አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
771 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
ቅድመ ዳሰሳ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና

የስድስተኛ ሳምንት መክፈቻ የሆነውን የሸገር ደርቢ የተመለከተው ዳሰሳችንን እነሆ።

የመዲናይቱ ሁለት ክለቦች ከድል መልስ የሚገናኙበት ተጠባቂ ጨዋታ ነገ ረፋድ ላይ ይከናወናል።

በእርግጥ ባለፉት ዓመታት የሸገር ደርቢ በሜዳ ላይ የታሰበውን ያህል ፉክክር ሳያሳየን የጎል ድርቅም እየመታው ሲጠናቀቅ ቆይቷል።

ይህ መሆኑ ተጠባቂነቱን ባይቀንሰውም ጓጉቶ ለሚጠብቀው የስፖርት ቤተሰብ የሚጠበቀውን ያህል አዝናኝ አለመሆኑ ቅሬታን የሚፈጥር ነው።

ለዚህ እንደአንድ ምክንያትነት የሚነሳው የሜዳ ላይ ጡዘቱ ወደ ደጋፊዎች ግጭት እንዳያመራ የመሰጋቱ ነገር ዘንድሮ በኮቪድ 19 ምክንያት ጨዋታዎች በዝግ በመካሄዳቸው የማይኖር በመሆኑ ጨዋታው ከፍ ያለ ፉክክር እንዲኖረው በር ሊከፍት እንደሚችል ይገመታል።

የቡድኖቹ ተጨዋቾችም ቀለል ባለ ጫና ውስጥ ሆነው ሲገናኙ የተሻለ ብቃታቸውን አውጥተው ለመጨወት ዕድል እንደሚያገኙም ይታሰባል።

ከሰባት ቀናት በኋላ ወደ ጨዋታ የሚመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስት ተከታታይ ድሎችን በማሳካት መልካም አቋም ላይ ይገኛል።

ከማሸነፍ በዘለለ በየጨዋታዎቹ ያስቆጠራቸው ግቦች ቁጥር ከፍ ማለትም ከእንደነገው ዓይነት ጨዋታ በፊት የቡድኑን በራስ መተማመን ከፍ ለማድረግ የሚረዳ ሌላው በጎ ነጥብ ነው።

ወደ ቀደመ የቀጥተኛነት አጨዋወቱ የማዘንበል ባህሪ እየታየበት ያለው ጊዮርጊስ ከተከላካይ ጀርባ የሚገኙ ክፍተቶችን በአግባቡ በመጠቀም ጥንካሬውን ማሳየት ችሏል።

ነባሮቹም ሆኑ አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ግብ በማስቆጠር እና ጨዋታ ለዋጭ ተፅዕኖዎችን በመፍጠር እያሳዩ ያሉት ብቃት ቡድኑ አማራጮች እንዲሰፉለት ጨዋታው ቢከብደው እንኳን በተጫዋቾች የግል ብቃት የሚገኙ ግቦችን ለማስቆጠር የሚረዳው ጉዳይ ነው።

በተለይ ኢትዮጵያ ቡና ከኃላ መስመር ላይ ከሚሰራው ተደጋጋሚ ስህተት አንፃር የፈረሰኞቹ ቀጥተኝነት እና ፊት ላይ ያሉ ተሰላፊዎቻቸው ፍጥነት ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይገመታል።

ቡድኑ መሀል ሜዳ ላይ ኳስን የማቆየት ሀሳብ ካለው ግን የተሻለ ውህደት ባለው ተጋጣሚው መፈተኑ የሚቀር አይመስልም።
ኢትዮጵያ ቡና እንደተጋጣሚው ረዘም ያለ የማገገሚያ ጊዜ ባይኖረውም ከኋላ ተነስቶ ያሸነፈበት የሰበታው ጨዋታ ትዝታ ትኩስ መሆኑ የቡድኑ ጉልበት ላይ የሚጨምርለት አዕምሯዊ ጥንካሬ ይኖራል።

የኳስ ቁጥጥር የበላይነትን አብዝተው የሚፈልጉት ቡናማዎቹ እንደ ሰበታው ጨዋታ ታታሪነት የታከለበት እና የፊት መስመር ተሰላፊዎች እገዛ ያልተለየው እንቅስቃሴ የመሀል ሜዳውን ጦርነት ለማሸነፍ ትልቅ እገዛ ያደርግላቸዋል።

እንደ #ዊሊያም_ሰለሞን እና #ሬድዋን_ናስር ዓይነት ወጣት ተጫዋቾቻቸው ጭምር ቡድኑ ለሚፈልገው አካሄድ በጨዋታ ጭምር ተፈትነው ለደርቢው መድረሳቸውም ለቡድኑ ተጨማሪ ኃይል ይሆነዋል።
ምንም እንኳን ከተጋጣሚው በራሱ ሜዳ ከፍ ያለ ጫና ሊደርስበት እንደሚችል ቢገመትም ያንን የሚያልፍበት ጥሩ ዕቅድ ከኖረው የጊዮርጊስን የአማካይ ክፍል ተጋፍጦ የመጨረሻ ኳሶችን ለማድረስ የተሻለ ዕድል ይኖረዋል።
ይህን ለማድረግ ግን ተደጋጋሚ ለውጦች የተደረጉበት የቡድኑ የተከላካይ አማካይ ተሰላፊ ሚና ከፍ ያለ ነው።

ፊት መስመር ላይ ያሉት የቡድኑ ተሰላፊዎችም እንዲሁ ከግብ አስቆጣሪነቱ ሳይቦዝኑ ለጨዋታው መድረሳቸው ለአሰልጣኝ #ካሳዬ ቡድን ጥንካሬን የሚያላብስ ነው።
ቡድኑ ከኋላ ያለከፍተኛ ጫና ሲሰራቸው እና ዋጋ ሲያስከፍሉት የሰነበቱት ስህተቶች ግን ነገ ከበድ ባለ ጫና ዳግም የመፈተሻቸው ነገር ስጋት የሚጭር ይሆናል።

በቡድኖቹ የተሻለ የማጥቃት ተሳትፎ ያላቸው ተከላካዮች #ሄኖክ_አዱኛ እና #ኃይሌ_ገብረትንሳይ ወደ ፊት ለመሄድ ከተቃራኒ ቡድን የመስመር አጥቂዎች የሚገጥማቸው ፈተና ፣ #ታፈሰ_ሰለሞንን ከሙላለም መስፍን ያሚያጋፍጡ ቅፅበቶች ፣ የጊዮርጊሶቹ አቤል ያለው እና አዲስ ግደይ ከቡና የተከላካይ መስመር ፊት እና ኃላ ያሉ ቦታዎች ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ ፣ የቡና መስመር አጥቂዎች በጊዮርጊስ መሀል እና መስመር ተከላካዮች መሀል ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት እንዲሁም የጌታነህ ከበደ እና የ#አቡበከር_ናስር ከተከላካይ መስመር ጋር የሚኖራቸውን ግብግብ በነገው ሸገር ደርቢ የምንጠብቃቸው የሜዳ ላይ ፍልሚያዎች ይሆናሉ።

ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ የቡድን ዜናዎችን ለማካተት ያደረግነው ጥረት በሁለቱም ክለቦች በኩል መረጃ ባለማግኘታችን አልተሳካም።

እርስ በእርስ ግንኙነት
– ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ 40 ጊዜ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 ጨዋታ ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያ ቡና 6 ድል አሳክቷል። በ16 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
– የሸገር ደርቢ ምንም እንኳ አሁን አሁን ያለ ግብ የሚጠናቀቅባቸው ጨዋታዎች በርከት ቢሉም ባለፉት 40 ግንኙነቶች 73 ጎሎች ተቆጥረዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ 49፤ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 24 ጎሎች ማስቆጠር ችለዋል።

ግምታዊ አሰላለፍ
ቅዱስ ጊዮርጊስ (4-2-3-1)
ፓትሪክ ማታሲ
ሄኖክ አዱኛ – ምንተስኖት አዳነ – አስቻለው ታመነ – ፍሪምፖንግ ሜንሱ
ሀይደር ሸረፋ – ሙሉዓለም መስፍን
አቤል ያለው – ሮቢን ንጋላንዴ – አዲስ ግደይ
ጌታነህ ከበደ

ኢትዮጵያ ቡና (4-3-3)
ተክለማሪያም ሻንቆ
ኃይሌ ገብረትንሳይ – ወንድሜነህ ደረጄ – አበበ ጥላሁን – አሥራት ቱንጆ
ታፈሰ ሰለሞን – ረመዳን ናስር – ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን
አቤል ከበደ – ሀብታሙ ታደሰ – አቡበከር ናስር
© ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ኢትዮጵያ ቡና የዛሬ አሰላለፍ

1 ተክለማርያም ሻንቆ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
16 ሬድዋን ናስር
13 ዊልያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
10 አበበከር ናስር
25 ሀብታሙ ታደሰ
17 አቤል ከበደ

አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ በሰበታው ጨዋታ ድል ያደረገውን ቡድን ሳይቀይር ጨዋታውን ይጀምራል ወጣቶቹ #ሬድዋን_ናስር እና #ዊልያም_ሰለሞንም በድጋሚ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ የመካተት ዕድልን አግኝተዋል።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
የአሁኑ አሰልጣኛችን የቀድሞው ተጫዋቻችን #ካሳዬ አራጌ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉 የሰከኑት #ካሳዬ_አራጌ #Gk

➡️አሰልጣኞች እንደ ማንኛውም ሰው በህይወት ጉዟቸው የስሜት ከፍታ እና ዝቅታ ማስተናገዳቸው ብሎም እነዚሁን ስሜቶች የሚያፀባሩቁባቸው ተለዋዋጭ ግብረ መልሶችን በስራቸው ላይ ማሳየታቸው የሰውነታቸው መገለጫ ተደርገው ይወሰዳሉ። ታዲያ ይህን የህይወታችን አንዱ አካል የሆነውን የስሜት መለዋወጥ ግን በኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ላይ መመልከት እጅግ አዳጋች ይመስላል።

➡️አሰልጣኙ ብዙዎቻችን በምናውቀው ከካሜራ ፊት እና በሜዳው ጠርዝ ቡድኑን ሲመሩ የሚታይባቸው የስሜት ወጥነት እጅግ አስደናቂ ነው።

➡️ቡድኑ ቢመራም አልያም ብልጫ ቢወሰድበት አሰልጣኝ ካሳዬ ግን እንደተለመደው እጅጉን ተረጋግተው በሜዳው ጠርዝ ላይ ይታያሉ እንጂ ሲቅበጠበጡ እና በስሜት መዋዥቅ ውስጥ ሆነው አናያቸውም።

➡️እንደ አብዛኞቹ የሊጉ አሰልጣኞች ከቡድኑ በተቃራኒ የሚወሰኑ የዳኝነት ውሳኔዎችን ተከትሎ እንኳን ተቃውሞዎችን ስያሰሙ አይስተዋልም።

➡️ታድያ ይህ የሰከነ ስብዕና አያስገርምም ትላላችሁ ?

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ቅድመ ዳሰሳ | ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ከነማ

BY: ዮናታን ሙሉጌታ

 ON: MARCH 5, 2021

 IN: ዜና

እጅግ ወሳኝ የሆነውን ጨዋታ በዳሰሳችን እንዲህ ተመልክተነዋል።

ነገ ረፋድ ላይ የሚደረገው ይህ ጨዋታ በዋንጫ ፉክክሩ ላይ የሚፈጥረው ልዩነት የተጋጣሚ ቡድኖችን ብቻ ሳይሆን የሊጉን ተከታታዮች ሁሉ ትኩረት የሳበ ሆኗል።

ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ያሸነፈው ኢትዮጵያ ቡና ከዘጠናኛው ሳምንት የወላይታ ድቻ ሽንፈት በኋላ ሳይረታ ከነገ ተጋጣሚው ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት እንዳይሰፋ በማድረግ ለጨዋታው ደርሷል።

ድል ቀንቶት ያሁኑን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ ማድረግ ከቻለም ኮስታራ ተፎካካሩነቱን አረጋግጦ ቀጣይ ጨዋታዎቹን ይከውናል።

በነገ ተጋጣሚው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በኋላ ለሽንፈት እጅ ያልሰጠው ፋሲል ከነማም ልዩነቱን ስምንት አድርሶ በፉክክሩ ላይ ትንፋሽ ለመውሰድ ቡናን ማሸነፍ ብቸኛ አማራጩ ነው።
የስድስት ተከታታይ ድል ጉዟቸው በሰበታ ነጥብ ሲጥሉ የተቋረጠባቸው ፋሲሎች በ11 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ሪከርዳቸውን ግን አሁንም በእጃቸው አድርገው ነው ነገ ለፍልሚያው የሚቀርቡት።

ኢትዮጵያ ቡና የዋንጫ ተፎካካሪ ቡድኖች ባህሪን ባንፀባረቀበት የመጨረሻው ጨዋታ በወልቂጤ ከተማ ብልጫ ተወስዶበትም ቢሆን ማሸነፍ ችሏል።

ነገር ግን በጨዋታው ዋነኛ ጠንካራ ጎኑ የሆነው አማካይ መስመሩ ላይ ብልጫ ተወስዶበት ማለፉ ከድሉ ባሻገር ከእንደነገ ዓይነቱ ከባድ ጨዋታ በፊት ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው።
አማኑኤል ዮሃንስ እና ሬድዋን ናስርን በአንድነት ማሰለፉ በፈጠራው ረገድ አብዛኛው ኃላፉነት ታፈሰ ሰለሞን ላይ መጣሉ ብቻ ሳይሆን መዳረሻቸውን ወደ መስመር አጥቂዎቹ ያደርጉ የነበሩት ኳሶች ከወትሮው በተለየ ደካማ የመስመር ተከላካዮች ተሳትፎ በነበረበት ጨዋታ ላይ በተደጋጋሚ በተጋጣሚው ኮሪደሮች ላይ የማጥቃት ሂደቱ እንዲቋረጥ ምክንያት ሆነው ታይቷል።
ይህም በተለይም የቡድኑ የቀኝ ወገን የማጥቃት ስልነት አውርዶት ታይቷል።

በማጥቃቱ ረገድ በርካታ የግብ ዕድሎችን በሚፈጥረው ቡድን ውስጥ መሰል ክፍተት መታየቱም የነገው ጨዋታ በሊጉ ዝቅተኛ ግብ በማስተናገድ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ካለ ቡድን ጋር እንደመሆኑ የቡድኑን ትኩረት የሚስብ ይሆናል።

እንደ ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና ባይሆንም በአመዛኙ ለኳስ ቁጥጥር ከፍ ያለ ግምት የሚሰጠው ፋሲል ከነማም በቅዱስ ጊዮርጉሱ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን ሰበታንም ሲገጥም የማጥቃት ዕቅዱ የግብ ዕድሎችን በሚፈልገው መጠን መፍጠር ባለመቻሉ ተፈትኖ አሳልፏል።
ከሙጂብ ቃሲም ጀርባ ከሚጠቀማቸው አማካዮች ውስጥ በግራ እና በቀኝ የሚገኙ ተሰላፊዎቹ ወደ ተጋጣሚ ሳጥን ውስጥ የሚያደላ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ በመሆናቸው እና ከጎን የሚተዉትን ክፍተት ቡድኑ በአግባቡ መጠቀም ላይ ተዳክሞ መታየቱ ለችግሩ አንዱ ምክንያት ነው ማለት ይቻላል።
በሌላ ወገን መሀል ሜዳ ላይ ከኳስ ጋር የተሻለ ምቾት የሚሰማቸው ተጨዋቾችን የሚጠቀመው ፋሲል ነገ በዚህ የተጨዋቾች ምርጫው የተጋጣሚውን ቅብብሎች የማቋረጥ ብቃቱ ኳስ ከመያዝ ባሻገር በፈጣን ሽግግር ጎል ላይ የሚደርስበትን አማራጩን ስኬት የሚወስን ይሆናል።

ከዚህ ጎን ለጎን ቀጥታ ወደ ሳጥን የሚላኩት የሱራፌል ዳኛቸው መካከለኛ እና ረዥም ኳሶችም ሌላው የቡድኑ የማጥቃት አማራጮች ሊሆኑ ይችላሉ።


የነገው ጨዋታ በቡድኖች ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃም መሪዎቹን እርስ በእርስ የሚያገናኝ ነው። ዘንድሮ ቡድኑ ካደረጋቸው ጨዋታዎች ውስጥ በሦስቱ ብቻ ግብ ያልቀናው #አበበከር_ናስር የቡና ብቻ ሳይሆን የሊጉ አስደናቂ ተጨዋች እንደሆነ ቀጥሏል።

የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ፉክክሩ መሪ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ብቻ አምስት ጊዜ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል።
በተለይም በወልቂጤው ጨዋታ በድኑ በቂ ዕድሎችን ባይፈጥርም በግል ልዩነት መፍጠር እንደሚችል ባሳየበት ሁኔታ ለተከላካዮች ፈታኝ ሆኖ መታየቱ ነገ ከፍ ያለ የመከላካል ሪከርድ ካለው ቡድን ተከላካዮች ጋር የሚኖረውን ፍልሚያ ተጠባቂ ያደርገዋል።

ከአጥቂዎች ውጪ ሌሎች ተሰላፊዎች ግብ ማግባቱ ላይ በሚያደርጉት ትተሳትፎ ከተጋጣሚው ፋሲል ጋር ሲነፃፀር ደከም ያለው ቡና ነገም ዳግም የአስር ቁጥሩን ልዩ ብቃት የሚጠብቅ ይሆናል።

የፋሲሉ የግብ አዳኝ ሙጂብ ቃሲም ደግሞ ከዚህ በተለየ ወቅታዊ አቋም ላይ ይገኛል። ለሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች የዘለቀው የግብ ማስቆጠር ሂደቱ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ተቋርጦ ቆይቷል።
በጊዮርጊሱ ጨዋታ ላይ በፍቃዱ ዓለሙ መቀየሩ እና ፍቃዱም ለውጤቱ መገኘት ምክንያት መሆኑ ነገ የሙጂብን የሜዳ ላይ ደቂቃዎች ይበልጥ ዝቅ ሊያደርጋቸውም ይችላል።
ይሁን እንጂ መሰል ተጨዋቾች በትልልቅ ጨዋታዎች ላይ መልሰው ራሳቸውን አግኝተው ወደ ጥንካሬያቸው መመለስ የሚችሉ መሆኑ ሙጂብ በነገው ጨዋታ አንዳች ነገር ሊያደርግ እንደሚችል እንድንጠብቅ ምክንያት ይሆናል።
በተለይም ተጨዋቹ ፍጥነቱን እና ተክለ ሰውነቱን በመጠቀም በግብ ጠባቂው አቤል ማሞ ጥረት ሲድኑ የሚታዩ ከተከላካይ ጀርባ የሚጣሉ ኳሶችን የመጠቀም ዕድሉ የጎላ ይሆናል።

ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን ሲገጥም በሜዳ ላይ ተደጋጋሚ ጉዳቶች መታየታቸው ከነገው ጨዋታ በፊት ስጋትን የሚጭርበት ነበር።
ሆኖም የሀብታመ ታደሰ እና ወንድሜነህ ደረጄ ወደ ልምምድ መመለስ እንዲሁም በጨዋታው ምቾት አጥተው የታዩት ምንተስኖት ከበደ ፣ ሬድዋን ናስር እና ታፈሰ ሰለሞን መልካም ጤንነት ላይ መገኘት ለአሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ እፎይታ ነው።
ነገ የመድረሱ ነገር አጠራጣሪ የሆነው ኃይሌ ገብረትንሳይ ውጪ አስራት ቱንጆም ለነገው ጨዋታ ዝግጁ እንደሆነ ተስምቷል።
ከውጤት ባሻገር በአካል ብቃቱ ረገድ ጥሩ ዓመት እያሳለፉ የሚገኙት ፋሲል ከነማዎችም ሙሉ ስብስባቸው መልካም ጤንነት ላይ ሆኖ ነው ለነገው ጨዋታ የሚደርሱት።

የእርስ በእርስ ግንኙነት

ክለቦቹ እስካሁን በተገናኙባቸው ሰባት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ሦስት ጊዜ ፋሲል ከነማ ደግሞ ሁለት ጊዜ ማሸነፍ ችለዋል። ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን እስካሁንም ኢትዮጵያ ቡና 10 ፋሲል ከነማ ደግሞ 6 ግቦችን ማስመዝገብ ችለዋል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ኢትዮጵያ ቡና (4-3-3)

አቤል ማሞ

እያሱ ታምሩ – ወንድሜነህ ደረጄ – አበበ ጥላሁን – አሥራት ቱንጆ

ታፈሰ ሰለሞን – ረመዳን ናስር – ፍቅረየሱ ተወልደብርሀን

ሚኪያስ መኮንን – አቡበከር ናስር – ሀብታሙ ታደሰ

ፋሲል ከነማ (4-2-3-1)

ሚኬል ሳማኬ

እንየው ካሳሁን – ከድር ኩሊባሊ – ያሬድ ባየህ – አምሳሉ ጥላሁን

ሀብታሙ ተከስተ – በዛብህ መለዮ

በረከት ደስታ – ሱራፌል ጌታቸው – ሽመክት ጉግሳ

ሙጂብ ቃሲም

© ሶከር 

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
አሠልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ በየዛሬው ጨዋታ ለዋንጫው ወሳኝ መሆኑን ተናግረው ከባለፈው የወልቂጤ ጨዋታ መጠነኛ ለውጦችን አድርገው ወደ ሜዳ እንደገቡ ገልፀዋል። በዚህም #ኃይሌ_ገብረትንሳይ#ምንተስኖት_ከበደ እና #እያሱ_ታምሩን በአስራት ቱንጆ፣ ወንድሜነህ ደረጄ እና ዊሊያም ሰለሞን ተክተው ለጨዋታው ቀርበዋል።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሃን ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።
የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ኢትዮጵያ ቡና
99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
8 አማኑኤል ዮሃንስ
13 ዊሊያም ሰለሞን
15 ሬድዋን ናስር
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና
ስለጨዋታው

የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ትንሽ ኃይል የቀላቀለ ጨዋታ ነበር።
ቢሆንም ግን የመውጫ ቦታዎች ነበሩ።
ግን ኳሶች ሲበላሹ እና ሲቋረጡ ያንን ክፍተት እያገኙ የተወሰኑ ኳሶች ሞክረውብናል።
በዕረፍት ሂደቱን ሳንለቅ በዛ ክፍተት እንዳይጠቀሙ ክፍተቶችን እየዘጋን የጎል ዕድል መፍጠር ነበር።
ያው ከዕረፍት በኋላ ብዙ የተጨዋች ቁጥር እነሱ ሜዳ ላይ ነበር።
ወደ ጎል አካባቢ ቀርበናል ግን በመጨረሻ ላይ የነበሩ ውሳኔዎች ላይ ስህተት ነበር።
ያ ነበር የእኛ ድክመት።

ስለዋንጫ ፉክክሩ

ገና እንግዲህ ሁለተኛው ዙር መጀመሩ ነው። ይሄ ሁለተኛ ጨዋታችን ነው።
ስለዚህ ከዚህ በኋላ ብዙ ጨዋታዎች አሉ።
አሁንም ቢሆን ለቻምፒዮንነት ለመጫወት ዕድሉ አለን።

ሊሻሻሉ ስለሚገቡ ችግሮች

ተከታታይ ባይሆንም ጫና ሲፈጠር ኋላ ላይ የምንሰራቸውን ስህተቶች መቀነስ ፤ የራሳችን ስህተቶች ማለት ነው።
ምክንያቱም ተጋጣሚ ያን ኳስ ካገኘ በኋላ ነው የሚጠቀምበት።
ሌላ እንግዲህ ወደ ተጋጣሚ ጎል ስንቀርብ የቁጥር ክምችት ሲገጥመን ያን የምንቀርፍበትን መንገድ ነው ማስተካከል የሚኖርብን።
ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና- አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

#የባህር ዳር_ስታድየም የመጨረሻ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናል።
ጉዳት ያጋጠመውን ሱራፌል ጌታቸውን በሄኖክ ገምቴሳ ብቻ ለውጠው ወደ ሜዳ የገቡት የድሬዳዋው አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በጊዮርጊሱ ጨዋታ የነበረባቸውን የአጨራረስ ችግር ለመቅረፍ ልምምዶችን እንደሰሩ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ተናግረዋል።

በባህር ዳር የነበራቸውን ቆይታ በውጤት ለማገባደድ እንዳለሙ የተናገሩት አሠልጣኝ #ካሳዬ በበኩላቸው የፋሲልን ውጤት ሳያስቡ የራሳቸውን ሥራ ብቻ እየሰሩ ለመቀጠል ሀሳብ እንዳላቸው ተናግረዋለወ።

ከፋሲሉ ጨዋታም #ታፈሰ_ሰለሞን እና #አማኑኤል_ዮሃንስን በፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን እና እያሱ ታምሩ ለውጠው ለዛሬው ጨዋታ ቀርበዋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ

ምሽት ላይ ከሚጀምረው ጨዋታ በፊት ተከታዮቹን መረጃዎች እንድትጋሩ ጋብዘናል።

ባህር ዳር ላይ ድሬዳዋ ከተማን ካሸነፉበት ስብስብ ውስጥ የአንድ ተጫዋች ለውጥ ያደረጉት አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ #ፍቅረየሱስ_ተወልደብርሀንን#ታፈሰ_ሰለሞን ተክተዋል።
በሀዋሳ ከተማ በኩል ከሰበታ ከተማው ሽንፈት ሦስት የአሰላለፍ ለውጦች ተደርገዋል።

በለውጦቹ አሰልጣኝ መሉጌታ ምህረት ብርሀኑ በቀለ ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ እና ተባረክ ሄፋሞን በአለልኝ አዘነ ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና መስፍን ታፈሰ ቦታ ተጠቅመዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ ነመሀል ዳኝነት ይመራዋል።

የቡድኖቹ የዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ኢትዮጵያ ቡና
99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
14 እያሱ ታምሩ
15 ሬድዋን ናስር
13 ዊሊያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ቅድመ ዳሰሳ | ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ዛሬ ምሽት የሚደረገውን ተጠባቂው የሸገር ደርቢን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

የውድድር ዓመቱን አራተኛ ሽንፈት በሀዋሳ ከተማ ካስተናገዱ በኋላ ሰበታን በመርታት ዳግም ወደ አሸናፊነት የተመለሱት ኢትዮጵያ ቡናዎች የድል ጉዞዋቸውን ለማስቀጠል፣ ከመሪው ፋሲል ከነማ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ እንዲሁም ተጋጣሚያቸው ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ ከሚከተሏቸው ብድኖች ለመራቅ በነገው ጨዋታ ሦስት ነጥብ ያስፈልጋቸዋል።

ድል ካደረጉ አራት የጨዋታ ሳምንታት ያለፋቸው ቅዱስ ጊዮርጊሶች በበኩላቸው ከአስከፊው ውጤት አልባ ጉዞ ለመላቀቅ፣ ከመሪው ፋሲል ከነማ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ፣ ደረጃቸውን ለማሻሻል እና ከድል ጋር ለመታረቅ ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ቡድን (36) የሆነው የአሠልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ ኢትዮጰያ ቡና የፊት መስመሩ ስልነት ለተጋጣሚዎች የራስ ምታት ሆኗል።

ምንም እንኳን ቡድኑ ኳስን በትዕግሰት ተቆጣጥረው ከሚጫወቱ ቡድኖች መካከል ቀዳሚው ቢሆንም ፊት መስመሩ ትዕግስት እና ርህራሄ የሚባል ነገር አያውቅም።

በተለይም የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ #አቡበከር_ናስር ብቃት ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያገኝ እያስቻለው ይገኛል።
ነገም በተመሳሳይ ቀልጣፋው አቡበከር ፍጥነቱን እና ቴክኒካዊ ብቃቱን ተጠቅሞ የሚያደርጋቸው የጎል ፊት እንቅስቃሴዎች የጨዋታውን ውጤት እንደሚወስኑ ይገመታል።

ከእርሱ በተጨማሪ ከመስመር የሚነሱት የቡድኑ ተጫዋቾች ተጨማሪ የጎል ምንጭ እንደሚሆኑ ይታሰባል።

የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች ከኳስ ጋር ጥሩ ቢሆኑም ከኳስ ውጪ የሚያሳልፉት ጊዜ ብዙም የተዋጣለት አይደለም።
በተለይ ቡድኑ ከማጥቃት ወደ መከላከል በሚያደርገው ሽግግር ተጋጣሚዎች በጎ ነገሮችን ለራሳቸው እያገኙበት ይገኛል።

ከዚህም መነሻነት ነገ በዚህ ክፍተት ፈጣሪ የመከላከል አደረጃጀቱ ፈተና ላይ እንዳይወድቅ ያሰጋል።
በተጨማሪም ቡድኑ ኳስ ከኋላ ሲጀምር መጠነኛ የቅብብል ስህተቶችን ሲሰራ ይስተዋላል።

በተለይ ተጭኖት የሚጫወት ቡድን ሲገጥም ይህ ችግሩ በጉልህ ይታያል። ስለዚህም ቡና በዚህ ረገድ ነገ ችግር እንዳይገጥመው ያሳስባል።

በቡናማዎቹ በኩል የኮቪድ ውጤታቸው ዘገባውን እስካጠናከርንበት ወቅት ባይደርስም አቤል ከበደ እና ኃይሌ ገብረትንሳኤ በጉዳት ምክንያት ከነገው ጨዋታው ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ከአዲሱ አሠልጣኛቸው #ፍራንክ_ነታል ጋር ለመሻሻል የሚያልሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የ17ኛ ሳምንት አራፊ ቡድን በመሆናቸው ከሰበታ ጋር ጨዋታቸውን ካደረጉ በኋላ ወደ ቢሾፍቱ ተጉዘው ነበር።
ቡድኑ በቢሾፍቱም ልምምዱን ለሳምንት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ትናንት ከሰዓት ድሬዳዋ ደርሷል።
ነታል ሰበታን ሲገጥሙ ቡድኑ ላይ የታየው የእንቅስቃሴ መሻሻል ነገ የቡድኑ ደጋፊዎች ተስፋን እንዲሰንቁ አድርጓል።
በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ ተጫዋቾቹ ላይ የታየው የማሸነፍ ፍላጎት ከወትሮ ለየት ያለ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም ለበርካታ ጊዜያት ቡድኑ አቶት የነበረውም ፍጥነት በተወሰነ መልኩ አግኝቶት ተመልክተናል።
ከዚህም መነሻነት ነገም ቡድኑ ኳስ ሲይዝ በፍጥነት ነገሮችን ለመከወን ከሞከረ በጎ ነገሮችን ሊያገኝ እንደሚችል ይታሰባል።

ባለፉት አራት ጨዋታዎች በድምሩ ከሁለት ያልበለጡ ግቦችን ብቻ ተጋጣሚ ላይ ያስቆጠረው ቡድኑ ከነገው ጨዋታ ሦስት ነጥብ ከፈለገ ከመቼውም ጊዜ በላይ ስል ሆኖ መቅረብ አለበት።
እርግጥ ቡድኑ ግቦችን ማስቆጠር ብቻ ሳይሆን የግብ ዕድሎችንም በተደጋጋሚ የመፍጠር ችግር አለበት።
ከላይ እንደገለፅነው በሰበታው ጨዋታ የታየው ነገር በተወሰነ መልኩ ችግሩ ሊቀረፍ እንደሚችል ፍንጭ የሰጠ ቢሆንም ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ፊት ላይ አስፈሪ መሆን ይሻዋል።
ከዚህ ውጪ መጠነኛ ድክመት የሚታይበት የኋላ መስመሩ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ መሆን የግድ ይለዋል።

እንደ ኢትዮጵያ ቡና ሁሉ ይህንን ዘገባ በምንሰራበት ሰዓት የፈረሰኖቹም የኮቪድ-19 የምርመራ ውጤት ባይደርስም አዲስ ግዳይ እና ሮቢን ንጋላንዴ ባጋጠማቸው ጉዳት የነገው ጨዋታ እንደሚያመልጣቸው ታውቋል።

እርስ በእርስ ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ 41 ጊዜ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 ጨዋታ ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያ ቡና 7 ድል አሳክቷል።
በ16 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

በሸገር ደርቢ ባለፉት 41 ግንኙነቶች 78 ጎሎች ተቆጥረዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ 51፤ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 27 ጎሎች ማስቆጠር ችለዋል።

* ወቅታዊው የኮቪድ ወረርሺኝ በቡድኖቹ የስብስብ ምርጫ ላይ እያሳደረ ካለው ተለዋዋጭነት አንፃር ግምታዊ አሰላለፍ ለማውጣት አዳጋች በመሆኑ የወትሮው የአሰላለፍ ትንበያችን በዳሰሳው ያልተካተተ መሆኑን እንገልፃለን።

© ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ካሳዬ #ቴዲ_አፍሮ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
⚠️ከትላንት በስትያ ከቦርድ አመራሮች ጋር በምክትል አሰልጣኙ ዙሪያ ለመወያየት አዲስ አበባ የተመለሰው #ካሳዬ_አራጌ ወደ ደብረዘይት በመመለስ ልምምድ አሰርቷል ።

በዚሁ ዙሪያ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተልን ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል!

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ካሳዬ_አራጌ እና #ተክሌ_አበራ ተገናኝተዋል ስለ ቡናም ተጨዋውተዋል ተክሌ #አይነ_ስውር ቢሆንም በየጊዜው ወደ ስታዲየም በመምጣት የቡናን ጨዋታ ይከታተላል ።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ይመለሳል
#ካሳዬ_አራጌ የእረፍት ጊዜውን በአሜሪካ ከቤተሰቦቹ ጋር አሳልፎ #ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳል ከሐሙስ ጀምሮም #በልምምድ ሜዳ ላይ የሚገኝ ይሆናል ።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ምን_ላይ_ይገኛሉ
#የኢትዮጵያ_ቡና ዋናው ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ሊጉ ተቋርጦ በሚገኝበት ጊዜ ለተጫዋቾች የሳምንት እረፍት ተሰጦ የነበረ ሲሆን ከሳምንታት እረፍት በኃላ ግን #በምክትል አሰልጣኝ #ገብረ_ኪዳን (ጋምብሬ) አማካኝነት ልምምዳቸውን ሲያከናውኑ የቆዮ ሲሆን #ካሳዬ ከአሜሪካ ከገባ ጀምሮ ማለትም ከትላንት ጀምሮ ልምምዳቸውን ከካሳዬ ጋር መስራት #ቀጥለዋል
©eyobed

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈