የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.79K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ  ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል።

ህፃናት ተስፋቸውን ተክለዋል። ወጣቶች ጽናተቸውን አሳይተዋል። አረጋውያን ውርስ አኑረዋል። ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከቤታቸው ወጥተው የማይደበዝዝ አሻራ አኑረዋል። በማበራችን እና በመጽናታችን በአለም በሌላ ስፍራ በአንድ ጀምበር ያልተደረገውን እኛ ኢትዮጵያውያን አድርገነዋል። ዛሬ ለአየር ንብረት ለውጥ ሚዛን ጥበቃ ቆመን ውለናል። የአፈር መራቆትን ለመመከት ተሰልፈን ውለናል። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ስንደክም ውለናል። ምድራችንን አረንጓዴ ለማልበስ ልምላሜን ለመመለስ ሳንበገር ሰርተናል። ፈጣሪም ረድቶን ለዛሬዋ ጀምበር ያሰብነውን አሳክተናል።

ዛሬ 29.1 ሚሊዮን ዜጎች በ318.4 ሄክታር በጂኦስፓሻል መረጃ በተገኘባቸው ስፍራዎች ላይ ችግኞችን ተክለዋል። እስካሁን በመረጃ ቋት ከተመዘገበው ውጭ የተተከሉ ችግኞች መረጃ በተከታታይ የሚገለፅ ይሆናል።

ለአስደማሚው የኢትዮጵያውያን ኅበረት እና ጽናት እነሆ ምስጋና። ለስኬታችን የእቅድ፣ የክትትል እና የመረጃ አውታር በመሆን በትጋት የሰራችሁ አመራሮች ባለሞያዎች እና የሚዲያ ተቋማት ምስጋና ይገባችኋል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው። ይኽንኑ እንቀጥላለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!!
እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮጵያውያን የዛሬ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል የቻልን ሲሆን ከዚህም ውስጥ እንደ አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን አቅደን 9.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል::

የከተማችን ነዋሪ የመሪችንን ጥሪ ተቀብሎ ማልዶ በመነሳት በአስደናቂ አፈፃፀም ከእቅድ በላይ ችግኞችን በመትከል ታሪክ የማይዘነጋው ታላቅ ገድል በመፈጸሙ ታላቅ አክብሮት ከምስጋና ጋር የሚገባው ሲሆን በተጨማሪም ይህ እንዲሳካ ያስተባበራችሁ እና የደከማችሁ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞቻችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

ይህ ዛሬ ያሳየነውን የተባበረ ክንድ የሚያመጣውን ለውጥ በሌሎች የልማት ስራዎቻችን ላይ በመድገም የሃገራችንን ብልፅግና እውን እንድናደርግ ጥሪዬን አቀርባለሁ::
የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
3👍2👏1