የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የስምምነት ሰነድ ከተፈራረማቸው 23 ባለድርሻ ተቋማት ጋር በ9ወር እቅድ አፈፃፀም በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች የግምገማ መድረክ አካሄደ።

15/08/2016ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ ተቋማት በጋራ ሆኖ በተሰሩ ስራዎች ላይ የባለስልጣኑ የማዕከል እና የክፍለ ከተማ አመራሮች እንዲሁም የባለድርሻ ተቋማት አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በጌት ፍም ሆቴል የውይይት መድረክ አካሄደ።

የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፋፉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱን ገልፀው የስምምነት ሰነድ ከመፈራረም ባሻገር በጋራ የተሰሩ ስራዎችን መገምገም ለውጤት እንደሚያበቃ ገልፀዋል።

ምክትል ስራ አስኪያጁ አያይዘውም በዛሬው ዕለት በ9ወራት ውስጥ ምን ተሰራ የሚለውን እና በቀጣይ ምን ይቀረናል በሚለው ዙሪያ ውይይት በማድረግ በቀጣይ በበጀት አመቱ በቀሩት ወራት ውስጥ በመደጋገፋ ውጤት ያለው ስራ በመስራት ህዝብ እና መንግስት የጣለብንን ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም የተዘጋጀውን የውይይት ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀፀላ 9ኙ የደንብ መተላለፎችንም ሆነ ሌሎች ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በመስራታችን በጋራ ስራዎቻችንን በመገምገማችን አመርቂ ውጤት ማምጣት ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።

በሰነዱም በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተፈፀሙ ዋና ዋና ተግባራትና የነበሩ ውስንነቶች እና የተወሰዱ መፍትሄዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችና የተቋሙ ባለድርሻ አካላት የቅንጅት ስራዎችን በጋራ ማቀድ እና መገምገም ይበል የሚያሰኝ እና በቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በማጠቃለያንግግራቸው ባለድርሻ አካላት በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ወደ ስራ በመግባታችን በአዋጅ የተሰጠንን ኃላፊነታችንን ለመወጣት አስችሎናል በማለት 24ተኛ የባለድርሻ አካል አድርገን የያዝነው የሚዲያ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራታችን ጥሩ መሻሻሎች እና ለውጦችን ማየት ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ይህ መድረክ በቀሪ ወራት ምቹ ስራን እንድንሰራ እና ክፍተቶቻችንን እንድንሞላ ያደርገናል ሲሉ የገለፁት ወ/ሮ አበባ እሸቴ ናቸው።

ዘገባው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው።
1