ባለስልጣኑ የወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ብክለት ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸምን ገመገመ
23/07/2027ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ በመሆን የወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸም የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት አፈጻጸም ሪፓርት በማቅረብ አፈጻጸሙን ገመገመ።
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በቅንጅት የመስራት ሂደቱ ያመጣው ውጤት መልካም መሆኑን ጠቅሰው ሪፖርቱን በመጠምገም በቀጣይ በትኩረት መሰራት በሚገባቸው ነጥቦች ግብአት ለመውሰድ መሆኑ ገልፀዋል።
በመድረኩ የወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ በሳምንት ውስጥ የተሰሩ ተግባራትን አፈፃፀም ሪፖርት ሰነድ በባለስልጣኑ የቁጥጥር እና ኢንሰፔክሽን ባለሙያ አቶ አባትነህ ውባለ ቀርቧል።
በቀረበው አፈፃፀም ሪፖርት ሰነድ መሠረት ከቤቱ በክፍተት በታዩ እና በቀጣይም መስተካከል የሚገባቸውና ፣ ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ነጥቦች ላይ ሀሳብ፣ አስተያየት እና ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ደንቡን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የተሄደበት መንገድ ከተጠበቀው በላይ መሆኑን በመግለጽ ጠንካራውን ጎን የበለጠ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
አክለውም በቀጣይም ግንዛቤ የማስጨበጥ እና ከሌሎች ከቀሩ ተቋማት ጋር በቅንጅት የመስራት ሂደት ላይ አሁንም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በተቋማቱ የበላይ አመራሮች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

ባለስልጣኑ ያልተጣራ ፍሳሽ በመልቀቅ ወንዝን የበከሉ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 1,000,000 ብር በመቅጣት እርምጃ መውሰዱን ገለፀ
24/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በልደታ ክ/ከተማ 2 ፍሳሽን ወደ ወንዝን በመልቀቅ ወንዝ የበከሉ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 1,000,000 ብር በድምሩ 2,000,000/ሁለት ሚሊዮን ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።
ባለስልጣኑ ቢጂ አይ ኢትዮጲያ እና ሞሀ የለስላሳ መጠጦች ማምረቻ ድርጅቶች የሚለቁት ፍሳሽ በተደረገለት የናሙና ምርመራ ወንዝን የሚበክል መሆኑን የተረጋገጠ ሲሆን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ወንዞችን ከብክለት የፀዱ ከማድረግ አንፃር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በስፋት እየሰጡ መሆኑ ገልፀዋል።
በግንዛቤው መሠረት ተቋማትና ግለሰቦች ከህገወጥ ተግባራቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተመላክቷል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን
ለተጨማሪ መረጃ፦
ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ለተቋማዊ የስራ ልምድ እና ተሞክሮ ለመውሰድ ድሬዳዋ ከተማ ገቡ
መጋቢት 25/2017 ዓ.ም
** ድሬዳዋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የባለስልጣኑና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት የልዑካን ቡድን አባላት ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገብተዋል።
በልምድ ልውውጡ በተቋም አደረጃጀት፣ በኮሪደር ልማት ደህንነት አጠባበቅቅ አሰራር፣ ፤በሌሎች የደንብ መተላለፎችና የፀጥታ ጉዳዮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ያለውን ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት ይሆናል፡፡
በልምድ ልውውጡ የአዲስ አበባ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ዋና-ስራ አስኪያጅ ቃለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የባለስልጣኑ አመራሮችና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡
ለልዑካን ቡድን አባላቱ ደድሬዳዋ ከተማ ኤርፖርት እንደደረሱ በከተማ አስተዳደሩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።