የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ 1499ኛው የመውሊድ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
መስከረም 4/2017
*አዲስ አበባ6
ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1499ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት / የመውሊድ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
የመውሊድ በዓል የሰላም ፣የጤና ፣የደስታ፣የፍቅር እና የመረዳዳት በዓል እንዲሆንልን እየተመኘሁ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በአብሮነት፣በመተሳሰብና ለተቸገሩ ወገኖች በመርዳት፣ ያለውን በማካፈል በአሉን በማክበር የተለመደው አብሮነቱን እንዲያስቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።
በዚሁ አጋጣሚ ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚከሰተውን የደንብ መተላለፍና ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ስራ ላይ ሁሉም ዜጋ በማገዝ ከተማችን የደንብ መተላለፍ የማይስተዋልባት፤ ለነዋሪዎቿና እንግዶቿ ምቹ እንድትሆን የበኩሉን እንዲወጣ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
በድጋሚ በራሴ እና በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ስም መልካም በዓል እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ!!
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረው እንዲውሉ በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ሁለቱ የአደባባይ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረው እንዲውሉ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት፡- ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የፀጥታ ግብረ ሃይል በማቋቋም የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረው እንዲውሉ ለማድረግ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የመሬት ወረራ፣ህገ-ወጥ ግንባታ በሚያደርጉ፣ያልተፈቀዱ መልዕክቶችን በሚያትሙ የህትመት ድርጅቶች እና እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ከአጎራባች ከሸገር ከተማ ጋር በቅንጅት ለማስራት ዝግጅት መድረጉንም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናግራዋል፡፡
በመጨረሻም ወ/ሮ ሊዲያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የመስቀል ደመራ መትከያ ቦታዎችን ከኤሌክትሪክ ሃይልና ከገበያ ማዕከላት በማራቅ እንዲሁም የኮሪደር ልማቱን በማያበላሹበት ሁኔታ እንዲሰሩ የሃይማኖቱ ተከታዩች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ህብረብሄራዊ አንድነትን ባሳተፈ መልኩ ያለምንም የጸጥታ ችግር የመስቀል ደመራ በዓልን እንዲያከብሩ ጭምር አሳስበዋል።

👍4
ባለስልጣኑ ለሰራተኞቹ የኤች አይቪ ኤድስ ሚኒስትሪሚንግ ስልጠና ሰጠ
10/01/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የማዕከል ሰራተኞች በኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት እና አጋላጭ ሁኔታዎች ዙሪያ በኤች አይቪ ሜን እስትሪሚንግ ፎካል ፕርሰኖች አማካኝነት በዛሬው ዕለት ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ለስልጠናው የሰጡት የተቋሙ የኤች አይ ቪ ኤድስ ሚኒስትሪሚንግ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አባይነህ ጥጋቡ እንዳሉት የፖለቲካ አመራሩ፣ ማህበረሰቡ እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በኤች አይ ቪ ኤድስ ቅድመ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ የነበራቸውን ሚና አጠናክረው ሊያስቀጥሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ኤች አይ ቪ ኤድስ መከሰቱ ከታወቀበት እ.ኤ.አ 1981 ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ32.7 ሚልዮን በላይ ሰዎችን ህይወት የነጠቀ ገዳይ በሽታ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ አለመጠቀም፣ በቂ እውቀት አለመኖር እና መጤ ባህሎችና ድርጊቶች መስፋፋት ለበሽታው ተጋላጭነት እንዳሰፋው ተገልጿል።
ኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት በአዲስ አበባ ከተማ እንደ ሀገር 2ኛ ደረጃ ሲሆን፣ ይህም በወጣቶች አልባሌ ሥፍራ መዋል፣ሴተኛ አዳሪዎች እና ቱሪስቶች የሚገኙበት አከባዎች በስፋት ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሆኑ የሀይማኖት አባቶች፣ ሽማግሌዎች፣ሲቪል ማህበራት ከመንግስት ጋር በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ቢሰሩ የቫይረሱ ስርጭት ይቀንሰዋል ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከብር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

👍3
203 የካሳንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ በዛሬው እለት አውጥተዋል፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የካዛንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓቱ እንደቀጠለ ነው፡፡
በአጠቃላይ በ3 ቀናት ውስጥ የዛሬውን ጨምሮ 428 የልማት ተነሺ የካሳንቺስ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ በማውጣት ቤታቸውን እየተረከቡ ይገኛሉ።
ባለ አንድ እና ባለ ሁለት መኝታ የመንግስት መኖሪያ ቤቶችን በአቃቂ፣ አራብሳ፣ገላን፣ ፈረንሳይ ጉራራ እና ጃርሶ ሳይት የመኖሪያ መንደሮች ለባለእድለኞች በእጣቸው መሰረት ተደራሽ እየተደረገ ነው።
የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ነገን ጨምሮ በቀጣይ ቀናትም እንደሚቀጥል ተገልጿል።
የልማቱ ተነሺዎች ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካለቸው በክፍለ ከተማው አስተዳደር 10ኛ ፎቅ ወደተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ ወይም በ9065 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉም ተገልጿል።