አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
771 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
#ወድማማቾቹ በአንድ ቡድን ውስጥ

#የአቡበከር_ነስሩ (አቡኪ) ወንድም #ሬድዋን_ነስሩ የኢትዮጵያ ቡና ዋናውን ቡድን ተቀላቅሏል የሙከራ እና የምልመላ ጊዜ በነበረበት ሰዓት በመታየት ነው ወደ ዋናው ቡድን መቀላቀል የቻለው ሬድዋን ነስሩ ያሳለፍነውን አመት #በአዲስ_አበባ ከነማ የተጫወተ ሲሆን ከ17 አመት #ብሔራዊ_ቡድንም መጫወት ችሏል።
እንኳን ደህና መጣህ ወደ ተወዳጁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና

© #eyobed_belayneh_coffee

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ3 ስታዲየሞች ብቻ ይካሄዳል !!

🏟 መቐለ
🏟 ባህርዳር
🏟 አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጠራው የውይይት መድረክ ዛሬ ተጀምሯል፡፡ 68 ክለቦች ከሚነጋገሩበት ጉዳዮች አንዱ የውድድር አካሄድን ይመለከታል፡፡

ውድድሮቹ በ3 ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን ከ1-5ኛ ሳምንት ያሉ ውድድሮች #መቐለ ላይ ከ6 -10ኛ ሳምንት ያሉ ደግሞ #ባህርዳር ላይ ከ11-15ኛ ሳምንት ደግሞ #በአዲስ_አበባ የማካሄድ ዕቅድ ተይዟል፡፡

የኮቪድ ምርመራ ወጪውን መንግስት እንዲችል የታሰበ ሲሆን ጨዋታ አይተው ብቻ የሚወጡ ጋዜጠኞች የምርመራ መረጃ እንዲያቀርቡ አይገደዱም።

ከጨዋታ በኋላ አሰልጣኞችን ቃለምልልስ የሚሰሩ ታች ትራኩ አካባቢ እንዲገኙ የሚፈቀድላቸው ጋዜጠኞችና ካሜራ ማኖች የኮቪድ 19 ምርመራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ተብሏል።
©yosef

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
☕️#አቡበከር ናስር እና ሚኪያስ መኮንን ስለ ውል ማራዘማቸው ይናገራሉ

☕️#በኢትዮጵያ እግርኳስ አንድን ተጫዋች ረዘም ላለ ሁኔታ ማስፈረም በማይቻልበት ሊግ የኢትዮጵያ ቡና ወጣት ተጫዋች የሆኑት አቡበከር ናስር እና ሚኪያስ መኮንን እስከ 2017 ድረስ ለአምስት የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ቡና የሚያቆያቸውን ኮንትራት ከሰዓታት በፊት መፈረማቸው ይታወቃል። ይህን አስመልክቶ አቡበከር እና ሚኪያስ ረዘም ላለ ጊዜ በኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት የተስማሙበትን ምክንያት ሶከር ኢትዮጵያ በተመለከተ አጭር ቆይታ አድርገዋል።
☕️#አቡበከር ናስር
☕️# “የአሸናፊ በጋሻውን ታሪክ ለመድገም ኮንትራታችንን ለረጅም ዓመት አራዝመናል። ይህ በመሆኑ በጣም ደስ ብሎኛል። በኢትዮጵያ ቡና እስካሁን በቆየንበት ዓመታት ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። በቀጣይም አቋማችንን ጠብቀን ለመዝለቅ እና የምንወደውን ኢትዮጵያ ቡናን እስከ መጨረሻው ለማገልገል ውላችንን የረዥም ዓመት ልናደርገው ችለናል።”
☕️#ሚኪያስ መኮንን

☕️#”ለኢትዮጵያ ቡና ካለን ከፍተኛ ፍቅር ኮንትራታችንን ለአምስት ዓመት ለማራዘም ወደናል። እኛን ለዚህ ያበቃን ክለባችንን ለቀን ላለመሄድ በማሰብ እና አንዳንድ በደሞዝ ጉዳይ ማሻሻያ ተደርጎልን ለመጫወት ችለናል። ባሳለፍነው እሁድ አንተም እንዳየኸው በአሸናፊ በጋሻው የዕውቅና ፕሮግራም ላይ ቃል ገብተን የነበረ በመሆኑ ያንን ቃላችንን ለማክበር በዛሬው ዕለት ስምምነታችንን ፈፅመናል።”

☕️#በአዲስ አበባ ሾላ ጉቶ ሜዳ አብረው ያደጉት ሁለቱ ወጣቶች ተስፋ ፍሬ ከሚባል ቡድን የእግርኳስ መነሻቸውን በማድረግ በሐረር ሲቲ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ባሳዩት ድንቅ አቋም ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ2008 በጥምረት መጫወት ችለዋል። ያለፉትን አራት የውድድር ዓመታት በቡናማዎቹ ማልያ በመጫወት ያሳለፉ ሲሆን አሁን ደግሞ አንድ እና ሁለት ዓመት ውል መፈራረም ብቻ በተለመደበት የኢትዮጵያ እግርኳስ ባህል በተለየ ሁኔታ ለአምስት ተጨማሪ ዓመታት (እስከ 2017) በክለቡ ለመቆየት ተስማምተዋል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንታት ጨዋታዎች የሚደረጉበት ሜዳ ተወስኗል
#ታኅሣሥ 3 እንደሚጀመር የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት ሳምንታት ጨዋታዎች የት እንደሚደረጉ ከውሳኔ ተደርሷል፡፡
#የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ #የኮቪድ 19 የመከላከል ሒደትን በመከተል የሚደረግ ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ ሳይሆን በተመረጡ ስታዲየሞች ላይ ብቻ እንደሚካሄድም ይታወቃል። የሊግ ኩባንያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ፕሪምየር ሊጉ ታኀሣሥ 3 ሲጀመር የመጀመሪያዎቹ #አምስት ሳምንታት ጨዋታዎች #በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲደረጉ መወሰኑን ገልፀውልናል፡፡ #አቶ ክፍሌ በገለፃቸው# “ከዲኤስቲቪ ጋር ተነጋግረን ነበር የመጀመሪያ አምስት ሳምንታት# 40 ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲሆን ወስነናል። በቀጣይ ቀሪዎቹን #አምስት ሜዳዎች እና የሚደረጉትን ጨዋታዎች እንገልፃለን።” በማለት ተናግረዋል፡፡
#የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርአት በቀጣይ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ላይ እንደሚወጣ የተሰማ ሲሆን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ለመስጠትም ትናንት ምሽት የዲኤስ ቲቪ ባለሙያዎች አዲስ አበባ እንደገቡ አቶ ክፍሌ አክለው ነግረውናል፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈