የደንብ ማስከበር ተልዕኮን ለማስፈፀም በስነ-ምግባር የታነፀ ኦፊሰርን መገንባት እንደሚገባ ተገለፀ።
27/05/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በስነ-ምግባር የታነፀ እና ሌብነትን የሚፀየፍ ኦፊሰርን ለማብቃት የሚያስችል ግምገማዊ ስልጠና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አዳራሽ አካሄደ።
በግምገማዊ ስልጠናው የሁሉም ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማው የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ቡድን መሪ፣ ተባባሪ አካላትና አጠቃላይ ኦፊሰሮች ተካፋይ ሆነዋል።
መድረኩን ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ ዓለሙ እንደተናገሩት ኦፊሰሩን ለተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ለማብቃት እየተሠራ እንደሚገኝና ውጤታማ ስራዎችንም ማከናወን እየተቻለ መሆኑን ገልፀዋል።
የመድረኩ የክብር እንግዳ የሆኑት የክፍለ ከተማው ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በቀለ እንዳሉት ተቋሙ ከጊዜ ወደጊዜ እራሱን በማዘመን የደንብ መተላለፎችንና የፀጥታ ስራዎችን በብቃት በመወጣት ተልዕኮውን እየፈፀመ እንደሚገኝና በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
ግምገማዊ ስልጠናውን የሰጡት እና የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ሲሆኑ ስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራርን ከመልካም አስተዳደር አንፃር በመቃኘት ለችግሩ መፍትሔ ማስቀመጥና ተጠያቂነትን ማስፈን የስልጠናው ዓላማ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በመሆኑም ባለስልጣኑ ፈፃሚውንና ኦፊሰሩን ከስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራር እራሱን በመጠበቅ የከተማ አስተዳደሩን ተልዕኮ ከዳር እንዲያደርስ የተለያዩ የአቅም ግንባታ እና ግምገማዊ ስልጠናዎችን እየሠጠ እንደሚገኝና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በስልጠናው ያነጋገርናቸው ሠልጣኞች እንደገለፁት፦ ማህበረሰቡን በመልካም ስነ-ምግባር በማገልገል ዘላቂ አጋርነቱን ማረጋገጥ እንድንችል ስልጠናው በርካታ ግንዛቤዎችን ያስገነዘበ መሆኑን አስረድተዋል።
የመድረኩን ውይይት የመሩት የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ እንደተናገሩት የደንብ ማስከበር ኦፊሰር በህዝቡ ተመልምሎ ሠልጥኖ መልሶ ህዝቡን የሚያገለግል በመሆኑ ሁልጊዜ እራሱን ከብልሹ አሠራር እየጠበቀ ህብረተሰቡን በታማኝነት ሊያገለግል እንደሚገባ ተናግረዋል።
አክለውም በከተማዋ ውስጥ ያለውን ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ስራዎች የተሳለጡ እንዲሆኑ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሩ ሚና የላቀ በመሆኑ በቀጣይም በትጋት ተልዕኮውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍12
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በወረዳ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶቹ ከባለድርሻ አካላት እና ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ
27-05 -2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የወረዳ ደንብ ማስከበር ፅህፈት በ2017 በጀት አመት የ6 ወራት ያከናወናቸው ተግባራት የአፈፃፀም ሪፖርት ሰነድ ቀርቦ አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት እና ከየወረዳው ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ።
በውይይት መድረኩ ተቋሙ በበጀት አመቱ 6 ወራት ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል እና በሂደቱ የተስተዋሉ ክፍቶችን ከማህበረሰቡ የጋራ ውይይት በማድረግ መፍትሄ ለመስጠት እንደሆነ ተገልጿል።
በውይይት መድረኮቹ ባለድርሻ አካላት፣የሀይማኖት አባቶች፣ተፅዕኖ ፈጣሪ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በጎ ፈቃደኞች፣አርሶ አደሮች እና የከተማው ነዋሪዋች ተገኝተዋል።
የህብረተሰብ ውይይት መድረኩ በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተማዎች በማካሄድ የማጠቃለያ መድረኩ እንደ ማዕከል የሚካሄድ ይሆናል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍19👏2❤1
ባለስልጣኑ የመንገድ መሠረተ ልማት ያበላሸ ድርጅት 300,000 ብር መቅጣቱ አስታወቀ
03-06 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ምሽትን ተገን በማድረግ የቆሸሸ ውሃ አዲስ ወደ ተሠራው አስፓልት የለቀቀው የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ) ብር በመቀሰጣት ያቆሸሸውን አካባቢ እንዲያጸዳ አድርጓል ፡፡
ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍20👏2
ባለስልጣኑ በክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ሲያካሄድ የቆየውን የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ
04/06/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በወረዳዎችና በክፍለ በከተሞች ሲካሄድ የቆየው የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ለመከላከል ያለመ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ ፕሮግራም ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የከተማው ነዋሪዎች ጋር የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከእቅድ አንፃር የተከናወኑ በርካታ የደንብ መተላለፎችን የመከላከል እና የመቆጣጠር ተግባራት እንዳሉ ጠቅሰው እነዚህ ተግባራት በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በባለድርሻ አካላት ትብብር የታገዙ እንደነበርና በቀጣይ ቀሪ ወራቶችንም ህብረተሰቡ ከጎናችን በመቆም በጋራ ሆነን ደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል ።
አክለውም በተሰጠን ተልዕኮ ዘጠኙ የደንብ መተላለፎችን በመከታተል እና በመቆጣጠር በህጋዊ መንገድ የሚሰራውን ማህበረሰባችን በአግባቡ በማገልገል እየተከናወነ ያለውን የሪፎርም ስራዎቻችንን በማጠናከርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን በማከናወን ከመቼውም ጊዜ በላይ ህብረተሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆንናቸውን ገልፀዋል።
በመድረኩ የባለሥልጣኑ የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የተቋሙ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ አቅርበዋል ።
በሪፖርቱ ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በቁርጠኝነት ከመወጣት ጎን ለጎን ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ ሰው ተኮር ስራዎችን በመከናወን በግማሽ ዓመቱ 11 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ አስረክቦል፣ የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት በማካሄድ ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ስራ ተከናውኗል እንዲሁም ወላጅ አልባ ህጻናት በመንከባከብ እያሳደገ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
በተጨማሪም በመድረኩ የባለስልጣኑ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የመልካም አስተዳደር ብልሹ አሰራር አፈጻጸም ሪፖርት እና በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 167/2016 ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቧል።
በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርት እና ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።
ዘገባው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

👍9👏1