የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለፉ ሴቶች ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
መጋቢት 5/2016 ዓ.ም
#አዲስአበባ
የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለፉ ሴቶች ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማዕከሉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የሴቶች ፆታዊ እኩልነት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሙሉ በሙሉ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ሴቶችን ማብቃት እና የእኩልነት መብታቸውን ማክበር እና ማስከበር እያረጋገጥን መሔድ እንደሚገባን በምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ውስጥ የትኩረት አቅጣጫችን መሆኑን የምናሳይበት አንዱ ሥራ ነው ብለዋል።
ዛሬ ይህንን ማዕከል መርቀን ስንከፍት አዲስ የተገነባ ሕንፃን ሥራ ከማስጀመር ባለፈ የተሻለ ነገን፣ ብሩህ ተስፋን፣ ፅናትን እና ሰፊ ሠርቶ የመለወጥ ዕድልን በዘላዊ ፅኑ መሠረት ላይ እየተከልን መሆኑን በማነን ነው ሲሉም አክለዋል።
በርካታ ሴቶች በሚደርስባቸው ፆታዊ አድልኦ፣ ተፅዕኖ እና ጥቃት ለተለያዩ ማኅበራዊ ጫናዎች እና በደሎች ከመጋለጥ በላይ በማኅበረሰባቸው እና ለሀገራቸው ዕድገት አቅማቸው የሚፈቅደውን አስተዋፀኦ ማድረግ እንዳይችሉ ከፍተኛ ውስንነት ውስጥ እንዲያልፉ እንደሚያደርጋቸው አንሥተዋል።
በሀገራችን ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ለሴቶች ዕድልን ለማስፋት፣ ለማብቃት፣ እኩል ተጠቃሚ እና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን እና አበራታች ውጤቶችም መታየታቸውን ጠቁመዋል።
ዛሬም በርከታ እህቶቻችን እና ልጆቻችን ላይ በሚደርሰው የተወሳሰበ ፆታዊ አድልኦ የኢኮኖሚ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ዕድል ጠባብ መሆን ተጨምሮበት ለኢኮኖሚ ጥገኝነት፣ ለአካላዊ እና ፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው እንደቀጠለ ነው ብለዋል።
በመሆኑንም ይህ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ሁሉን ችግር የሚፈታ ባይሆንም ለጎዳና ሕይወት እና ለወሲብ ጥቃት እንዲሁም ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ የሆኑ እህቶቻችን አማራጭ የገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ መሰማራት እንዲችሉ የሚያበቃቸውን እና ብቁ የሚያደርጋቸውን የክህሎት፣ የሥነ-ምግባር፣ የሥራ ባህል፣ የሥራ ስምሪት ጭምር እንዲፈጠርላቸው በማድረግ ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ እንደሚያስችል እምነታቸውን መግለፃቸው AMN ዘግቧል።
#Ethiopia
#addisababa

🙏4👍2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በግንባታ እና በምርቃት ሂደት ለተሳተፉ የተቋሙ አመራሮች እና ኦፊሰሮች ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት።
መጋቢት 05/2016 ዓ.ም
#አዲስአበባ
የተከበራቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሴቶች የተሀድሶ እና የልህቀት ማዕከል ጥራቱን በጠበቀና ባማ መልኩ በጣም በሚገርም ፍጥነት በ11ወር ተገንብቶ ዛሬ ተመርቋል ።
ማዕከሉ የተሻለ ነገን፣ ብሩህ ተስፋ የሚሰጥና ለሴቶች እኩል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው፤ ይህም ለበርካታ ሴቶች ከኢኮኖሚ ጥገኝነትና የሚያወጣ ሲሆን ሀገራችን በለውጥ አመራችዋ በስኬት የታጀበች መሆኗ የሚያሳይ ነው።
ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት በተለይ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ሀላፊ አቶ ደጀኔ ነገሮ እና የክ/ከተማው ከሚያስተባብራቸው ኦፊሰሮችን በመሆን ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ አስከ ተመረቀበት ቀን ድረስ ዝናብ እና ፀሀይ ሳይበግራቹ ላበረከታችሁት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በተቋሙ ስም ከልብ አመሠግናለሁ ።
በምረቃ ዋዜማው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በአቶ ዳኜ ሂርጳሳ የተመራው ጀግኖቹ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች በተጠሩበት ፈጥነው ቦታው በመድረስ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት በመፈፀማችሁ ከልብ አመሠግናለሁ።
በአጠቃላይ ከሁሉም ክፋለ ከተሞች የተወጣጡ እና በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በወ/ሮ መአዛ ተክሉ የተመራው የሴት ኦፊሰሮች በማዕከሉ አዳርም ጭምር በመስራት ብርዱን ሳይበግራቸው ተልዕኮአቸውን በፍጹም ኢትዮጵያዊ ወኔ በመፈጸማቸው ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል ።
በልማት ኮሪደር ላይ የምትገኙም አመራሮቻችን እና ኦፊሰሮች ጥሩ ሥራ አየሠራችሁ በመሆኑ እያመሰገንኩ በርቱ እያልኩኝ በሥራችን የሚያጋጥመን ፈተና ካለ ተደጋግፈን እንሻገራለን።
ከተባበርን፣ከተደማመጥን እና ከተደመርን የሚሠጠንን ተልዕኮ በመወጣት ሀገር እናሻግራለን የሚያግደን ነገር አይኖርም ።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር
ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ

👍9🙏4
ባለስልጣኑ የቀጣይ ዘጠና ቀናት እቅዱን ለማሳካት ያለመ ውይይት አደረገ ።
መጋቢት 11/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የባለስልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ ለማሳካት በተዘጋጀው እቅድ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ከማዕከል ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ጋር የባለስልጣኑ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት በጌት ፋም ሆቴል ውይይት አካሄደ ።
መድረኩን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አንደገለፁት ተቋሙ የ90 ቀናት እቅዱን በየደረጃው ለክ/ከተማ እና ለወረዳ በማውረድ ለሰራዎቹን ትኩረት በመስጠት ክትትልና ድጋፍ በማድረግ አፈጻጸሙን የሚገመግም ይሆናል ብለዋል።
የተቋሙ የ90 ቀን ዕቅድ ለማሳካት የተዘጋጀው አጋዥ እቅድ በባለስልጣኑ የለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል አድማሱ ተክሌ የቀረበ ሲሆን የበጀት ዓመቱ መሪ እቅድ በተለያዩ ምክንያት ሳይፈጸሙ የቀሩ ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ከተቋሙ ሁለቱ አላማ ፈጻሚ ዘርፎች እና በድጋፍ ሰጪ ዳሬክተሮች በኩል በመቀናጀት የተጀመሩ ሰራዎች አጠናክሮ በመቀጠል በቀጣይ 90 ቀናት ማጠናቀቅ አንደሚገባ ተገልጿል ።
በቀጣይም ለነባር የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የስልጠና ቡድን መሪ አቶ አዳነ ለገሰ የቀረበ ሲሆን ባለስልጣኑ በክ/ከተማ እና በወረዳ የሚገኙ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለማሰልጠን አቅዶ በቀጣይነት ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ከመድረኩ ተገልጿል ።
በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፣ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ እና ም/ሰራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ አሸቴ በኩል ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት ዋና ሰራ አስኪያጁ የቀጣይ የስራ የትኩረት አቅጣጫ አስቀመጠው ውይይቱ ተጠናቋል ።
ዘገበው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!

👍3👏1
ባለስልጣኑ በተግባቦት ፣ በመረጃ አያያዝ እና የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም በተመለከተ ስልጠና ሰጠ ።
መጋቢት 12/ 2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤቶች በኮሙኒኬሽን እና ሶሻል ሚዲያ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች በተግባቦት ፣በመረጃ አያያዝ እና በሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የሚዲያ አግባቦችን በመጠቀም ላይ ይገኛል ይህንንም ስራ በጋራ ለማሳለጥ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ የመረጃ ቅብብሎሹን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
ሀላፊው አያይዘው የተቋሙን ገጽታ በመገንባት ለደንብ ማስከበር ስራ ህብረተሰቡ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረው እና ህገ-ወጥነትን የሚኮንን ዜጋን ለማፍራት ተግባቦት እና ሚዲያ ሚናው ከፍተኛ ስለሆነ ስልጠናው እንደሚያግዝ ገልፀው በቀጣይ የተሰጠውን ስልጠና ተግባራዊ በማድረግ ከሰልጣኞች እና ሁሉም የተቋሙ ባለሙያዎች በተቋሙ ገጽታ ግንባታ ስራው የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል ።
በተግባቦት፣በመረጃ አያያዝ እና የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የተዘጋጀው ስልጠና በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ የምስራች ግርማ የተቋሙን ተግባራት ማዕከል ባደረገ መልኩ ሰጥተዋል።
የስልጠናው ዓላማ በተቋሙ የሚሰሩ ስራዎችን ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ ፣ሶሻል ሚድያ በመጠቀም የተቋሙ የመረጃ ልውውጥ ተደራሽ ለማድረግና ተቋሙ በየጊዜው የሚከፈትበትን የሶሻል ሚድያ ስም ማጥፋት ዘመቻ ሰራተኛው ትግል በማድረግ ትክክለኛውና የተደራጀ መረጃ ለህብረተሰቡ እንዲሰጥ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል ።
የሚዲያ አካላትን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው የተቋምና የሀገር ገጽታ ከመገንባት ባለፈ ለሀገራችን ሰላም ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን ያለአግባብ ከተጠቀምንበት ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጣ መሆኑን በመገንዘብ ማህበራዊ ሚዲያን ለመልካም ተግባርና ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምበት እንደሚገባ በስልጠናው ተገልጿል።
በመጨረሻም ከሰልጣኞች ጋር በቀጣይ በጋራ በተቀናጀና በተናበበ ሁኔታ ለመስራት ውይይት በማድረግ ከሰልጣኞች ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምሰራች ግርማ እና የሬ/ቴ/ህ/ዝግጅት ቡድን መሪ በአቶ ሄኖክ ታደሰ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል ።

👍2