አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
183K subscribers
4.94K photos
156 videos
14 files
750 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
የአቡበከር ናስር ወደ ታላቅነት ጉዞ
(ክፍል 1)

➡️በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ እግርኳስን የሚከታል ሁሉ ቅድሚያ ሊጠራው የሚችለው የተጫዋች ስም ግልፅ ነው።

➡️ አቡበከር ናስር! ከእድሜው የቀደመው ትንሹ ልጅ ዘንድሮ እጅግ በአስደናቂ መንገድ ላይ ይገኛል።

➡️እኛም የኢትዮጵያ ቡናውን አጥቂ ከሰፈር ሜዳ እስከ ዘመኑ ኮከብነት ያለፈበትን የእግርኳስ ጉዞ እንዲህ ቃኝተነዋል።

➡️ትውልድ እና እድገቱ በመዲናችን #አዲስ _አበባ በተለምዶ #ሾላ_ገበያ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ነው።

➡️በአካባቢው የሚገኘውና በአዲስ አበባ ለምልክት ከቀሩ የመጫወቻ ክፍት ቦታዎች አንዱ የሆነው “ጉቶ ሜዳ” ኳስን ማንከባለል የጀመረበት፣ ከመጫወት በዘለለ ብስክሌት ለማሽከርከር ለሚመጡ ወጣቶች በማከራየት ገቢ ለማግኘት የሚጥርበት ነበር።
በሰፈር ከእኩዮቹ ጋር ከመጫወት አልፎ በታዳጊ ቡድኖች የመቀላቀል ዕድል ያገኘው በፍጥነት ነበር።

➡️በ2006 ነገ ተስፋ በሚባል በአሰልጣኝ ደግፌ በሚመራ ቡድን ውስጥ ታቅፎ መሥራት ጀመረ።

➡️ በአቡበከር እድገት ትልቅ ሚና ከተጫወቱት ግለሰቦች አንዱ የሆነው አሰልጣኝ #ደግፌ የታዳጊው አቡበከር ሁኔታን ትናንት የሆነ ያህል ያስታውሰዋል። “አቡበከርን ማየት የጀመርኩት የካቲት ትምህርት ቤት ከ9–13 ዓመት ታዳጊዎች የፉትሳል ውድድር ላይ ነው።
በ2004 እና 2005 አካባቢ ማለት ነው።
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እርሱ ወደሚገኝባቸው ሜዳዎች ሁሉ ምግብ ሳልበላ እየተከተልኩ አየው ነበር።
በሚገርም ሁኔታ ከልምምድ ይልቅ ጨዋታዎችን የሚወድ ነበር።

➡️ብዙ ልምምድ ላይ ትኩረት አያደርግም ነበር። የውድድር ሰው ነው። አብረውት ከሚጫወቱ ተጫዋቾች ሁሉ እርሱ ላይ የተለየ አቅም አይበት ነበር።

➡️አብረውት እንደ ቡድን የሚጫወቱት እምብዛም ኳስ ላይ ያላቸው መረዳት እምብዛም የነበሩ ‘የማይችሉ’ ልጆች ነበሩ።

➡️ውድድር ላይ እርሱ ከእነርሱ የተሻለ ስለነበረ ይዘውት እንዲጫወትላቸው ይመጡ የነበረ ይመስለኛል።

➡️በዚህ መሐል እርሱ ጎልቶ ይወጣ ነበር። አቅሙ ከፍ ያለ ስለ እግርኳስ የአዕምሮ መረዳቱ ከፍተኛ የሆነ በጣም ተስዕጦ ያለው ልጅ ነበር።

➡️ እርሱን ሳየው ሰውነቴን ሁሉ ውርር ያደርገኝ ነበር። ገና ብዙ ነገር ከእርሱ እጠብቃለሁ።”

የአቡበከር የጨዋታ ዝግጁነት ከልጅነቱም የነበረ እንደሆነ የሚናገረው አሰልጣኝ ደግፌ በወቅቱ ያለውን አቅም እንዳያወጣ ሊያግዱ የሚችሉ ሁኔታዎችም እንደነበሩም ያስታውሳል። ” የሆነ ሰዓት ድንገት መጫወት አቆሞ ጥፍት ይልና እንደገና በራሱ ሰዓት በድጋሚ ይጫወት ነበር።

➡️ በዚህ ምክንያቶች በፍጥነት የታዳጊ ቡድኔ ውስጥ እንዳልቀላቅለው ፈተና ሆኖብኝ ነበር። በትምህርት ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ አልያም በሳምንት ሦስት ወይም አራት ቀን በልምምድ ማድረግ ስላለበት ከሚኖርበት ሠፈር ወደ የካቲት 19 ሜዳ መጥቶ ለመሥራት የትራንስፖርት ችግር የሚያጋጥመው ይመስለኛል።

➡️ ያም ሆኖ ታላቅ ወንድሙ ጅብሪል እኔ ጋር ይሰለጥን ስለነበረ አቡበከር እኔ ጋር እንዲሰራ እጠይቀው ነበር። መጨረሻም 2006 የነገ ተስፋ የሚባል የኔ ቡድን ውስጥ ገብቶ ይሰራ ጀመረ።” ይላል።
#አቡበከር በነገ ተስፋ ቡድን ብዙም ሳይቆይ ፈለቀ በሚባል ግለሰብ አማካኝነት ታዳጊዎችን በማፍራት ጥሩ ስም ወዳለው #ኒያላ ታዳጊ ቡድን ሙከራ እንዲያደርግ እድል ተመቻቸለት።

➡️ ሆኖም የቡድኑ የልምምድ ሜዳ ከመኖርያ ቤቱ መራቅ እክል መፍጠሩ አልቀረም።

➡️ለጥቂት ጊዜ እስከ ቃሊቲ እየተጓዘ ልምምድ ማድረጉ ሲከብደውም ለማቆም ተገደደ።

➡️ የዚህ ጊዜ ነበር የእግርኳስ ህይወቱን መልክ ወዳስያዘለት #ሐረር_ሲቲ ያመራው።

➡️ክለቡ አዲስ አበባ መቀመጫውን አድርጎ የሚወዳደር ታዳጊ ቡድን ለማቋቋም በ2007 ምልመላ ሲያካሂድ የታዳጊ ቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ደግፌ ለቡድኑ እንዲጫወት አደረገውና በድጋሚ ተገናኙ።

➡️በቀድሞው አጥቂ #እስማኤል አቡበከር በሚመራው #ሐረር_ሲቲ እንደተጫዋች መገራት እና መጎልበትም ጀመረ።
አቡበከር እንደታዳጊ የመጫወት ፍላጎቱ ከፍተኛ ነበር።

➡️ በአካባቢው የኳስ መጫወቻ ሜዳ ከመኖሩ እና ቤተሰቡም ከኳስ ጋር ጥሩ ቁርኝት ያለው እንደመሆኑ ለኳስ የነበረው ፍቅር “ለጉድ” ነበር።

➡️ይህ የኳስ ፍቅሩም #በሐረር_ሲቲ ይበልጥ ራሱን እንዲገልፅ እና እንዲያብብ ረዳው።

➡️ በቡድኑ አሰልጣኝ #እስማኤል አቡበከር ከፍተኛ እገዛ እዚህ እንደደረሰ የሚናገረው አቡበከር ወደ ልምምድ ለመሄድ የትራንስፖርት ለመክፈል ሲቸገር እንኳ ከኪሱ እያወጣ እንደሚሰጠው በአንድ ወቅት ለድገፃችን ተናግሯል።

➡️በቡድኑ ውስጥ እድገት ቢያሳይም ከሌሎች የተለየ የአዕምሮ ብስለት የነበረው መሆኑ ጎልቶ እንዲወጣ ሳያደርገው አልቀረም። ” ከሌሎች ተጫዋቾች የተለየ የሚያደርገውና በጨዋታ መሀል እርሱ ጎልቶ እንዲወጣ የሚያስችለው ኳስ አያያዝ፣ ኳስ አገፋፍ፣ ለጓደኛ የማቀበል ዕይታ፣ የቦታ አጠቃቀሙ፣ እያሰበ መጫወቱ በስልጠና ያልዳበረ የተፈጥሮ ችሎታ እንደነበረ ያስታውቅ ነበር።
➡️#አቡበከር ጎልቶ መውጣት የነበረበት አሁን ሳይሆን ገና ከልጅነቱ ዕድሜ ጀምሮ መሆን ነበረበት።

➡️ ከሲ ቡድን ነተስቶ ነው በቀጥታ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው።

➡️ይህ የአዕምሮ ብስለቱን ያሳያል” ይላል።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈