የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.1K subscribers
1.79K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣጣኑ "ሰው ተኮር ተግባሮቻችን ለአብሮነታችን" በሚል መሪ ቃል የአቅመ ደካማ እናት ቤት እድሳት አጠናቆ ለባለቤቱ የቁልፍ ርክክብ አደረገ

13/06/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ "ሰው ተኮር ተግባሮቻችን ለአብሮነታችን" በሚል መሪ ቃል በወረዳ 02 ለሚገኙ አቅመ ደካማ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ አስረከበ፡፡

በቤቱ ምርቃት መርሀ-ግብር ላይ የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለ ስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ ፣የወረዳ ደንብ ማስከበር አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በፕሮግራሙ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ ደንብ መተላለፎችንና ህገ-ወጥ ተግባራትን ከመከላከል ጎን ለጎን ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ሰው ተኮር የበጎፍቃድ ስራዎችን በመስራት ለህብረተሰቡ ያለውን አለኝታነት በተግባር እያሳየ ይገኛል ይህ ሰው ተኮር በጎ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በምርቃት ፕሮግራሙ የኮልፌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ በኑሮአቸው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ረዳት ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በሰው ተኮር ተግባራት ላይ በመሳተፍ በክ/ከተማው በቤት እድሳት፣ማእድ በማጋራትና በሌሎች የተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎች እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

አክለውም የብልፅግና እሳቤ ከሆነው የሰው ተኮር ስራ አንዱ በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው ያሉ ወረዳዎችን በማስተባበር የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረክበዋል በቤት እድሳት ወቅት አስተዋጾ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የቤት እድሳት የተደረገላት የወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሙሪዳ አወል ከደንብ ማስከበር አመራርና አባላት ለተደረገላቸው ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል፡፡

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍2
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 የግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሂዷል ።

15 /06 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 የመጀመሪያ ስድሰት ወር የእቅድ አፈጻጸም የእውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ ።

በመርሀ ግብሩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስ፣ የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ኢቲቻ፣ ሌሎች አመራሮችና የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ኦፊሰሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ተቋሙ የደንብ መተላለፎችን በመቀነስ እየሠራና እንዲሁም ስራዎችን በቴክኖሎጂ በማዘመን ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝና የኦፊሰሮችን ጥቅማ ጥቅም ለማስጠበቅ ሰፊ ስራ አየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

በዋናነትም ማንኛውንም የተቋሙን ተልዕኮ ስንወጣ በፍጹም ስነ-ምግባርና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ኃላፊነታችን በታማኝነት አንወጣ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመድረኩ የተገኙት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስ በክ/ከተማው ሚሰተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ እና የአደባባይ በአላትና የአፍርካ ህብረት ጉባኤ ሰላማዊ ሆኖ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የደንብ ማስከበር ተቋም ከሌሎች አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራዎችን መሰራቱንና ክ/ከተማውም እውቅና መስጠቱን አሰታውቀዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ኢቲቻ በግማሽ ዓመቱ በክ/ከተማው እንደ ጽ/ቤት የነበረውን እቅድ አፈጻጸም ሲገልጹ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት ህገወጥነትንና ደንብ ጥሰቶችን በመከላከልና በመቆጣጠር ደንብ ተላላፊ ከሆኑ አካላት ከቅጣት 7 ሚሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን ገልፀዋል።

በመጨረሻም በ2017በጀት ዓመት በስድስት ወራት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች የእውቅናና ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን
1ኛ ወረዳ 01
2ኛ ወረዳ 03
3ኛ ወረዳ 05 በመሆናቸው የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆነዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡