የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
አራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም የእውቅና የሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ

የካቲት 16/2017 ዓ.ም
**አዲስ አባባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ በኮሪደር ልማት ስራዎች እና የ2017 በጀት አመት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ፣የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራ፣ሌሎች የክ/ከተማው ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የመከላከያ፣ የፌደራል እና የከተማው የፖሊስ አባላት፣ ባለድርሻ አካላት ፣ የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ኦፊሰሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ዓለምን ያስደመመው አፍሪካውያንን ያነጋገረ የአዲስ አበባ የልማት ስራ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አባሎቻችን እና ባለድርሻ አካሎች ከልብ አመስግነው የመጀመሪያ የኮሪደር ልማት ስረሠ የተጀመረው በአራዳ ክፍለ ከተማ ላይ ነው የአራዳ ክፍለ ከተማ ነው ለዚህም ትልቁ ኃይላችን የደንብ ማስከበር እንደነበር ገልጸዋል።

በዚህም ኦፊሰሩ ለልማት የተነሱ እናቶቻችን እና አባቶቻችን ያለምንም ወጪ እቃቸውን ወደ ተሽከርካሪ በመጫንና ወደ ተሰጣቸውም ቦታ በመውሰድ የአራዳ ክፍለ ከተማ ኦፊሰሮችና አመራሮች ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ጠቁመዋል።

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክ/ከተማ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ ደንብ ማስከበር በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የሚገኝ ተቋም መሆኑና እያከናወናቸው ያሉ ውጤታማ ተግባራት በግልጽ ማሳያ ናቸው በማለት በቀጣይ ተቋሙ ለሚያከናውኗቸው ስራዎች ከጎኑ ሆነው እንደሚደግፉ ተናግረዋል ።

የአራዳ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲ የተሰራው የኮሪደር ልማት ስራው ተውቦና ደምቆ የምናየው ከፊትም ከኋላም ደንብ ማስከበር አባላት መሰዋዕትነት እየከፈሉ ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ላደረጉት አስተዋፅኦ ተቋሙና አባላቱ ማመሰገን፣ ማክበር እና መሸለም እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመድረኩ የእንኳን ደና መጣቹ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን ቀን እና ሌሊት የሰሩ የደንብ ማስከበር ተልዕኮ ተቀብለው የሚታዩ የደም መተላለፍና ህገ-ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር በመከላከል በዚህ ስድስት ወር ውስጥ የደንብ የደንብ መተላለፍ 53.9% መቀነሱ ገልጸዋል።

አክለውም እውቅና እና ሸልማት መሠጠቱ የተሰሩ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት ጉልህ ሚና አንዳለው ገልጸው ከ1ኛ - 3ኛ የወጡ ወረዳዎች እውቅና እና ሸልማት ተበርክቶላቸዋል።

እውቅና እና ሸልማት በአፈፃፀማቸው መሠረት 1ኛ ወረዳ 5 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
2ኛ ወረዳ 6 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
3ኛ ወረዳ 9 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በመውጣት እውቅና እና ሸልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘገበው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ ለ6ተኛ ዙር ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ከኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ።

17/06/2017
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ6ተኛ ዙር ለሚያሠለጥናቸው 2ሺህ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ውል ስምምነት ተፈራረመ::

ስልጠናው የሚሰጠው በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርስቲ አፓስቶ ካምፓስ እንደሚሰጥ በውል ስምምነቱ ወቅት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አስታውቀዋል።

የፓራ ሚሊተሪ እጩ ኦፊሰሮቹ ስልጠና የንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ ስልጠናዎችን ያካተተ እንደሚሆንና ብቁ የደንብ አስከባሪ ኦፊሰሮችን በማሰልጠን ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ረ/ኮሚሽነር ደረጀ አስፋው ገልፀዋል።

በውል ስምምነት ፊርማው ወቅት የሁለቱም ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል ኃላፊዎቹ ተፈራርመዋል።

ከዚህ ቀደም ዩንቨርስቲው የ5ተኛ ዙር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን ስልጠና እና የአጠቃላይ ኦፊሰሮችን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠቱ ይታወሳል።

ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍9👏3
የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርኃ ግብር ተከናወነ።

17/06 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀትና ተሞክሮ ሽግግር የሚካሄድበት የወርቃማ ሰኞ ማለዳ ፕሮግራም ሠራተኛውን የሚነቃቃና ለስራ ዝግጁ የሚያደርግ መሆኑ ተገለፀ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ያለፈውን ሳምንት ውጤታማ ስራዎችን አስታውሰው የተያዘው ሳምንት የስራ አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል።

ይህ የወርቃማ ሰኞ ማለዳም በአመራሩና በሰራተኛው መካከል ያለውን ቤተሰባዊነት እጅግ እያጠናከረና ምቹ የስራ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሚገኝ አስታውሰዋል።

በዛሬው መድረክም የባለስልጣኑ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ በራስ የመተማመን /self confidence / በተመለከተ እውቀታቸውን በማካፈል የህይወትና የስራ ተሞክሯቸውን አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍9