ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ
05/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 3,176,000/ሶስት ሚሊየን አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 800,000 ብር፣ በልደታ ክፍለ ከተማ 750,000 ብር፣በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 426,000 ብር ፤በቦሌ ክፍለ ከተማ 300,000 ብር፣አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 300,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
በተያያዘ ዜና በኮልፌ ክ/ከተማ 300,000 ብር ፤በአቃቂ ክ/ከተማ 300,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት 7 ድርጅቶች እና 5 ግለሰቦችን በመቅጣት በድምሩ 3,176,000/ሶስት ሚሊየን አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ/ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ መደረጉን ተገልጿል።
ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ያስጠነቀቀ ሲሆን ድርጊቱን በሚፈጽሙ አካላት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👏11👍2❤1
የሀዘን መግለጫ
የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ በነበሩት በወ/ሮ መሰሉ ገ/ወልድ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።
ባለስልጣኑ ለቤተሰባቸው ፣ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል።
የቀብር ስነ-ስርዓታቸው በዛሬው እለት በቅዱስ ዮሴፍ ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 6 ሰዓት የሚፈጸም
ይሆናል።

😭11👎2
አዲስ አበባን ከብልሹ አሰራርና ከደንብ መተላለፎች ለማጽዳት በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
መጋቢት 6/7/2017 ዓ,ም
**የአዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በስነ-ምግባር፣በመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው የሰጡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ተቋሙ በሰጠው ስልጠና ግንዛቤ መሰረት በቀጣይ የስነ ምግባር ችግሮች የሚታይባቸው ሰራተኞች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አጠናክረን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉ ጌታ ጎንፋ በበኩላቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ተቋማዊ ለውጥን ለማረጋገጥ ሙያዊ ስነ-ምግባር በመላበሰ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
አክለውውም ኦፊሰሩ በስልጠናው መሠረት የአመለካከት ለውጥ በማምጣት የተገልጋዩን እርካታ ማሳደግና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በስልጠናው የተገኙት የባለስልጣኑ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶሰለሞን ይልማ ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት የተቋሙን እሴቶች፣ በመላበስ የተሰጠን ተልእኮዎችን መፈፀም እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዕለቱ የደንብ ማስከበር አመራርና ባለሙያዎች አዲስ አበባን ከብልሹ አሰራርና ከደንብ መተላለፎችና ለማጽዳት የተለወጠ አስተሳሰብ ለተቋማዊ ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ በመረዳት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ ተገልጿል።
በመጨረሻም ከስልጠናው ተሳታፊዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በተነሱት ሀሳብና ጥያቄዎች ላይ ከመድረክ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።

👍8❤1
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/2017 የተላለፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን 4,505,000 /አራት ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
07/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 4,505,000/ አራት ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በየካ ክፍለ ከተማ 3,740,000 ብር፤በአራዳ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፤በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 165,000ብር ቅጣት ተቀጥቷል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት 10 ድርጅቶች እና
13 ግለሰቦችን በድምሩ 4,505,000 /አራት ሚሊየን አምስት መቶ አምስት ሺህ/ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ የሚበክሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ ህግ የማስከበሩ ስራ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።

👍14❤1