የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ዛሬ ማለዳ የከተማችን ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ለውጥ 6ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ድጋፋቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል።

ለውጡ ሀገራችንን ከፍ ባደረጉ ታላላቅ ስራዎች እና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ከፍ ብሎ አንድነት የደመቀበት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምረን ያጠናቀቅንበት፣ የቱሪዝም መስህቦች እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ የጀመርናቸው ለሰው ልጅ ቅድሚያ በሰጠው ሰው ተኮር ስራዎቻችን የበርካቶች የኑሮ ሸክም ቀልሎ እምባቸው ታብሶ ተስፋቸው የለመለመበት ነው።
በቀጣይም መዲናችንን የብልጽግና ተምሳሌት፣ እንደ ስሟ ውብ እና ለኑሮ ምቹ በማድረግ በሁሉም ዘርፍ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል የማድረግ ጥረታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ሁሌም ድጋፋቸው ላልተለየን የከተማችን ነዋሪዎች አክብሮታችን ከፍ ያለ ነው፤ እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በፀጥታ እና መረጃ ዘርፍ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና አጠናቀቀ።

መጋቢት 29/ 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ለአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል አስከ ወረዳ ላሉ የጸጥታና መረጃ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ለተከታታይ 7 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና የማጠቃለያ መርሐ ግብርና የምርቃት ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ሰንዳፋ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል ።

በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፣የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ፣የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ-አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ፣የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::

በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀ/ል መስፍን አበበ እንደተናገሩት ሰልጣኞች ከሀገርና ከተቋም የተጣለብንን ተልዕኮ ለማሳካት በአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የምናገኘውን ዕውቀት በመጠቀም ለህዝብና ለሀገር ጥሩ መልካም አገልግሎት በመስጠት ለሌሎችም አርአያ መሆን ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ እንደተናገሩት ቢሮው በከተማው ውስጥ የሚታየውን የጸጥታ ስጋቶች ፣ የጽንፍና የሽብር እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የጸጥታ አዝማሚያዎችን በተገቢው በመተንተን የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም በጸጥታ መረጃ ላይ የተመሰረተ ወንጀልና የመሳሰሉትን ህገወጥ ተግባራት ለመከላከልና በከተማው የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ ቢሮው ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ለ 7 ቀን ሙያዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት መቻሉን ገልጸዋል ።

የቢሮ ሀላፊዋ አክለውም ለሰልጣኞች የወሰዳችሁትን ስልጠና እንደ ተጨማሪ አቅም በመጠቀም በከተሞችን አዲስ አበባ ልትደርስበት ያስቀመጠችውን ለማድረግ፤በህዝብ ተሳትፎ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ ፣ለስራና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና የማየት ራዕይ ከዳር ለማድረስ የሚጠበቅባችሁን ሃላፊነት በቁርጠኝነት እንድትወጡ አደራ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል ።

ስልጠናው አስመልክቶ ሪፖርት ያቀረቡት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ም/ፕሬዚዳንት ም/ኮሚሽነር ዳንኤል ብርሃኑ እንደገለፁት ተቋማቸውን ለማገልገል ወቅቱን የጠበቀ ውጤት ለማምጣት እንዲችሉ በከፍተኛ ትኩረት ስልጠናው መሰጠቱን ገልጸዋል ።

ስልጠናውን ወስደው ያጠናቀቁ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና መረጃ አመራሮችና ባለሙያዎች ብዛት 249 ሲሆኑ በሰባት ቀናት ቆይታቸው የጸጥታ መረጃ ባለሙያዎች ስነምግባርና የሀገር ወዳድነት ትምህርት ፣ የወንጀል ስፍራ መረጃ አሰባሰብና አደረጃጀት ፣ የፈንጂና ተቀጣጣይ ነገሮች መለየት እና የፍተሻ ስልጠና ፣ የመረጃ አሰባሰብ የማደራጀትና የመተንተን ስልት፣ የአደጋ ስጋት ተጋላጭነት መከላከልና መቆጣጠር ፣የመሰረታዊ የወንጀል መከላከልና የአካል ደህንነት ፣ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ከጸጥታ መረጃ ስራ አንጻር ፣ የክክትልና መረጃ ስልጠና እንደወሰዱ ተገልጿል ።

በመጨረሻም ለስልጠናው መሳካት ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ አመራሮች፣ ለአሰልጣኞች አና ለአስተባባሪዎች እውቅና እና ሽልማትና ተበርክቶላቸዋል ።

ዘገባው ፦ የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።