የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
993 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በትላንትና በዛሬው እለት ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 5,670,000/ አምስት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰባ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

16/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በድምሩ 5,670,000/ አምስት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰባ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በየካ ክ/ከተማ 2,350,000 ብር፤ በቦሌ ክ/ከተማ 950,000 ብር ፤ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 1,050,000
ብር፤በቦሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 600,000
ብር ቅጣት ተቀጥቷል።

በተያያዘ ዜና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 370,000 ብር ፤በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 300,000 ብር እና በኮልፌ ክፍለ ከተማ 50,000 ብር ቅጣት በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡

ባለስልጣኑ በሁለት ቀናት በአጠቃላይ 14 ድርጅቶች እና 14 ግለሰቦች በድምሩ 5,670,000/ አምስት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰባ ሺህ/ ብር ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ እንዳይበከሉ ለድርጅቶችና ለግለሰቦች በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን በቀጣይ የግንዛቤና ህግ የማስከበሩ ስራ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች!!

18/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፐፕሊክና የፍትህ ልዩ ወረዳ 'ትናንት ፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!' በሚል መሪ ቃል ባለፉት 7 አመታት ከመጋቢት እስከ መጋቢት በተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ስኬቶች በተመለከተ ውይይት ተካሄደ።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ፣ የፍትህ፣የሠላምና ፀጥታ ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮችና አባላቶች ተገኝተዋል።

የመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልዩ ወረዳው ሰብሳቢ አቶ አሰፋ መብራቴ ከሰባት ዓመት በፊት ሃገሪቱ የነበረችበት ከፓለቲካና ከኢኮኖሚ አዙሪትና መሠረታዊ የሆነ ለውጥ ለማምጣት የተጓዘችበትን እርቀት የምናስታውስበት እንዲሁም የቀጣይ ስራችንን የምናጠናክርበት መሆኑ ገልጸዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና አውት ሶርሲንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በቀለ ተመስገንአቶ ፓርቲው ባለፉት ሰባት ዓመታት ያፀናቸውን ለውጦችና የተመለከተ የውይይት መነሻ ሰነድ አቅርበዋል።

በሂደቱም የፓለቲካ ለውጥ፣ በኢኮኖሚው ላይ የተደረገው ማሻሻ፣ የተቋማት ሪፎርም እና የዲፕሎማሲው ቱሩፋቶች አበይት የሰባት ዓመቱ የለውጥ ሂደቶች እንደነበር በሰነዱ ተገልጿል።

የሪፍርምና የስርዓት ለውጥ በማምጣት አካታች የሆነ የፓለቲካ ምህዋርን ለማፅናት በርካታ ውስብስብ ፈተናዎች ታልፈው ለዛሬው አንፀባራቂ የብልፅግና ጉዞ ላይ ለመገኘት እንደተቻለና ለነገዋ ኢትዮጵያ ልዕልና በ7/24 እየተሠራ እንደሚገኝ በሰነዱ ተብራርቷል።

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ባለፉት የለዉጥ ዓመታት ጉዞ ሀገራችንን በከፍታ ማማ የሚያስቀምጡ በርካታ ውጤቶች የተገኙበት የመጋቢት ፍሬዎችን በአግባቡ ማስገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን ተጠቅሷል።

በውይይቱ አመራርና አባላት ባለፉት ዓመታት ፓርቲው ያሳካቸው ውጥኖችና በቀጣይ በትኩረት መሰራት አለበት ባሉት ሃሳቦች ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በዕለቱ ለተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች በልዩ ወረዳው አመራሮች ምላሽና ማብሪሪያ በመስጠቱ መድረኩ ተጠናቋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ መጪው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ውይይት አካሄደ ።

19-07 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በቀጣይ የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠነቀቅ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በዓሉን አስመልክቶ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የፀጥታ፣የህገወጥ እርዶችንና ሌሎች የደንብ መተላለፎች እንዳይከሰቱ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አክለውም በዓሉ በሚከበርበት ወቅት በከተማዋ ላይ የተሰሩትን የኮሪደር መሠሰተ ልማቶች እንዳይበላሹ ህብረተሰቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ከደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ጋር በመቀናጀት ከተማችንን ጽዱ እና ውብ እንድትሆን መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል ።

ለውይይት መነሻ የተዘጋጀው ሰነድ የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ።

በመድረኩ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅና በበዓሉን አስመልክቶ አላሰፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና የግባእት እጥረት እንዳያጋጥም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚያስፈልግ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና-ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት

20/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446 ዒድ አል-ፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ ዒድ ሙባረክ!!!

የኢድ-አልፈጥር በዓል የሰላም ፣የጤና ፣ የደስታ ፣ የፍቅር እና የመረዳዳት በዓል እንደሆንልን እመኛለሁ።

በዓሉን ስናከብር ህዝበ ሙስሊሙ በጾም ወቅት በአብሮነት፣በመተሳሰብ እና የተቸገሩ ወገኖች ማዕድ በማጋራት ያለውን በማካፈል ጾሙን ሲያስፈጥር እንደነበረ ሁሉ በበዓሉ እለት እና ከበዓል በኃላ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ።

በበዓሉ እለትም የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት፣ በመተዛዘን ካለን በማካፈል በዓሉን በአብሮነት ልናከብር ይገባል ።

ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ ጥሰትና ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና በሚያደርገው ጥረት ላይ ህብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

ኢድ-ሙባርክ

ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ
ባለስላጣኑ በደንብ ቁጥር 179/2017 እና በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ ስልጠና ሰጠ

መጋቢት 22/2017ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ኃይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን የወጣ የዝውውርና ምደባ ደንብ ቁጥር 179/2017 እና በወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣውን በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ ሰራተኞች በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የስልጠናው ዓላማ በወንዝ ዳርቻ ብክለትና እንክብካቤ የወጣውን ደንብ ሀሉም ሰራተኞች በመገንዘብ ለከተማው ህዝብ ያለውን ፋይዳ ተደራሽ ለማድረግ እንዲያስችል እና የሰው ኃይል ውስንነት ያለባቸው ቦታዎችን ተመጣጣኝ የሰው ኃይል እንዲኖራቸው ለማድረግ የወጣውን ደንብ ለይ የሚሰጠውን ስልጠና መሆኑ ገልፀው ሰለጣኞች በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል ፡፡

በወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣውን ደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ የተዘጋጀ ሰነድ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠና ዳይሬክቶሬት የስልጠና ባለሙያ በአቶ ዮናኤል ለታ አቅርበዋል ።

በሰነዱ የወንዞችና የወንዞች ዳርቻን ስለማልማት፣ወንዝና የወንዝ ዳርቻ ከብክለት ስለመከላከል ፣ስለ ተከለከሉ ተግባራት ፣ ስለ ወንዝና ወንዝ ዳርቻ አስተዳደራዊ ቅጣት በሰፊው ገለፃ ተደርጓል

በሌላ መልኩ የሰው ሀይል ስምሪትን በልዮ ሀኔታ ለማመጣጠን የወጣውን ደንብ ቁጥር 179/2017 ስልጠና የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰው ሀይል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ሲሆኑ በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ሃብት ስምሪቱን ለማመጣጠን እንዲቻል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ሀብት መረጃዎችን ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በስልጠናው ከመቶ ስልሳ ፐርሰንት በላይ የሰው ኃይል ከተሟላላቸው ላይ ዝቅተኛ የሰው ኃይል ቁጥር ወዳላቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች በልዩ ሁኔታ በማዛወር ወይም በመመደብ የተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር በማስቻል የተገልጋዩን እርካታ ከፍ ማድረግ እንዲያስችል ደንቡ መደንገጉን አስገንዝበዋል ።

በለስልጠናው ሰለ ደንቡ ጠቅላላ ድንጋጌ፣ ስለ ዝውውርና ምደባ አፈጻጸም፣ ስለ አብይ ኮሚቴ አባላት እና ተግባርና ኃላፊነት፣ በዝውውር አፈጻጸም የሠራተኛ መብቶችንና ግዴታዎች ጨምሮ ዝርዝር ጉዳዮችን ላይ ሰፋ ባለ አቀራረብ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከመድረኩ በሁለቱም ደንብ ቁጥሮች ዙርያ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በአሰልጣኞቹ ምላሽ ተሰጥቶበት ስልጠናው ተጠናቋል።

ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።