የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.86K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸሙ በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀመጠ

ሚያዝያ 4/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጸጸም የግምገማ መድረክ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የ11ዱም ክፍለ ከተማና የ119 የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት በጌት ፋም ሆቴል የስብሰባ አደራሽ አካሂዷል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ-ስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመድረክ መክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት በ2016 በጀት ዓመት 9 ወራት በርካታ ስራዎች በስኬት የተፈተመበጽ ሲሆን በተለይ ህገወጥ የመሬት ወረራ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት መቻላችን እና በከተማዋ የተወረረ መሬት አለመኖሩን የተቋሙ ትልቅ ስኬት መሆኑ ገልጸው አሁን ላይ የተጠናከረው የቅድመ መከላከል ተግባሩ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ዋና ስራ-ስኪያጁ አያይዘው በቀጣይ ከአንደኛ ዙር አሰከ አራተኛ ዙር ያሉ የፓራ ሚሊተሪ ሰራተኞች አቅማቸው ለመገንባት በተለያዩ ዙሮች ስልጠና እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል፡፡

በእለቱ የቀረበው የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የባለስልጣኑ የእቅድ እና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል አድማሱ ተክሌ ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ ባለስልጣኑ ከተቋም ግንባታ አንጻር ከታቀደው በላይ ስራዎች የተሰሩ እንደሆነና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችም በስፋት በመሳተፍ ተቋሙ ለኅዝብ አለኝታነቱን ውጤታማ ስራ በመስራት ማሳየት እንደተቻለ በሪፖርቱ ተገልጸዋል፡፡

ባለስልጣኑ አሁን ላይ ያለው የሰው ሀይል እጥረት ለመቅረፍና በሌሊት የሚፈጸሙ ህገወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ከፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰራ መሆኑና በቀጣይ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በማካሄድና ችግሮችን ለመለየት መታቀዱን ተመላክቷል፡፡

በእለቱ ከመድረክ ተሳታፊዎች በርካታ ሃሳቦችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የባለስልጣኑ ከፍተኛ ሃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
"የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ከማህበረሠቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው" ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

ሚያዚያ 09/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት 9 ወራት በቅንጅት የተሰሩ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ቢሮዉ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማጠናከር የፀጥታ መዋቅሩን ከማህበረሠቡ ጋር በማቀናጀትና የሠላም ባለቤት እንዲሆን በማስቻል በፈጣን የመረጃ ቅብብሎሽ የፀረሰላም ሀይሎችን የሽብርተ
ኝነት እንቅስቃሴዎችን በማጨናገፍና በመቆጣጠር ህገ-ወጥ እና አዋኪ ድርጊቶችን በመከላከል እና ህጋዊ እርምጃ በመዉሠድ፣ በማስወሰድ ደረቅ ወንጀሎችን በመቀነስ በቅንጅት የተሳካ ስራ መስራት ችለናል ብለዋል፡፡

ሀላፊዋ አከለዉም ዘላቂ ሠላም በከተማችን እንዲሰፍንና ሌብነትና ብልሹ አሠራርን ከመዋጋት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የተደራጀው የሠላም ሠራዊቱን የሠላም ባለቤት በማድረግ የተሠራው ሥራ፣ውጤት ያመጣው በየደረጃው የሚገኘው አመራር ከባለሙያዉ ጋር በመቀናጀት መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም የተቋማቱን አቅም በአሰራር፣ በሰዉ ሃይልና በቴክኖሎጂ በማዘመን በተቀናጀ አግባብ እነዚህን ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡:

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸዉ የመሬት ወረራን በማስቆም እና የተወረሩ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ በማስገባት ህገወጥ ግንባታና የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ዉጤት ያስመዘገብነዉ በቅንጅት ስለሰራንና የአመራር ፑል በመጠቀም ወጥነት ያለዉ ግምገማ በመዋቅራችን ዘርግተን ስለሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

የዉይይቱ ተሳታፊዎችም ተቋማቱ ስኬታማ ያደረጋቸዉ ስራዎች በተቀናጀ አግባብ ቀን ከሌት በመሰራቱ ስራዉ በአግባብ የተመራ በመሆኑ እና ከማእከል እስከ መንደር የሥራዉ ባለቤት በመሆን በቁርጠኝነት በመሳተፋቸዉ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይ የተቋማትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማሳደግ የጋራ አቋም በተያዘባቸዉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
2👍2
ፕሬስ ሪሊዝ

ባለስልጣኑ ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በከተማዋ ጽዳት ዙሪያ የፓናል ውይይት ሊያካሄዱ ነው።

ሚያዚያ 09/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር "ጽዱና ምቹ አዲስ አበባን ለመፍጠር የተቋማት ቅንጅታዊ ስምሪት ያለው ፋይዳ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የቴሌቪዥን የዓር ሰዓት ላይ የፓናል ውይይት ሊካሄዱ መሆኑን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ጠቆሙ።

የአዲስ አበባ ከተማ እንደ ስሟ ውብና ፅዱ ለማድረግ ሁለቱም ተቋማት በከተማ አስተዳደሩ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በቅንጂት እየተወጡ እንደሚገኛና ከዚህ በላቀ መንገድ ስራዎችን ወደ ዘላቂ ውጤት ለማሻገር እንዲያስችል የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች፣የባለድርሻ ተቋማት ሀላፊዎች የሁለቱም ተቋማት ከፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የከተማዋ የጽዳት አምባሳደሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በጌት ፋም ሆቴል ለአንድ ሰዓት በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት የሚተላለፍ የፓናል ውይይት እንሚካሄድ አቶ የምስራች ገልፀዋል።

በዉይይቱም ተቋማቱ ስራዎችን በቅንጅት በመፈፀም ረገድ ያሉ ጥንካሬዎችና ተግዳሮቶች በመነጋገር የቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን እንደሚቀመጡ ይጠበቃል።
👍11