የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

ሚያዝያ/16/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለማዕከል አመራሮች፣ሰራተኛና ከ11 ክ/ከተማ ለተወጣጡ FOCAL PERSON ተባባሪ አካላት በሙስና ወንጀልና በብልሹ አሰራር ለመግታት ከባለስልጣን ሰራተኞች ምን ይጠበቃል በሚል ፅንሰ ሀሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ የስልጠና ዓላማ እንደ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተቋም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመግታት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው የባለስልጣኑ የጸረ ሙስናና የስነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ እዮብ ከበደ የተሰጠ ሲሆን ደንብና መመርያ መጣስ ፤በስራ ላይ የራስን ጥቅም ማስቀደም ሙስና እና ብልሹ አሰራር መሆኑ ገልፀዋል፡፡

ሙስናን እንደሀገር ይሁን እንደ ተቋም በቀላሉ ተቆጣጥሮ መግታት ያልተቻለው፤ ሰውርና ውሰብስብ ባህሪ ያለው በመሆኑ እና በህብረተሰቡ ዘንድ እንደ ነውር አለመታየቱ እንደዚሁም ሌብነት እንደ ጀብድ ተቆጥሮ እለት ከእለት የህዝብ ሀብት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በግለሰብ፤ በቡድን እየተመዘበራ ህብረተሰቡ እያየ ዝም ማለቱ ተግባሩ ለመቆጣጠር ችግር መሆኑን በስልጠናው ተገልጿል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከስልጠናው የግንዛቤ እንዳገኙ በመግለፅ ስልጠናው በቀጣይ ለመላው ሰራተኛ የሚሰጥበት ሁኔታ ቢፈጠር ከግንዛቤ እጥረትና በቸልተኝነት ከሚከሰቱ ብልሹ አሰራሮች ሊቀንሱ ይችላል በማለት ሀሳብ ሰጥተዋል።
ባለስልጣኑ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር በዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም በተከናወኑ ስራዎች እና በቀሪ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሄደ።

ሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም
* አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የበጀት ዓመቱን በዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም በተከናወኑ ስራዎች እና በቀሪ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂዷል።

ባለስልጣኑን በሶስተኛ ሩብ ዓመት የደረሰበት እቅድ አፈፃፀም ያቀረቡት የባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል አድማሱ ተክሌ እንዳሉት በ9ወራት ውስጥ በተለያየ መንገድ የተሰበሰበ ከ34 ሚሊየን ብር በላይ ወደ ፍይናንስ ገቢ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

አክለውም በቦታ 5840 ቦታዎች እንዲሁም በካሬ ከ10 ሚሊዮን ካሬ በላይ መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ ተደርገው በባለስልጣኑ እየተጠበቁ ይገኛሉ ብለዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ሰራተኞችም በቀሪው 3 ወራት ውስጥ ከእቅዳችን ለማሳካት እና ክፋተቶቻችንን ለመሙላት በትጋት ልንሰራ ይገባል ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል።

የመድረኩን ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፍሁን አሉላ በአጠቃላይ በአመራሩ እና ሰራተኛው ጥረት አሁን ላይ በተቋሙ ጥሩ አፈፃፀም መኖሩ ገልፀው ይህንንም አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል በማለት ከሰራተኛው ለቀረበላቸው ሀሳብና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የውይይት መድረኩን ተጠናቋል።

ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍2
ባለስልጣኑ “በህብረተሰቡ የላቀ ተሳትፎ የደንብ መተላለፎችን እንከላከላለን” በሚል መሪ ቃል የህዝብ ውይይት አካሄደ

18/08/2016ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እና የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት በ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ እና በደንብ ቁጥር 150/2015 የአፈፃፀም መመሪያ ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ አከናወነ።

የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ ከተማችን አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ፅዱ እንድትሆን ሌት ተቀን እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው ብለዋል።

አክለውም የ 2016 በጀት አመቱን ሲጀመር እቅዱን ለህዝብ በማስተቸት ወደ ስራ እንደገባ ገልፀው። ለባለስልጣኑ የጀርባ አጥንት የሆነውን የህብረተሰባችንን አስተያየት በመቀበል ስራዎችን ስንሰራ የቆየን ሲሆን በዛሬው ዕለትም በ9 ወራት ውስጥ ምን ተሰራ ምንስ ይቀረናል የሚለውን የምናይበት መድረክ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።


የባለስልጣኑን የሶስተኛ ሩብ ዓመትን የዕቅድ አፈፃፀም በእቅድ እና በጀት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ኮነሬል አድማሱ ተክሌ በበጀት ዓመቱ ከህብረተሰብ ጋር ተቀራርበን በመስራታችን ብዙ ለውጦች መምጣታቸውን ገልፀዋል።

ሌላው በደንብ ቁጥር 150/2015 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሰነድ ያቀረቡት የቅድመ መከላከል እና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ናቸው ።

በቀረቡት ሁለት ሰነዶች ላይ ሀሳብና አስተያየቶች ከህብረተሰቡ የተሰጡ ሲሆን ስራዎችን በጋራ መስራት ለውጤት እንደሚያደርስ እና ይህንን ለማስቀጠልም ተቀራርቦ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ መስራት ከጀመርን በኋላ ለተቋማችን ትልቅ ኃይል ሆናችኋል ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የተናገሩት የውይይት መድረኩን ሲመሩ የነበሩት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ናቸው ።

ሌላኛው መድረኩን ሲመሩ የነበሩት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፋፉ እንዳሉት በዛሬው ውይይታችን ያየናቸውን ነገሮች ለሁሉም ህብረተሰብ ማድረስ እንደሚገባ እና ለከተማዋ ልማት እንዲሁም ለተቋሙ ራዕይ እና ተልዕኮ እንቅፍት የሚሆኑ ህገወጦችን ከእናንተ ጋር በመሆን እንታገላለን ብለዋል። ለተነሱ ሀሳብ እና አስተያየት ምላሽ የሰጡ ሲሆን የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍3