የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የየተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡና የአደባባይ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ

24/05/2017ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያ ግማሽ አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡና የአደባባይ በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስተዋፅኦ ላበረከቱ ለባለድርሻ አካላት እና የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎችና የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እውቅናና የምስጋና ፕሮግራም የባለስልጣኑና የክፍለ ከተማው አመራሮች በተገኙበት የእውቅናና ምስጋና እና ፕሮግራም ተካሂዷል።

በመረሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈሪ እንደገለፁት፣ የባለስልጣኑን የውስጥ አሰራሮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው አመራሩና ኦፊሰሩ በሰራው ጠንካራ ስራ የደንብ ጥሰት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር በከተማዋ 58 በመቶ ቀንሷል ብለዋል።

ተቋሙን በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሀይል እና በአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ናቸው።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ግርማ ሰንበቱ በበኩላቸው የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያ ግማሽ አመት ከ6 ሚሊየን ብር በላይ በቅጣት እና በጨረታ ገቢ ማድረጉን ገልፀው ባሳለፍነው አመት ተመሳሳይ ወቅት የተገኘው 3 ሚሊዮን ብር እንደነበር አስታውሰዋል።

ሀላፊው በተያዘው በጀት አመቱ 6ወራት የደንብ መተላለፎች በብቃት በመከላከል እና በመቆጣጠር የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ወረዳዎች እና የተከበሩ በአላትን/የኢሬቻ፣ መስቀል እና ጥምቀት/ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲያልቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለ ድርሻ አካላት እና የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እውቅና መስጠት የቀጣይ ስራችን ላይ ተነሳሽነት እንደሚፈጥር ገልጿል።

በእውቅና እና ሽልማቱን ፕሮግራሙ ወረዳ1፣ወረዳ10 እና ወረዳ 8 ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍3👏1
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ።

26-05 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ተካሄደ

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ንቁ በሆነ መንፈስ ሳምንቱን በጥሩ ሁኔታ ዉጤታማ ስራ ለማከናወንና በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን እና እየተመካከርን ሳምንቱ ሙሉ ወርቃማ እንዲሆንልን መልካም ምኞት በመለዋወጥ እርስ በእርሳችን የምንመካከርበት፣ የምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል ።

በዕለቱ የባለስልጣኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ የራሳቸውን የህይወትና የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።

ራስን ሁል ጊዜ በዕውቀት ማዳበር ፣ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ጋር መልካም ግንኙኘት መኖር ፣ለባለሙያ ልምድን ማጋራት እና ስራን በትብብር ፣ በአንድነት እና ዝቅ ብሎ መስራት ዉጤታማ እንደሚያደርግ በመድረኩ ገልጸዋል ፡፡

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍94
ባለስልጣኑ የቀሪ ስድሰት ወራት የተከለሰ የእቅድ ውይይት አካሄደ

26-05 -2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ስድስት ወራት የተከለሰ ዕቅድ ውይይት ከማዕከሉ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ባለፈው ስድስት ወራት በነበረን አፈፃፀም የታዩ ጥንካሬዎች በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ወራት የመፈጸምና የማስፈፀም አቅምን በማጎልበት ውጤታማ ውጤታማ ተግባር መከናወን ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት የጣይ ስድስት ወራት የተከለሰ እቅድ ሰነድ በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል ።

በሰነዱ ባለፉት ስድስት ወራት የተቋም ግንባታ ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋማዊ እርምጃ መወሰዱን ተጠቅሰዋል፡፡

ባለስልጣኑ ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድ ሰው ተኮር ሰራዎችን በማከናወን አስራ አንድ የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ማስረከቡ በሪፖርቱ ተገልጿል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍73