አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
198K subscribers
5.09K photos
161 videos
14 files
768 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#አሼ_በቀጠሮ

📜 በ1996 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ቡና
ልደታው ኒያላ 3ለ 0 ይሸነፋል ።በዚህ ጊዜ የጊዮርጊስ ደጋፊዎች አሸናፊ ግርማን ይሰድቡትና ያበሽቁት ጀመር
እሱም በአፀፋው በእጅ ምልክት በሚቀጥለው ጨዋታ
እንገናኝ ብሎ ቀጠሮ አስያዛቸው።

📄 ቀኑ ደርሶ #ቡና #ከጊዮርጊስ
ተገናኙ የዝናብ ጨዋታ አሸናፊ ግርማ በቀጠሮው መሰረት ማራኪ ጎል አስቆጠረባቸው ።

⌚️ ዘጠና ደቂቃ ሙሉ በዝናብ ቡድኑን ሲያበረታታ የዋለው የቡና ደጋፊም "በቀጠሮ አሹ በቀጠሮ" እና
"እንደበረደን አሹ አሞቀን"
በሚሉ ጭፈራዎች ስቴድዮሙን አደመቀው classic game!
#respect Ashu saviola #9

#ቡና#ቅዱስ_ጊዮርጊስ በታሪካቸው ለመጀመርያ ጊዜ
ሲገናኙ አሽናፊ የሆነው ኢትዮጵያ ቡና ነበር 2 ለ 1

💬 #በኢትዮጵ_ቡና ተጫዋቾች ታሪክ ጊዮርጊስ ላይ የመጀመርያዋን ጎል ያስቆጠረው ሚሊዮን በቀለ (ሆዴ)
የተባለ ተጫዋች ነበር ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቡና ቀድሞ ቢመሰረትም በ ብዙ ፕሮፌሽናል ነገሮች ግን ቡናን እንደ ጅራት ሲከተል
ተስተውሉዋል ።

✔️ #ህጋዊ_የደጋፊ_ማህበር በመመስረት ፣ ተጫዋቾች እግር ኩዋሱን እንደ መደበኛ ስራቸው በመቁጠር በካምፕ እንዲቀመጡ በማድረግ ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ከሀገር ውጪ ሜዳልያ ይዞ በመምጣት(1990 ከ ዛንዚባር) ፣ ኦፊሺያል የደጋፊዎች መዝሙር በማሳተም ፣ የራሱን የሬዲዮ የአየር ሰአት በመግዛት ፣ የራሱ የቲቪ ፕሮግራም በማዘጋጀት ደጋፊውን ያሳተፈ የልማት ስራ በመስራት ደጋፊው ክለቡ ላይ የባለቤትነት ስሜት እንዲኖረው
በማድረግ....... ወዘተ ቡና ፈር የቀደደ ክለብ ሲሆን ሼባው ደግሞ የቡናን copy ...paste በማድረግ ስራ ተጠምዱዋል !!!

♨️ ጆሮ ቀድሞ ይፈጠራል ነገር ግን ዘግይቶ የተፈጠረ ቀንድ ይበልጠዋል❗️

💮 አሁን ያለው #የቡና_ስብስብ እንደ በፊቱ ባይሆንም ነገር ግን አሁን ያሉት ልጆች በ ሞራል እየተጫወቱ ስለሆነ አሁንም 90 ደቂቃውን ሙሉ ከጎናቸው ሆነን ልናበረታታቸው ይገባል ።

#ድል_ለ_ኢትዮጵያ_ቡና❗️❗️❗️

🌐 #Tadios_Gashaw🌐

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆

👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈

ጥሩም መጥፎም ዜና ነው ግን እነዚህን ተጫዋቾች አተናል በሚሄዱበት ሁሉ መልካም ነገር ይግጠማቸው
#ቡና ወደፊት ከዚ በላይ አድጎና ጠንክሮ እንዲመለስ ምኞታችን ነው

#ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አምስት ተጨዋቾች ተለያዩ#

የስማቸው ዝርዝር

1 #ሳምሶን ጥላሁን
2 #ቶማስ ስምረቱ
3 #ወንድይፍራው ጌታሁን
4 #ክሪዝስታም ንታምቢ
5 #ወንድወሰን አሸናፊ በረኛው

ከኢትዮጵያ ቡና ጋ ተለያይተዋል

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆

👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆


#4ኛው_ዙር_የቡና #የቤተሰብ_የሩጫ_ቀን እሁድ #ነሐሴ_19 የሚደረግ ይሆናል በመሆኑም ለሩጫው ስንመጣ ሁላችንም ማስተዋል አለብን ሩጫው የሚካሄደው
#ከመስቀል_አደባባይ ወደ #ሜክሲኮ ስለሆነ የምንሮጠው ስንመጣ መንገድ ዝግ ስለሚሆን ሁላችንም በዚህ መንገድ እንጠቀም ወደ ሩጫው መግቢያ ቦታ በሶስት ቦታ ብቻ ነው ።
#አንደኛው =》 #በእስጢፋኖስ_ቤተክርስቲያን በኩል
#ሁለተኛው =》 #በቦሌ በኩል
#ሶስተኛው =》 #በኡራኤል በኩል መሆኑን ለማሳወቅ እንፈልጋለን ።
#ቡና_ደሜ_ነው
#ሼር_ያድርጉት_ለተሳታፊዎቻችን_እዲደርስ !!

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
🔆 #በታማኝነታችን_በተለመደው_ትዕግስታችን_እንቀጥል


🇪🇹☕️1980 አጋማሽ ላይ ለድንቅነሽ(ሉሲ) ዋንጫ ቡና "#ከፈረሰ" በኋላ እንደገና ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሜዳ የሚመጣበት ጊዜ ይፋ ሆነ የመጀሪያውንም ጨዋታ ከአየር መንገድ ጋር ደረሰው

👉 #ቡና_ገበያ ወደ ሜዳ ሲገባ ደጋፊው ገንፍሎበት ቡድኑን እንደገና ሜዳ ላይ በማየቱ በአጥር ዘሎ በመግባት ተጨዋቾቹ እግር ላይ ሳየቀር እየወደቀ ባንደራውን ይዘው

👉 #እያለቀሱ ከሜዳ አንወጣም በሚል ጨዋታው ሳይጀመር ከ30 ደቂቃ በላይ6 ቆየ ደጋፊው መሬትቱን #ይስማል ባንዲራውን ይዘው #የሚጨፍሩ ደጋፊዎችም ነበሩ እርስበእርስ #ተቃቅፈው ያለቅሳሉ ሁሉም ስሜቱን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ነው።

👉#ዳኞቹም ፊሽካ በመንፋት ውድድር ቶሎ እንዲጀመር አላደረጉም በሁኔታው ተገርመው #ይውጣላቸው ብለው ተዋቸው ደጋፊው ውድድሩን አልፈለገም ቡድኑ ዳግም በመመለሱ #ኢትዮጵያ_ቡናን ሜዳ ላይ በማየታቸው ብቻ ተደሰቱ፡፡

አሁንም ያ #ታማኝነት ለክለባችን ያለን #ፍቅር ሳይቀንስ እዚህ ደርሷል እኛም እናስቀጥለዋለን ።
#አይታጠፍም_ቃላችን_ዘላለም_ቡንዬን_ብቻ

©eyobed

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈

#ካታንጋ በዚህ ሰአት ሙሉ ለሙሉ እንጨቱ ተነስቶ ፍቅር የሆኑ የ #ቡና_ደጋፊዎችን በናፍቆት እየጠበቀች ነው ።

#ውድ #የጅማ_አባጅፋር_ደጋፊዎች የእናንተ ቦታ ከማን አንሼ ያለ ወንበር ከ ጥላ ፎቅ በግራ በኩል ያለው 3 ቁጥር ነው ።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#ሲዳማ
#ቡና

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#ቡና_ይለያል
አዲሱ መዝሙራችን😘

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ቀጣይ ጨዋታ
#ሲዳማ ቡና#ኢትዮጵያ ቡና
9:00
ረቡዕ ጥር 26/2013
#ድል #ለኢትዮጵያ #ቡና👆👆👆

#ግምታችሁን በ ኮመንት መስጫ አስቀምጡልን

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ቡና_ባንክ_ከኢትዮጵያ_ቡና_ስፖርት_ክለብ_ጋር_የተፈራረመውን_የዘላቂ_አጋርነት_ስምምነት_አደሰ

*አዲስ አበባ መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም

*በቡና ባንክ እና በቡና ስፖርት ክለብ መካከል በ2013 ዓ.ም የተፈረመውና የመቆያ ጊዜው የተጠናቀቀው የዘላቂ አጋርነት ስምምነት እንዲራዘም ስምምነት ላይ በመደረሱ አንድ ዓመት ታድሷል።

*ስምምነቱ የታደሰው ባንኩና ስፖርት ክለቡ በ2013 ዓ.ም የተከናወኑት ተግባራት የሁለትዮሽ ጥቅምን በማሳደግ በኩል የነበራቸውን ሚና ከገመገሙና አጋርነቱ ያስገኘው ውጤትም ተስፋ ሰጪ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

*ስምምነቱ የተደረሰው በቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቶ ሙልጌታ አለማየሁ እና በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋና ስራ አስኪያጅ በአቶ ገዛኸኝ ወልዴ ፊርማ ከፀደቀ በኋላ ነው።

*በስምምነቱ መሰረት ቡና ባንክ ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብና ለክለቡ ደጋፊዎች ማህበር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደርጋል።

*በስምምነቱ መሰረት ቡና ባንክ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለቡን እና የደጋፊዎች ማህበሩ የሚያካሂዱትን የቲኬት ሽያጭ እና የአባልነት ክፍያዎች በዲጂታል አማራጮች በመሰብሰብ እንዲያግዝ፣ ክለቡ ለሚያጋጃቸው ልዩ ልዩ ኹነቶች፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎችና የማስተዋወቂያ ዘመቻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ፣ የክለቡንና የደጋፊ ማህበሩን የፋይናንሺያል ማሳለጫ አገልግሎት እንዲያግዝ፣ ለክለቡ እና ለተጨዋችና አመራሮቹ የባንክ አገልግሎቶችን ና የመሳሰሉትን ድጋፎች እንዲያደርግ ይጠበቅበታል።

*ክለቡ በበኩሉ የቡና እግር ኳስ ክለብ ማሊያ ላይ የቡና ባንክን አርማ በደረት በኩል እንዲያትም እና በረፕሊካ ቁምጣና ማሊያው ላይም የባንኩን ሎጎ እንዲያስቀምጥ፣ በሃገር ውስጥና ውጪ የሚገኙ የቡና ክለብ ደጋፊዎች እና የክለቡ ስፖንሰሮች የቡና ባንክ ደንበኛ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች፣ የባንኩን ብራንድ እና አገልግሎቶችን ሶሻል ሚዲያን ጨምሮ ባሉት ሚዲያዎች እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንዲያስተዋውቅና ሌሎች ባንኩን ከማስተዋወቅና የቢዝነስ እንቅስቃሴዎቹን ከባንኩ ጋር ከማድረግ ጋር የተገናኙና መሰል ተግባራትን እንዲያከናውን ይጠበቅበታል።

*በስምምነቱ የተጠቀሱት ነጥቦች አፈጻጸም ከሁለቱም ወገኖች በተዋቀረውኮሚቴ በየሶስት ወሩ የሚገመገም አስፈላጊ ማሻሻያዎች እየተደረገበት ዓመቱን ይዘልቃል። ስምምነቱ እንደአፈጻጸሙ ደረጃ እየታየ በሚቀርበው ሪፖርት ላይ ተመስርቶ በየዓመቱ የሚታደስ ይሆናል።

*ቡና ባንክ ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና ለስፖርት ክለቡ ደጋፊዎች ስኬትን እየተመኘ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዘላቂ አጋር በመሆኑ ክብር የተሰማው መሆኑን ይገልጻል።

*ቡና ባንክ በቅርቡ በተፈረመ ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስፖንሰር መሆኑ ይታወቃል።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ቡና_ደሜ_ነው

ቡና ደማችን ነው ስንል ቃላት ለማሳመር አይደለም!! የእውነትም ደማችን ስለሆነ ነው። የቡና ኳስ ለማየት ደማቸውን የሸጡለት ፣ አይን የጠፋለት ፣ ህይወት የተሰዋለት.... ብዙ ብዙ ያልተነገሩ መስዋእትነቶች የተከፈለለት ስለሆነ ነው እኛ ቡናውያን ቡና ደማችን ነው ደማችንም ቡኒ ነው የምነለው።

ነገ ቡናማው ሰራዊት አዳማን ያጥለቀልቃታል በዝማሬ ትናጣለች በቡኒ እና ቢጫ ማሊያ ከተማዋ ታሸበርቃለች።

#ቡና_ደሜ_ነው የሚለውን ማሊያ ለብሰን ዘጠና ደቂቃ ልጆቻችንን እናበረታለን በማሊያችንም ህብረ ቀለማትን እየፈጠረን ውበታችንን ለአለም እናሳያለን

የሚለበሰው ማሊያ 👉 #ቡና_ደሜ_ነው

#አንድነታችን_ውበታችን_ነው
#አንድነታችን_ሃይላችን_ነው
#አንድነታችን_ድላችን_ነው

እኛ የታላቁ ኢትዮጲያ ቡና #የማይሸነፈው_ደጋፊ_ነን
💚💛👆

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ነገስ

      ♻️
#አሼ_በቀጠሮ

👉 በ1996 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ኢትዮጵያ
ቡና በ ልደታው ኒያላ 3 ለ 0 ይሸነፋል ።

በዚህ ጊዜ የጊዮርጊስ ደጋፊዎች አሸናፊ ግርማን
ይሰድቡትና ያበሽቁት ጀመር ።
አሼም በአፀፋው በእጅ ምልክት በሚቀጥለው ጨዋታ እንገናኝ ብሎ ቀጠሮ አስያዛቸው።

ቀኑ ደርሶ
#ቡና ከ ጊዮርጊስ
ተገናኙ የዝናብ ጨዋታ ነበር በጊዜው አሸናፊ ግርማ በቀጠሮው መሰረት ማራኪ ጎል አስቆጠረባቸው።

ዘጠና ደቂቃ ሙሉ በዝናብ ቡድኑን ሲያበረታታ የዋለው የቡና ደጋፊም

በቀጠሮ አሹ በቀጠሮ "
እንደበረደን አሹ አሞቀን "
በሚሉ ጭፈራዎች ስቴድዮሙን አደመቀው
ጊዜው 1986 ነው ::

በወቅቱ በአንድ ቀን ሶስት ጨዋታ ነበረ ይደረግ የነበረው የመጀመሪያውን ጨዋታ በትክክል አላስታውስም ሁለተኛው ጨዋታ ግን ቡና ገበያ ከ ክራይ ቤት 2-2 የተጠናቀቀ ግሩም ጨዋታ ነበረ። የእለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ቢራን ከ እርሻ ሰብል ያገናኘው እና በቢራ 1-0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ነበረ።

ጨዋታው ተጠናቆ ጋሼም ከጓደኞቻቸው ተሰናብተው ወደ ቤት ስናመራ አንድ ጥያቄ ጠየቁኝ እንዴት ነበረ ጨዋታዎቹ ብለው? እኔም አሪፍ ነበረ በጣም ደስ ይላል ሚሊዮን በጋሻው እና ሙልጌታ ከበደ ተመችተውኛል አልኩ (በተደጋጋሚ ሲጠራቸው ስማቸውን ስለያዝኩ) በመቀጠል እኔም ፈራ ተባ እያልኩ ጋሼ እኔ ግን ዛሬ ባየሁት ከሆነ ቡኒዎቹን ነው መደገፍ የምፈልገው አልኩ 😔 ሌላ ወሬ ሳናወራ ቤት ደረስን የኔና የጋሼ የስታዲየም ጉዞ በአንድ ቀን ለዘለዓለም ተቋጨ 🤚

ልቤን አሸንፎት አደገኛው ቡና
ስምክን ሳላነሳው ስውል ይለኛል ቅር

በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብሆን የኔ ቡና ቢራን ሲያሸንፍ እንደማየት የሚያስደስተኝ ነገር የለም!!

#ቡና_ገበያ_የዘር_ሀረግ

📷 Gediyon Seyoum ገፅ የተወሰደ።
ደሱ ከማን አንሼ ✍️

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና-አደገኛ
💛🤎@coffeefc💛🤎
💛🤎@coffeefc💛🤎
#ቡና_ባንክ_ከኢትዮጵያ_ቡና_ስፖርት_ክለብ_ጋር_የተፈራረመውን_የዘላቂ_አጋርነት_ስምምነት_አደሰ

አዲስ አበባ ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

በቡና ባንክ እና በቡና ስፖርት ክለብ መካከል በ2015 ዓ.ም የተፈረመውና የመቆያ ጊዜው የተጠናቀቀው የዘላቂ አጋርነት ስምምነት እንዲራዘም ስምምነት ላይ በመደረሱ ውሉ ለአንድ ዓመት ታድሷል።

ስምምነቱ የታደሰው ባንኩና ስፖርት ክለቡ በ2015 ዓ.ም የተከናወኑት ተግባራት የሁለትዮሽ ጥቅምን በማሳደግ በኩል የነበራቸውን ሚና ከገመገሙና አጋርነቱ ያስገኘው ውጤትም ተስፋ ሰጪ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

በስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ ቡና በኩል በሚለብሳቸው ማሊያ ላይ የቡና ባንክን አርማ በደረት በኩል እንዲያትም እና በሪፕሊካ ማሊያው ላይም የባንኩን ሎጎ እንዲያስቀምጥ፣ በሃገር ውስጥና ውጪ የሚገኙ የቡና ክለብ ደጋፊዎች እና የክለቡ ስፖንሰሮች የቡና ባንክ ደንበኛ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች፣ ሌሎች ባንኩን ከማስተዋወቅና የቢዝነስ እንቅስቃሴዎቹን ከባንኩ ጋር ከማድረግ ጋር የተገናኙና መሰል ተግባራትን እንዲያከናውን ይጠበቅበታል።

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለቡና ባንክ ማኔጂግ ቦርድ፣ ማኔጅመንት፣ ሰራተኞች እና ደንበኞች መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እና የ2016ዓ.ም የስኬት ዘመን እንዲሆንላችሁ እየተመኘ፤ ቡና ባንክ ዘላቂ አጋራችን በመሆኑ ክብር የተሰማው መሆኑን ይገልፃል።

#በተያያዘ
ዋናው አጋራችን ሐበሻ ቢራ አ.ማ ላለፉት አስር ዓመታት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በአጋርነት በመስራቱ የተሰማውን ክብር እና ደስታ እየገለፀ፤ በቀጣይ ከሐበሻ ቢራ ጋር በምንሰራቸው ስራዎች ዙሪያ እና ያሳለፍናቸውን ስኬቶችን እና ውጣውረዶችን በተመለከተ ተከታታይ ዘገባዎችን ይዘን እንቀርባለን።
#ቡና ድሮም ሰው ነው ሀብቱ

👉 ይሄ ሲባል ቡና ስኬት አይፈልግም ማለት አይደለም። ቡና ውጤት አዮድለትም ማለት አይደለም ። ቡና ዋንጫ አይናፍቅም አይፈልግም ማለት አይደለም ።

👉 የቡና ሀብት ቦርዱ አልያም ደጋፊ ማህበሩ አይደለም ። የቡና ሀብት እንቁ የሆነው ደጋፊ ነው ።

👉 አመራሮች ባሰባቹት እና መሸወድ በቻላችሁት መጠን እየተጓዛችሁ ያለችሁ ይመስላችኋል ። ነገር ግን አይደለም ከ 10 አመት በላይ ይሄ ደጋፊ ከዛሬ ነገ ለውጥ ይመጣል ብሎ በትግስት ስለጠበቀ ነው ።

👉 እናተ አሰልጣኝ እና ተጫዋቾች ለማቆየት እንደማትታገሱት ይሄ ደጋፊ ግን ታግሷል ። አሁን ግን በቃ በቃ እዚህ ጋር ይበቃችኋል ።

👉 ለነበራችሁ የውድቀት ዘመን የአዘቅት ጊዜ ከድጡ ወደ ማጡ አስገብታችሁ መከራ ስላሳያችሁን ከልብ እናመሰግናለን

የቴሌግራም የመወያያ ግሩፓችንን ይቀላቀሉ🔽⬇️
➡️  @BunnaFC  💛🤎
➡️  @BunnaFC  💛🤎
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM