የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.86K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በፀጥታ እና መረጃ ዘርፍ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና አጠናቀቀ።

መጋቢት 29/ 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ለአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል አስከ ወረዳ ላሉ የጸጥታና መረጃ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ለተከታታይ 7 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና የማጠቃለያ መርሐ ግብርና የምርቃት ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ሰንዳፋ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል ።

በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፣የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ፣የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ-አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ፣የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::

በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀ/ል መስፍን አበበ እንደተናገሩት ሰልጣኞች ከሀገርና ከተቋም የተጣለብንን ተልዕኮ ለማሳካት በአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የምናገኘውን ዕውቀት በመጠቀም ለህዝብና ለሀገር ጥሩ መልካም አገልግሎት በመስጠት ለሌሎችም አርአያ መሆን ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ እንደተናገሩት ቢሮው በከተማው ውስጥ የሚታየውን የጸጥታ ስጋቶች ፣ የጽንፍና የሽብር እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የጸጥታ አዝማሚያዎችን በተገቢው በመተንተን የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም በጸጥታ መረጃ ላይ የተመሰረተ ወንጀልና የመሳሰሉትን ህገወጥ ተግባራት ለመከላከልና በከተማው የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ ቢሮው ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ለ 7 ቀን ሙያዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት መቻሉን ገልጸዋል ።

የቢሮ ሀላፊዋ አክለውም ለሰልጣኞች የወሰዳችሁትን ስልጠና እንደ ተጨማሪ አቅም በመጠቀም በከተሞችን አዲስ አበባ ልትደርስበት ያስቀመጠችውን ለማድረግ፤በህዝብ ተሳትፎ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ ፣ለስራና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና የማየት ራዕይ ከዳር ለማድረስ የሚጠበቅባችሁን ሃላፊነት በቁርጠኝነት እንድትወጡ አደራ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል ።

ስልጠናው አስመልክቶ ሪፖርት ያቀረቡት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ም/ፕሬዚዳንት ም/ኮሚሽነር ዳንኤል ብርሃኑ እንደገለፁት ተቋማቸውን ለማገልገል ወቅቱን የጠበቀ ውጤት ለማምጣት እንዲችሉ በከፍተኛ ትኩረት ስልጠናው መሰጠቱን ገልጸዋል ።

ስልጠናውን ወስደው ያጠናቀቁ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና መረጃ አመራሮችና ባለሙያዎች ብዛት 249 ሲሆኑ በሰባት ቀናት ቆይታቸው የጸጥታ መረጃ ባለሙያዎች ስነምግባርና የሀገር ወዳድነት ትምህርት ፣ የወንጀል ስፍራ መረጃ አሰባሰብና አደረጃጀት ፣ የፈንጂና ተቀጣጣይ ነገሮች መለየት እና የፍተሻ ስልጠና ፣ የመረጃ አሰባሰብ የማደራጀትና የመተንተን ስልት፣ የአደጋ ስጋት ተጋላጭነት መከላከልና መቆጣጠር ፣የመሰረታዊ የወንጀል መከላከልና የአካል ደህንነት ፣ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ከጸጥታ መረጃ ስራ አንጻር ፣ የክክትልና መረጃ ስልጠና እንደወሰዱ ተገልጿል ።

በመጨረሻም ለስልጠናው መሳካት ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ አመራሮች፣ ለአሰልጣኞች አና ለአስተባባሪዎች እውቅና እና ሽልማትና ተበርክቶላቸዋል ።

ዘገባው ፦ የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
የኢድ አልፈጥር በአል መጪው ረቡዕ ሚያዚያ 2 /2016 ዓ.ም እንደሚከበር ተገለጸ

መጋቢት 30/2016 ዓ.ም 

ጨረቃ በዛሬው እለት በሳውዲአረቢያ ባለመታየቷ ነው በአሉ መጪው ረቡዕ ሚያዚያ 2 /2016 ዓ.ም የሚከበር ይሆናል።
👍31
የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅደመ መከላከል ዘርፍ ስልጠናዊ ግምገማ መድረክ አካሄደ

ሚያዝያ/1/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከልና ዘርፍ በ2016 በጀት ዓመት ለክፍለ ከተሞች ባደረገው ድጋፍና ክትትል መሰረት የነበሩ ጥንካሬዎች እና ክፋተቶች በመጥቀስ ከክፍለ ከተማ የተወጣጡ የስራ አስተባባሪዎችና የቅድመ መከላከል ቡድን መሪዎች በተገኙበት ስልጠናዊ ግምገማ መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ምክትል ስራ አሰኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሼቴ የመድረኩ ዓላማ በክፍለ ከተሞች የተካሄደው የድጋፍና ክትትል ላይ የታየውን ክፍተት በማሳየት ፤ በቀጣይ እንዳይደገሙና በጎ ፈቃደኞች ለባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ለመከላከልና ግንዛቤ ለማስጨበጥ አሰፈላጊነታቸው በማመላከት ከእነሱ የሚጠበቅ ተግባራትና ሀላፊነት በአግባቡ እዲወጡ ለማድረግ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ድጋፍና ክትትል ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል፤ እንዲሁም ለስራችን እገዛ አለው ሆኖም ከተማው ለድጋፍ ሲመጣ ቅድሚያ አቅጣጫ ቢሰጠን ይገባል፤የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪዎች ለተቋሙ የደንብ መተላለፍና ግንዛቤ ማስጨበጥ ቀላል የማይባል አስተዋጾኦ ያበረክታሉ ስለዘህ ለእገዛቸው እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
👍1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የዒድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

ሚያዚያ 01/08/2016 ዓ.ም

ለመላው የዕስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ተኛ የዒድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

የኢድ-አልፈጥር በዓሉ የሰላም ፣የጤና ፣የደስታ፣የፍቅር እና የመረዳዳት በዓል እንደሆንልን እየተመኘሁ ህዝበ ሙስሊሙ በጾም ወቅት በአብሮነት፣በመተሳሰብና ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ በማጋራት ያለውን በማካፈል ጾሙን ሲያስፈጥር የነበረውን ሠናይ ተግባርና መልካም እሴቶችን በበዓሉ እለት እና ከበዓል በኋላ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ።

ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ መተላለፍና ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረት ላይ ሁሉም ዜጋ በንቃት በመሳተፍ አዲስ አበባ ከተማችንን የደንብ መተላለፍ የማይስተዋልባት፤ ለነዋሪዎቿና እንግዶቿ ምቹ እንድትሆን እንድንረባረብ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

በራሴ እና በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ስም መልካም በዓል እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ።
                       
                        ዒድ ሙባረክ!

                ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ
👍10
የውይይት መድረክ ቀን መቀየሩን ስለማሳወቅ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለሀሙስ ሚያዚያ 03/2016 ዓ.ም ለማካሄድ ተይዞ የነበረው  መድረክ በአስቸኳይ ስራ ምክኒያት በተያዘው ቦታ እና ሰዓት ወደ አርብ ሚያዚያ 04/2016 ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር  እናሳውቃለን።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን
👍10