የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ለነዋሪዎች የበዓል ቅርጫ እርድ ክልከላ አለመደረጉ ተገለፀ

ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያው መረጃ እየተሰራጨ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የቅርጫ ስጋ እርድ ክልከላ ያልተደረገ መሆኑና በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገ ጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጿል።

የከተማችን ነዋሪ በዓላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው፦የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ነው::
6👍2
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም የፍቅር የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል ፣በመቆጣጠርና ተፈፅሞ ሲገኝ እርምጃ በመውሰድ ከተማዋ ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ እንድትሆን ለማድረግ እየሠራ ይገኛል።

ሰለሆነም መላው የከተማው ህብረተሰብ ከባለስልጣኑ ጎን በመሆን መዲናችን ህገ-ወጥነትና የደንብ መተላለፎች የማይስተዋልባት ከተማ ለማድረግ በጋራ እንስራ እያልኩ በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
             
                     መልካም በዓል!
                   ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ዋና ስራ አስኪያጅ
👍6
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የፅ/ቤቱ ሰራተኞች ማዕድ አጋራ

             26/08/2016 ዓ.ም
             አዲስ አበባ

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 01 የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት ዝቅተኛ ደሞዝ ላላቸው 41 ለሚሆኑ የፅ/ቤቱ ሰራተኞች ዱቄትና ዘይት በስጦታ ማበርከቱን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 01 የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት እሊሊ ጌታቸው ገልፀዋል::

ከፅ/ቤቱ ሰራተኞች በተጨማሪም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ  የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ለሚያሳድጋቸው 9 ህፃናት ለዶሮ መግዣ የሚሆን ብር እና በዓይነት ዱቄት፣መኮረኒ፣ ሩዝ፣ሶፍት፤ሳሙና እንዲሁም   ለሚያሳዲጋቸው ህፃናት እና 13 ለሚሆኑ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በስጦታ ማበርከቱን የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እሊሊ ጌታቸው ገልፀዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም  በፕሮግራሙ  ላይ ተገኝተው እንኳን ለጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል  አደረሳችሁ የሚል መልዕክት በማስተላለፍና  በአሉን በአብሮነት እና በመተሳሰብ ካለን ላይ አካፍለን እና ተካፍለን መብላት ባህላችን በመሆኑ ልበ ቀናዎች በማስተባበር ይህን ማዕድ ማጋራታቸውን ገልፀዋል፡፡
👍7
ፕረስ ሪሊዝ

በከተማዋ የደንብ መተላለፎችን በተጠናከረ ሁኔታ ለመቆጣጠር ለደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገለፀ።

ሚያዚያ 28/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ የሚታየውን የደንብ መተላለፎችና ህገ-ወጥነት በተጠናከረ ሁኔታ መቆጣጠር እንዲቻል ከ5000/አምስት ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ የነባር ኦፊሰሮች አቅም ለመገንባት ወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው ማክሰኞ ሚያዚያ 29/08/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የመክፈቻ ፕሮግራም እንደሚካሄድ የባለስልጣኑ የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ አዳነ ለገሰ ገልፀዋል።
👍19
ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል የህዝብ አገልጋይነትን ስሜትን ተላብሰው መውጣት ይገባቸል

ሚያዚያ29/2016ዓ.ም
**ሰንዳፍ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኢትዮጲያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ ነባር 910 የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች የባለስልጣኑ እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ወታደራዎ እና ንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የኢትዪጵያ ፓሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ በመድረኩ በመክፍቻ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት የፀጥታ አካላት አጋዧች መሆናችሁ እና የከተማዎን ፀጥታ ለማስከበር በመስራት ላይ መሆናችሁ የሚታወቅ ነው።

በመሆኑም በተቋማችን የህዝብ አገልግሎት ያለውን ባህሪ እና እሴት ተግባራዎ በሆነ ስልጠና እውቀታችንን እና ችሎታችንን ሳንሳስት የምናካፍላችሁ ይሆናል ብለዋል።

አክለውም ተቋማቸው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሰሮችን ተቀብሎ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ እና ታሪካዊ መሆኑንም ገልፀዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ በመድረኩ ንግግር ሲያደርጉ እንዳሉት በመጀመሪያ የኢትዮጲያ ፓሊስ ዮኒቨርስቲ የተቋሙን ሀሳብ በመቀበል በትብብር ለመስራት ፍቃደኛ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተግባር እና ኃላፊነት እየተወጣ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ገልፀው በተቋማችን የሚገኙ ኦፊሰሮች የደንብ መተላለፎችን ከመከላከል እና መቆጣጠር ባሻገር በተለያዮ የፀጥታ ስራዎች ላይ የፀጥታ ኃይል አጋዥ ሆነው የሚያገለግለሉ መሆኑ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም ከነበረው የመከላከል እና የመቆጣጠር ዘዴ በመቀየር ከከተማዋ እድገት ጋር ፈጣን መሆን ያስፈልጋል ለዚህም ለኦፊሰሮቻችን ወታደራዊ እና ንድፈ ሀሳባዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ይህም ስልጠና በ5 ዙር በመክፈል ለ 1ወር ያህል የሚቆይ እና ወደ 5000 ያህል ሰልጣኞችን የሚይዝ ነው ብለው። በዚህ ስልጠና ላይ የምትሳተፍ ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ዕውቀታችሁን አቅማችሁንና ስነምግባራችሁን የሚገነባውን ስልጠና በአግባቡ ሊከታተሉ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው።
👍42
የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አዋኪ ተግባር ማስጠቀሚያ እቃዎች አስወገደ።

ግንቦት 1/2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው በተለያዩ ቦታዎች አዋኪ ድርጊቶች ሲከናወን እርምጃ በመውሰድ የወረሳቸውን የሺሻ ማስጨሻ እቃዎችን በማቃጠል አስወገደ ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ከሰላምና ጸጥታ እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተለያዩ ጊዜያቶች ከተለያዩ ንግድ ቤቶች ፣ ሆቴሎች ፣መኖሪያ ቤቶችና ከፔንሲዮኖች በተደረገ ክትትልና ድንገተኛ ኦፕሬሽን ከ1000 በላይ የሺሻ ማስጨሻ እቃዎችን በመውረስ በዛሬው ዕለት በማቃጠል
እንዲወገዱ ተደረገ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን እንደገለፁት በጊዜው ድርጊቱን ሲያከናውኑ የተገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ እቃዎቹ የተወረሱ መሆኑን ገልጸዋል ።

አክለውም ህብረተሰቡ መሰል አዋኪ ድርጊቶች ሲፈጽሙና ሲያስጠቅሙ ከተመለከተም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በመጠቆምና በነፃ የስልክ መስመር 9995 ትብብሩን ሊያደርግ እንደሚገባም ኃላፊው ተናግረዋል ።

የክ/ከተማው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ም/ኢንስፔክተር ፍፁም ወልደ አንደተናገሩት አዋኪ ተግባራት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የክትትል ስራዎችን በማጠናከር እንዲቀንሱ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።

ህብረተሰቡ በአሁኑ ሰዓት ህገ ወጥነትን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ስራ በማጠናከርና በባለቤትነት ተባባሪ በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባና ከመሰል አዋኪ ተግባራት ራሳቸውን በማራቅ ለሌሎች አርዓያ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
2👍1