህን አመስግን። ከዚያ ቀጥሎ ግን "ዛሬ ይደብራል፤ ቀኑ ይቀፋል...." የሚሉ ቃላቶች በምንም ተዓምር ከአንደበትህ እንዳይወጣ፣ ፈጣሪህን ካመሰገንክ በኋላ ልትላቸው የሚገቡህ ቃላት "እኔ፣ ቤተሰቤ፣ ቀኔ፣ ሥራዬና ሀገሬ ሁሉም ነገር ድንቅ ነው!" የሚል ብቻ መሆን አለበት። አሁን ላይ ድንቅ የሆኑ ቃላትን ከዘራህ፣ በኋላ ድንቅ የሆኑ ውጤቶችን ታጭዳለህ! ይህ ደግሞ የተፈጥሮ ህግ ነው።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
መልካም ቀን

ለ30ኛ ዙር የፓራዳይም ሺፍት ስልጠና ምዝገባ ባለን ውስን ቦታ፣ +251938252525 በመደወል አሁኑኑ ይመዝገቡ።

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
የሕይወትና ስኬት ምስጢራትን በመማር፣ መረዳትና በመጠቀም ሕይወትዎን መቀየር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ አሁኑኑ ይወስኑ!
ለበለጠ መረጃ በ+251938252525 በመደወል ይመዝገቡ።
ሕይወትህ እንዲቀየር ራስህን መቀየር አለብህ!

ተራ ሰው፣ ሕይወቱን ለመቀየር እናቱ፣ አባቱ፣ ሚስቱ፣ ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ መሥሪያ ቤቱ፣ መንግስት እና ሌሎች ሰዎች እስኪቀየሩ ይጠብቃል። እነዚህ ሰዎች ከተቀየሩ ይቀየራል፣ ካልተቀየሩ ደግሞ ተስፋ ይቆርጣል። ድንቅ ሰው ስትሆን ግን፣ ራስህን ለመቀየር ሕይወትህን ትቀይራለህ፣ ማንም ሰው ወይም ምንም ነገር እስኪቀየር አትጠብቅም፣ ሕልምህን ለማሳካት መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ከማለዳ አንስቶ መክፈል ትጀምራለህ። ሙሉ ቀን፣ መሆን የሚገባህን በመሆን ማድረግ ያለብህን በማድረግ፣ መቀየር ያለብህን በመቀየር፣ መሥራት ያለብህን በመሥራት፣ የማንንም ሰው ዕርዳታ ሳትጠብቅ፣ ራስህን በመቀየር ሕይወትህን መቀየር አለብህ ስለዚህ ሕይወትህ እንዲቀየር ከፈለግክ፣ መቀየር ያለበት ከአንተ ውጪ ያለ ሌላ አካል ሳይሆን፣ አንተ ራስህ ነህ!

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
መልካም ቀን

ለ30ኛ ዙር የፓራዳይም ሺፍት ስልጠና ምዝገባ፣ +251938252525 በመደወል አሁኑኑ ይመዝገቡ

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram