የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ኘረስ ሪሊዝ

ባለስልጣኑ በ2016 ዓ.ም በመጀመሪያው ስድስት ወራት የላቀ የእቅድ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አካላት ዕውቅና ሊሰጥ ነው።

መጋቢት 20/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2016 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የላቀ እቅድ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ለማዕከል ዳይሬክቶሬቶችና ቡድኖች እንዲሁም ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች እውቅና በመስጠት የማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ሊያበረክት መሆኑ ተገልጿል።

እውቅናው በነገው እለት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በጌት ፋም ሆቴል የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላው እንግዶች በተገኙበት በእቅዳቸው መሠረት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት እውቅናው እንደሚሰጥ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ጠቁመዋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍6
ባለስልጣኑ የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም የእውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ ።

መጋቢት 21/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2016 ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት የእውቅና ሽልማት ፕሮግራም በጌትፋም ሆቴል አካሄደ ።

በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ፣ የከተማው ሰላምና ፀጥታና የባለስልጣኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ፣ የክ/ከተማና የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ አርቲስቶች ፣ የማዕከሉ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ በአዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃትና በጥራት እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ለስራዎቻችን መሳካት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት አካላት እነማን ናቸው ሚለውን ምዘና በማካሄድ በመለየት በዛሬው ዕለት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ እውቅናና ሽልማት በመስጠት ማበረታት ለቀጣይ ስራችንን መሳካት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውንን መሬት በልዩ ትኩረት በመጠበቅ በተያዘው በጀት ዓመት ምንም አይነት ወረራ እንዳየፈጸም ማድረግ ችሏል ።
የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በማጠናከር ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራት በከተማችን የሚታዪ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል በመቆጣጠርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እርምጃ በመውሰድ ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት እንደ ስሟ አዲስና ውብ እንድትሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ዋና ሰራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ 2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም የምዘና ዉጤት ትንተና ማጠቃለያ ሰነድ በባለስልጣኑ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ አንደተናገሩት ደንብ ማስከበር ደንብ ጥሰትን ከመከላከል ጎን ለጎን ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ ከማስጠበቅ አንጻር እየሰራ ያለው ስራ ሊበረታታ እእንደሚገባ በመግለፅ ህብረተሰቡ በቀጣይ የደንብ ማስከበር ስራን በመገንዘብ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ከጎኑ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ፣የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፣ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል
በ2016 ግማሽ ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ክ/ከተማና ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ፣ የማዕከል ዳይሬክቶሬትና ቡድን መሪዎች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።
በዚህም መሰረት ከ 11 ክ/ከተማ ከ1ኛ አስከ 3ኛ የወጡት
1ኛ ጉለሌ ክፍለ ከተማ
2ኛ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
3ኛ ልደታ ክፍለ ከተማ የእውቅና ሽልማትና ላፕቶፕ ተበርክቶላቸዋል

ከ119 ወረዳዎች ከ1ኛ አስከ 3ኛ የወጡት
1ኛ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 11
2ኛ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7
3ኛ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 እና ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የኮምፒውተር ሽልማትና ተበርክቶላቸዋል።

ከማዕከል ዳይሬክቶሬት ከ1ኛ አስከ 3ኛ የወጡት
1ኛ የደንብ መተላለፍ ክትትልና ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት
2ኛ የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት
3ኛ ደንብ መተላለፍ መከላከል ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት

ከማዕከል ቡድን ከ1ኛ አስከ 3ኛ የወጡት
1ኛየንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን
2ኛ የስልጠና ቡድን
3ኛ የሲቪል የሰው ሀይል ቡድን

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን
👍6
ከእድር ምክር ቤቶች ጋር በጋራ መስራት የደንብ መተላለፍን በመከላከል ረገድ ሚናው የላቀ መሆኑ ተገለፀ።

መጋቢት 23/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ለሚገኙ እድር ምክር ቤት አመራሮች በደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ ግንዛቤ ፈጠረ።

የደንብ መተላለፍን በዘላቂነት ለመከላከል በከተማዋ ውስጥ ከሚገኝ አጠቃላይ ማህበረሰብ ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባና በተለይ የማህበረሰቡ እሴትና መስተጋብር አውዎንታዊ በሆነ መልኩ በሚገነባበት እድሮች ጋር ተቋሙ ሲሰራ እንደቆየና በቀጣም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዘርፉ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠርካለም ጌታሁን ገልፀዋል።

አክለውም በደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ግንዛቤ አስጨብጠዋል።

በመድረኩ በየቀጠናው ከሚገኙ የባለስልጣኑ ቅድመ መከላከልና የግንዛቤ ማስጨበጥ ኦፊሰሮች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ለህብረተሰቡ ግንዛቤን በማስጨበጥ በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ መተላለፍ አስቀድሞ በመከላከል ምቹ አዲስ አበባን በጋራ መገንባት እንደሚገባ ወ/ሮ ሠርካለም ተናግረዋ።

የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን አስቀድሞ ለመከላከል በዘርፉ በርካታ የቅድመ መከላከል ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውሰው፤ የዕድር አመራሮች በህብረተሰቡ ውስጥ ያላችሁን ተደማጭነት በመጠቀም ከተቋሙ ጎን ተሰልፋችሁ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ እየቀረፍን ውጤታማ ስራዎችን እናከናውናለን በማለት ማንኛውንም ጥቆማዎች በተቋሙ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ላይ እንዲጠቁሙ አስታውሰዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ከእኛ ጋር በይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት እና አዲሱ ደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ ግንዛቤ መፈጠሩ እጅግ የሚበረታታ ነው፤ እኛም በማህበረሰባችን ዘንድ ያለንን ተደማጭነት በመጠቀም የሚጠበቅብንን ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለፅ አልፎ አልፎ የስነ-ምግባር ጉድለት የሚስተዋልባቸው ኦፊሰሮች ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ጠቁመዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ነው።
👍21