የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የስራ አፈጻጸሙን ገመገመ።

08-07 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ከአስራ አንዱንም ክ/ከተማ ከተወጣጡ የቅድመ መከላከልና ስልጠና አስተባባሪዎች ጋር የደንብ ቁጥር 180/2017 አፈፃፀም እና የ3ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሂዷል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አንደተናገሩት በከተማችን የሚገኙ የህብረተሰብ አካላት የደንብ ጥሰትን እንዳይፈጽም እና እንዲጸየፍ ለማድረግ እየተሰጡ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው።

ተሻሽለው የሚቀርቡትን ደንብ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ በቂ እውቀት ኖሮት እና የተሻለ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ህብረተሰቡ በማውረድ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር እንዲቻል በማድረግና ህብረተሰቡ የደንብ ጥሰት መከላከል አላስፈላጊ መሆኑን በማስረዳት በጋራ አብሮን አንዲሰራ ማድረግ አንደሚገባ ም/ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

አክለውም ኦፊሰሮቻችን ስነምግባር የተላበሱ ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዱ እንዲሆን የተለያዩ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች የስራ አፈጻጻም የየክፍለ ከተማቸው ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ደንብ ቁጥር 180/2017 ከቅጣቱ በፊት ግንዛቤ ላይ ትኩረት ተሰጥቶበት መሠራቱን ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አስቀምጠዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍5
ባለስልጣኑ የህገ-ወጥ ነጋዴዎች መጋዘን በመቆጣጠር ከነ ሙሉ እቃው እርምጃ መውሰዱን ገለፀ

08-07 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ ባደረገው ጠንካራ ክትትል መሠረት የህገ-ወጥ ነጋዴዎች መጋዘን በመቆጣጠር ከነ ሙሉ እቃው እርምጃ መውሰዱን ገለፀ ።

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገቡ ዲማ እንደገለፁት በግለሰብ ግቢ ውስጥ መሸሸጊያ በማድረግ ተከማችተው የተቀመጡ በርካታ ህገወጥ የንግድ እቃዎችን በደንብ ማስከበር ፅ/ቤት በግብረሀይል በመውረስ በግምት ከ400,000/ አራት መቶ ሺህ/ ብር በላይ የሚገመቱ እቃዎቾ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል ።

ባለስልጣኑ ህገወጥነትን እደማይታገስና በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ እንደሚገባቸውና ወደ ህጋዊ መንገድ እንዲገቡ አሳስቧል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍5
የ6ተኛ ዙር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የንድፈ ሃሳብ ትምህርት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተጀመረ።


09/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቀጣይ ለሚሰጠው እጩ የ6ኛ ዙር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና የባለድርሻ አካላት ደንብ፣ መመሪያና አሠራርን የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የአሠልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ።

በስልጠናው መነሻ ላይ ተገኝተው የስልጠናውን ዓላማ እና ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ እንዲከታተሉ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እና የደንብ መተላለፍ፣ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ናቸው።

ከማዕከሉና ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ ሰልጥኖ አሰልጣኞች ስልጠናውን የሚሰጡት ባድርሻ ተቋም ከሆኑት ከግንባታ ፍቃድ፣ መሬት አስተዳደር ፣ ከተማ ግብርና፣ ቄራዎች ድርጅት፣ አከባቢ ጥበቃ፣ ውኃና ፍሳሽ፣ ፅዳት አስተዳደር፣ ትራፊክ ማናጅመንት፣ ንግድ ቢሮ እና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የመጡ አሰልጣኞች ሲሆኑ ስልጠናውም በማዕከሉ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት የግንባታ ፍቃድ፣ መሬት አስተዳደር፣ ቄራዎች ድርጅት እና ከተማ ግብርና ደንብ፣ መመሪያዎችና አሰራሮች በዝርዝር ቀርቧል።

ስልጠናው ለቀጣይ ሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ሰልጣኞችም በዲስፕሊንና በመልካም ተሳትፎ እየተከታተሉ መሆኑን ተመልክተናል።

ዘገባው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍5