የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
"የህዳሴ ግድባችን በትናንትናው ዕለት 3ኛው እና 4ኛውን ተርባይኖች ሥራ አስጀመርን። ሌሎቹ ዩኒቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ"።

መከናወንን የሰጠን ፈጣሪ ይመስገን!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
👍3
ባለስልጣኑ መሬት የወረሩ እና ባልተፈቀደ ቦታ ሽንት የሸኑ 22 ግለሰቦች መቅጣቱ አስታወቀ

ነሀሴ 20/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ6**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የህዝብና የመንግስት የሆነ መሬት በህገወጥ መንገድ የወረሩ ግለሰቦች እና በከተማው ባልተፈቀደ ቦታ ሽንት የሸኑ 22 ግለሰቦች መቅጣቱ አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረደ 11 ባልታፋቃደ ቦታ ሽንታቸው ሸንተው አካባቢ ያቆሸሹ 22 ግለሰቦች በባለስልጣኑ በተሻሻለዉ የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት 22 ሰዎች እያንዳንዳቸው 2000 ሺህ ብር አጣቃላይ 44000 ሺህ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማደረጉ ገልጿል ።

በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የህዝብና የመንግስት የሆነ መሬት በህገወጥ መንገድ በመውረር ታጥሮ የነበረ 5 ቦታዎች በአጠቃላይ 2,200 ካሬ ሜትር መሬት በአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እርምጃ መወሰዱ ባለስልጣኑ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በህገ ወጦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ሆን ብለዉ ደንብ የሚተላለፉ አንዳንድ ግድ የሌሽና ስግብግብ ግለሠቦች ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጠይቋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
👍8💔2
እንኳን ደስ አላቹ እንኳን ደስ አለን!!!

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ እውቅና ተሰጠው

            ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም
            **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ በተሰራው የልማት ኮሪደር ስራዎች ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከኢትትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የፌደራልና እና የከተማው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እውቅና እና የወርቅ ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጁ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በከተማው የልማት ኮሪደር ስራዎች ከተጀመረባቸው ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ በ7/24 እየሰራ በከተማ አስተዳደሩ በተያዘው እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣኑ በተለይ በተሰራው የኮሪደር ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ እና ውበቱና ጽዳቱ ለማስጠበቅ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር እና በደንቡ መሰረት አስተማሪ ቅጣት በመቅጣት ደንብ እያስከበረ መሆኑ ገልጸዋል፡፡

ዋና ስራ-አስኪያጁ ለተቋማቸው በተሰጠው እውቅና አመስግነው በለቀጣይ የበለጠ ስራ ለመስራት ትልቅ መነቃቃትን አንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡

ዋና ስራ-አስኪያጁ ባለስልጣኑ በተሰጠው እውቅና እና የወርቅ ሰርተፊኬት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች፣ኦፊሮች፣መላው የጠቋሙ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካሎቻችን ለስራችሁ ውጤት አግኝታችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ዘገባው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍13
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ያስገነባውን አዲስ ቢሮ አስመረቀ

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከነበረበት የቢሮ ጥበትና እጥረት ምክንያት ወረዳውንና ሌሎች በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር ያስገነባውን ምቹና ያማረ የስራ ቦታ(ቢሮ) በቀን 25/12/16ዓ/ም ያስመረቀ ሲሆን በምረቃ ስነስርአቱ የተገኙት የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሲ/ር ግሩም ንጉሴ እንደገለፁት የወረዳው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት 7/24በመስራት አናፂም ግምበኛም እራሳቸው በመሆንይህን የመሠለ የስራ ቦታ በመገንባት ለተገልጋይ ክፍት እንዲሆን አስችለዋል ።

ስራ አስፈፃሚዋ አያይዘው እንደገለፁት የተሰራው ስራ ለሌሎች ምሳሌ እንደሆነ አስቀምጠው መልካም የስራጊዜ እንዲሆን ተመኝተዋል።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ  ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ እንዳስቀመጡት ጽ/ቤቱ ሰፊ ተልእኮ ተሰቶት እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ ነው በተጨማሪ ከልማት ኮሪደር ጋር በተያያዘ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው የወረዳው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የነበረበትን የቢሮ ጥበት ለመቅረፍ የተሰራውን ስራ እንደተቋም እየደገፍን በዚህ ያማረ የስራ ቦታ ከብልሹ አሰራር  ነፃ የሆነ የህዝብ አገልጋይ እንደምትሆኑ ተስፋ አደርጋለው በማለት ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

የወረዳው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ በቀለ በወረዳዉ እንደጽ/ቤት ከነበረብን የቢሮ ጥበት የተነሳ በተገልጋይ ላይ ችግር ሲፈጥርብን ነበር ነገርግን ከወረዳው አመራርና በጎ ፈቃደኞች ጋር በመነጋገርና በመግባባት ሁሉም የጽ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች ለስራው ግምባር ቀደም ሆናችሁ ለሰራቹት ስራ ምስጋና ይገባቹሃል በማለት ።

መረጃው፡-የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ነው።
                   
👍8👏2