የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

እንኳን ለአዲሱ አመት 2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

በዓሉ ስናከብር በኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ ባህልና እሴት መሰረት ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችን እያሰብን ያለንን በማካፈል ፣ ማእዳችንን በማጋራትና ሊሆን ይገባል ፡፡

ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፎችን በመቆጣጠር፣ በመከላከልና ተፈፅሞም ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ከተማዋ ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ እንድትሆን ለማድረግ እየሠራ ይገኛል።

በከተማዋ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፎች በጋራ በመከላከል ሀገራዊ ግዴታችን እንወጣ እያለ ጥሪውን ያቀርባል።

መልካም አዲስ አመት!!!
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ
1
ባለሰልጣኑ ለሴና ሰባ ትምህርት ቤት የትምህርት መሳሪያዎችና ለተማሪዎች ምገባ የሚሆን ድጋፍ አደረገ

መስከረም 3/2017 ዓ.ም
* አዳማ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አዳማ ለሚገኘው ሴና ሳባ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ለተማሪዎች ምገባ የሚሆን ድጋፍ አደረገ።

የተደረገው ድጋፍ የባለስልጣኑ ዋና ስራ- አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ለአዳማ ከተማ አፈ-ጉባኤ የወረዳው አመራሮች በተገኙበት አስረክበዋል።

በርክክቡ የባስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በንግግራቸው በአዳማ ከተማ መስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የጎሮ ወረዳ ፅ/ቤት ስር ለሚገኘው ለሴና ሰባ ትምህርት ቤት በተደረገው ጥሪ መሰረት የትምህርት ቁሳቁስና ለተማሪዎች ምገባ የሚሆን ድጋፍ መደረጉ ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታቸው መሆኑ ገልፀዋል።

አክለውም እንደ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመረዳዳት እና የመቻቻል ባህል በማዳበር ከከተማ ወጣ በማለት ይህን ድጋፍ አድርገናል ተግባሩም በቀጣይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር አፈ ጉባኤ የሆኑት ወ/ሮ እመቤት ጅባ በበኩላቸው ህፃናት ተማሪዎች ላይ መስራት ሀገር ላይ እንደመስራት ነው ብለው በዛሬው ዕለትም የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለተማሪዎቻችን የተደረገ ድጋፋ እጅግ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ገልፀው ለባለስልጣኑ ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው።
👍4
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ