የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
504 ዩኒት ደም 3ሰዓት ባልሞላ ጊዜ መለገሱን ተገለፀ

ባስልጣኑ ''ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት እንታደግ'' በሚል መሪ ቃል ባደረገው የደም ልገሳ መርሀ-ግብር ከ1100 በላይ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ አመራሮቹና ሰራተኞቹ በማሳተፍ ከ504 ዩኒት ደም መለገሱን ብሄራዊ ደም ባንክ ገለፀ።

የደም ልገሳው እጅግ ውጤታማና የተቀናጀ በመሆኑ ስራው መሳካቱ የተገለፀ ሲሆን ለዚህም የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች ላደረጉት መልካም ተግባር በብሄራዊ ደም ባንክ ተመስግነዋል።

"ደም መስጠት ህይወት መስጠት ነው"

መረጃው፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍148
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብ ተካሄደ።

                 14- 11- 2017 ዓ.ም
                  አዲስ አበባ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በእውቀት ሽግግሩ መርሀ ግብር እለቱን በስኬት በማለት ካለቸው ልምድና ተሞክሮ ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የክትትል ቁጥጥር እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ባለሙያ አቶ በሀይሉ አበራ የፓራ ሚሊቴሪ ህይወት ላይ ያጠነጠነ ሰነድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።

ወታደር ማለት ከብሔር፣ ከሀይማኖት፣ ከዘር እና ከጎሰኝነት አስተሳብ የፀዳ ኢትዮጵያዊነትን ተላብሶ ለሀገር ሉአላዊነት ክብር መስዋእት መሆን ነው ያሉት አቅራቢው ክብር ሰው በመሆን ብቻ የሚሰጥ መሆኑን በወታደራዊ ማስልጠኛ  ቆይታ አይቻለሁ።

ለኔ እዚህ ደራጃ ለመድረስ የቤተሰቦቼ ጥብቅ ክትትልና የሞራል ድጋፍ እንዲሁም በወታደራዊ ስልጠና በፓራ ሚሊተሪ የስራ ቆይታየ ከቅርብ ሀላፊዎቼ ብሎም የስራ ባልደረቦቼ ያገኘሁት ልምድና እውቀት ነው በማለት የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብሩ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።

በተጨማሪም በህይወቴ ትልቅ ችግርን በትንሽ ተስፋ ማለፍ እንደሚቻል አይቻለሁ ስለዚህ ችግሮችን ተቋቁሞ ተስፋን በመሰነቅ ነገን አሻግሮ ማየት ያስፈልጋል በማለት ገልፀዋል።

በመጨረሻም ከወታደራዊ ማሰልጠኛ ጀምሮ በስራ ቆይታቸው ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ በሰፊው በማቅረብ ዝግጅታቸውን ቋጭተዋል።

ዘጋባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
6
እንኳን ደስ አላችሁ!!! እንኳን ደስ አለን!!!
ድርብ ደስታ!!! ድንቅ ስኬት!!!

ሁለቱም ተቋሞቻችን በ2017 በጀት ዓመት በላቀ አፈፃፀም ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከተቋማት 1ኛ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከከተማው ከቢሮዎች 2ኛ በመውጣት የመኪና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
👍24🏆81😁1
"እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! ስኬቱ የሁሉም አመራርና፣ ሰራተኞችና ኦፊሰሮች የጥረት ውጤት ነው" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ

ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት በተካሄደው ምዘና ከተቋማት ( ካቢኔ አባል ካልሆኑ ) በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አንደኛ ደረጃ በመውጣት የመኪና ሽልማት ተበርክቶለታል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት ይህ ዕውቅናና ሽልማት መምጣት የቻለው ከላይ እስከታች የሚገኝ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ በትጋት፣ በጥረት፣ በመደማመጥ፣ በቅንጅትና በትብብር ተግባብቶ በጋራ መስራት በመቻሉ ስለሆነ መላው የደንብ ማስከበር አመራሮች ፣ሰራተኞችና የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ልፋታችን ውጤታማ ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ።

በእለቱ የባለስልጣኑ አመራሮች በዘንድሮ አመት ለውጤት ያበቃንን ተግባብቶና ተናቦ የመስራት ባህል በቀጣዩ በጀት ዓመት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አስገንዝበዋል ።

አክለውም በ2018 በጀት አመትም ወርቃማ ድል ለማስመዝገብና የከተማችን የደንብ ጥሰት ለመቀነስ ከወዲሁ ዝግጁ መሆን ይገባናል ብለዋል።

በተጨማሪም የባለስልጣኑ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች በተገኘው ውጤት ደስተኞች መሆናቸውንና በቀጣይም የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍121