"የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ከማህበረሠቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው" ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
ሚያዚያ 09/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት 9 ወራት በቅንጅት የተሰሩ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ቢሮዉ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማጠናከር የፀጥታ መዋቅሩን ከማህበረሠቡ ጋር በማቀናጀትና የሠላም ባለቤት እንዲሆን በማስቻል በፈጣን የመረጃ ቅብብሎሽ የፀረሰላም ሀይሎችን የሽብርተ
ኝነት እንቅስቃሴዎችን በማጨናገፍና በመቆጣጠር ህገ-ወጥ እና አዋኪ ድርጊቶችን በመከላከል እና ህጋዊ እርምጃ በመዉሠድ፣ በማስወሰድ ደረቅ ወንጀሎችን በመቀነስ በቅንጅት የተሳካ ስራ መስራት ችለናል ብለዋል፡፡
ሀላፊዋ አከለዉም ዘላቂ ሠላም በከተማችን እንዲሰፍንና ሌብነትና ብልሹ አሠራርን ከመዋጋት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የተደራጀው የሠላም ሠራዊቱን የሠላም ባለቤት በማድረግ የተሠራው ሥራ፣ውጤት ያመጣው በየደረጃው የሚገኘው አመራር ከባለሙያዉ ጋር በመቀናጀት መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም የተቋማቱን አቅም በአሰራር፣ በሰዉ ሃይልና በቴክኖሎጂ በማዘመን በተቀናጀ አግባብ እነዚህን ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡:
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸዉ የመሬት ወረራን በማስቆም እና የተወረሩ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ በማስገባት ህገወጥ ግንባታና የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ዉጤት ያስመዘገብነዉ በቅንጅት ስለሰራንና የአመራር ፑል በመጠቀም ወጥነት ያለዉ ግምገማ በመዋቅራችን ዘርግተን ስለሰራን ነዉ ብለዋል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎችም ተቋማቱ ስኬታማ ያደረጋቸዉ ስራዎች በተቀናጀ አግባብ ቀን ከሌት በመሰራቱ ስራዉ በአግባብ የተመራ በመሆኑ እና ከማእከል እስከ መንደር የሥራዉ ባለቤት በመሆን በቁርጠኝነት በመሳተፋቸዉ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይ የተቋማትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማሳደግ የጋራ አቋም በተያዘባቸዉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!

❤2👍2
ፕሬስ ሪሊዝ
ባለስልጣኑ ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በከተማዋ ጽዳት ዙሪያ የፓናል ውይይት ሊያካሄዱ ነው።
ሚያዚያ 09/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር "ጽዱና ምቹ አዲስ አበባን ለመፍጠር የተቋማት ቅንጅታዊ ስምሪት ያለው ፋይዳ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የቴሌቪዥን የዓር ሰዓት ላይ የፓናል ውይይት ሊካሄዱ መሆኑን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ጠቆሙ።
የአዲስ አበባ ከተማ እንደ ስሟ ውብና ፅዱ ለማድረግ ሁለቱም ተቋማት በከተማ አስተዳደሩ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በቅንጂት እየተወጡ እንደሚገኛና ከዚህ በላቀ መንገድ ስራዎችን ወደ ዘላቂ ውጤት ለማሻገር እንዲያስችል የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች፣የባለድርሻ ተቋማት ሀላፊዎች የሁለቱም ተቋማት ከፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የከተማዋ የጽዳት አምባሳደሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በጌት ፋም ሆቴል ለአንድ ሰዓት በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት የሚተላለፍ የፓናል ውይይት እንሚካሄድ አቶ የምስራች ገልፀዋል።
በዉይይቱም ተቋማቱ ስራዎችን በቅንጅት በመፈፀም ረገድ ያሉ ጥንካሬዎችና ተግዳሮቶች በመነጋገር የቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን እንደሚቀመጡ ይጠበቃል።

👍11
"አዲስ አበባን እንደ ስሟ ጽዱና ለነዋሮቿ ምቹ ለማድረግ ተቋማት ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል" የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጄንሲና ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በመተባበር “ጽዱና ምቹ አዲስ አበባ ለመፍጠር የተቋማት ቅንጅታዊ የስራ ስምሪት ያለው ፋይዳ” በሚል መሪ ቃል ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በመተባበር የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ አርቲስቶችና የከተማው የጽዳት አምባሳደሮች በተገኙበት የፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ጽዱና ለነዋሮቿ ምቹ ለማድረግ ተቋማትና ህብረተሰቡ አብሮ ተቀናጅቶና ተናቦ በመስራት የተጀመሩ ስራዎች በማጠናከር ከተማ አስተዳደሩ የሰጠንን ተልዕኮ ለማሳካት እንደሚረዳ ገልጸዋል።
የፓናል ውይይቱ አስፈላጊነት በተመለከተ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በበኩላቸው እንደ ህብረተሰብ አገልጋይነታችን የተቋማቶቹ ተግባርና ሃላፊነቶች ለህብረተሰቡ በማድረስና የከተማው ልሳን በመሆን መረጃን ተደራሽ ለማድረግ በቀጣይ አጠናክረው እንደሚሰሩ በመድረኩ ቃል ገብተዋል፡፡
በእለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ በበኩላቸው በሁለቱም ተቋማት አዲስ አበባን ውብና ጽዱ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እንደተሰራ በመግለጽ ሁለቱም ተቋሞች በቀጣይ በመነጋገር ተቀራርቦ በመስራት የሚገጥሟቸው ችግሮች በመፍታት ከህብረተሰቡ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በጋር መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ለፓናል ውይይቱ መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በሁለቱ ተቋማት በጋራ የተሰሩ ውጤታማ ስራዎች በጥንካሬ፣ በክፍተትና ለወደፊቱ መስተካከል ያለባቸው በሚል በዝርዝር አቅርበው ሁለቱ ተቋማት ከመወቃቀስ ይልቅ ተግባብቶና ተቀናጅቶ አብሮ በመስራት ተግዳሮቶችን መፍታት ለተሻለ የከተማችን ጽዳት ትልቅ ግብ እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች ሁለቱም ተቋማት በቀጣይ ከንግግር ባለፈ ስራዎቻቸው በተግባር ማሳየት እንዳለባቸውና ከመቅጣት ይልቅ ደጋግመው ለህብረተሰቡ በማስተማርና ግንዛቤ በማስረጽ የባህሪ ለውጥ እንዲመጣ መደረግ አለበት በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በተነሱ ሀሳቦች ላይ የተቋማቶች የበላይ አመራሮች ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ ተቋማቶቹ ተናቦና ተቀናጅቶ በመስራት በህዝብና በከተማ አስተዳደሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣትና አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ጽዱ ለማድረግ በቀጣይ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ለመስራት በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

👍2❤1