የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
996 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የአንካራው ስምምነት የተገኘው ውጤት የሀገራችን ጠንካራ የዲፕሎማሲ ውጤት ማሳያ መሆኑን ተገለፀ

07/04/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የማዕከል፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ኃላፊዎች እእንዲሁም የማዕከሉ ዳይሬክተሮች በተገኙበት በወቅታዊ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተደረሰውን የአንካራ ስምምነት ተከትሎ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የውይይቱ መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ ቤት የአቅም ግንባታ እና የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ የአንካራው ስምምነት የተገኘው ውጤት የሀገራችን ጠንካራ የዲፕሎማሲ ውጤት ማሳያ መሆኑ ገልፀዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፅኖ ፈጣሪነት ለማሳጣት በጎረቤት ሀገራት በጠላትነተ ለማስፈረጅ የየተዘጋጁ አካላት ሴራ ያከሸፈ መሆኑ ገልፀዋል።

አክለውም ስምምነቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥበብና ብስለት በተሞላበት መንገድ ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ በህጋዊ መልኩ ምላሽ የተገኘበት መሆኑ ገልፀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በአንካራው ስምምነት በርካታ የኢኮኖሚ ትሩፋቶች የሚያስገኝ በመሆኑ የተጀመሩ የልማት ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል የሀገራችን ብልፅግና እውን ለማድረግ የሚያጠናክር መሆኑ ገልፀዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ ሰሞኑን በNBC Ethiopia በሳምንቱ ጫወታ ፕሮግራም ስለደንብ ማስከበር ባለስልጣን የቀረበው መረጃ የተሳሳተና ተቋሙን የማይገልፅ መሆኑ አስታወቀ

16/04/2017 ዓ.ም
**አዲስ አባባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ደንብና ህግና የማስከበር ተግባሩን ለማስተጓጎል ሆን ብለው የተቋሙን ስም ለማጠልሸት የተሳሳተ አመለካከት በህብረተሰቡ ላይ እንዲሰርፅ በሚያደርጉ ግለሰቦችና ተቋማት በህግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

የባለስልጣኑ የህግ አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ ብርሃኑ ኮርሳ ሰሞኑን በNBC Ethiopia በሳምንቱ ጫወታ ፕሮግራም ስለደንብ ማስከበር ባለስልጣን የቀረበውና በሶሻል ሚዲያዎች የተጋራው መረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የማይገልፅና ከሚሰጠው አገልግሎት ፈፅሞ የተሳሳተ መረጃ መሆኑ ገልፀዋል።

የፕሮግራሙ አቅራቢው ስለባለስልጣኑ የገለፀው መረጃ ከተቋሙ ተግባር ፍፁም አሉባልታና የሀሰት መሆናቸውና ድርጊቱ ህገ-ወጦችን የሚደግፍና የሚያበረታታ በመሆኑ ሊታረም እንደሚገባ ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ ፕሮግራሙ ከሚዲያ እና ከጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ባፈነገጠ መልኩ የተቋሙን ሀሳብ፣ አሰራርና መመሪያ ለህብረተሰቡ አሉታዊ እንዳለውና በጥላቻና ሀላፊነት በጎደለው መልኩ የቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቋል።

ፕሮግራሙ እንደ ሚዲያ አሰራር የተቋሙ ስራዎች በመግለፅ ክፍተቶቹን እንዲታረሙ ማሳየት ሲገባው ሆን ብሎ ከዚህ በተቃራኒ ፍፁም አሉታዊና የጥላቻ አመለካከትን የቀረበበት በመሆኑ ጉዳዩ ለህግ እንደሚያቀርበው ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ተቋሙ የሄደበትን በህግ የመጠየቅ ሂደትና የደረሰበት ውጤት ለህብረተሰቡ ግልፅ እንደሚደረግና በተቋሙ ላይ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጭ ማንኛውም አካላት ላይ በህግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ አዲስ አበባ ከተማን ውብ ፣ፅዱ፣ ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ ለማድረግ የደንብ መተላለፎች ለመከላከልና የበኮሪደር ልማቱ መሰረተ ልማት ደህንነት ለማስጠበቅ የተሰጠውን ሀላፊነት ለመወጣት ቀን ከለሊት እየሰራ ያለውን ስራ በሀሰት መረጃዎች አንደማይደናቀፍ አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በሀሰት መረጃ እና በአሉባልታዎች የተቋሙን ስም ለማጠልሸትና ለህብረተሰቡ የተሳሳተ መረጃ የሚሰጡ ግለሰቦችና ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ የህዝብና የመንግስትን መሬት የወረረን ግለሰብ ተጠያቂ ማድረጉን አስታወቀ

ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ቶልቻ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሬት ባንክ የገባን የህዝብና የመንግስትን መሬት በህገወጥ መንገድ ለግል ጥቅም ለማዋል የተወረረን መሬት ማስመለሱ አስታውቋል።

ግለሰቡ በሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ 477.61ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ በማጠር የወረረ መሆኑን በባለስልጣኑ የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር አባላቱ በተደረገው ክትትል የተደረሰበት መሆኑ ተጠቁሟል።

ባለስልጣኑ መረጃውን በማጣራት ከፖሊስ አባላት ጋር በመሆን ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል በሊዝ አዋጅ ተጠያቂ እንዲቀጣ ክስ እንዲመሰረት በማድረግ የታጠረውን ቦታ በማፍረስ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ማድረጉ ገልጿል።

ባለስልጣኑ በህገ ወጦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ደንብ የሚተላለፉ አንዳንድ ግድ የሌሽና ስግብግብ ግለሠቦችን ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪውን ያቀርባል ።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/

የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement

የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT

የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ
ባለስልጣኑ የአቅመ ደካማ ቤት አድሶ በማጠናቀቅ ከበዓል ስጦታ ጋር ለባለቤቱ አስረከበ

28 - 04 - 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ወረዳዎችን በማስተባበር በወረዳ 6 ለሚገኙ አቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ሙሉ እድሳት አድርጎ በማጠናቀቅ ከበዓል ስጦታ ጋር ለባለቤቱ አስረከበ።

በርክክብ ፕሮግራሙ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ ደንብ መተላለፎችንና ህገወጥ ተግባራትን ከመከላከል ጎንለጎን ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ችግር ፈቺ የሆኑ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በመስራት ዛሬ እድሳቱ አጠናቆ ለርክክብ የበቃው ቤት አንዱ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም ሰው ተኮር ተግባራት ተቋሙ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ በዋነኝነት የተሰጠንን ተልዕኮ ከማሳካት ባሻገር በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት በመሳተፍ ላይ እንደሆነ ገልፀው በክ/ከተማው ወረዳ 6 ለሚገኙ አቅመ ደካማ የቤት እድሳት የወረዳውን አመራሮች በማስተባበር በማጠናቀቅ በበዓል ዋዜማ ለባለቤቱ በማስረከባቸውን መደሰታቸው ገልጸዋል ።

የቤቱ እድሳት የተደረገላቸው ወ/ሮ በቀለች ባልቻ ቤታቸው በመታደሱ እና በባለስልጣኑ በተደረገላቸው የማዕድ ማጋራት የደንብ ማስከበር ባለስልጣንን በተለይም የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤትን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ በማስረከቡ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ የሚሰጠውን አገልግሎትና ተግባራቶቹን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም በማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ
30/04/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አገልግሎትና ተግባራቶቹን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የሚያስችል አጭር የማስፈፀሚያ እቅድ የባለስልጣኑ ፕሮሰስ ካውንስል አባላትና እና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከተወከሉ የሶፍትዌር እና የፕሮጀክት ቡድን መሪዎቸሸ ጋር ውይይት ተካሄደ ::

በውይይቱ ባለስልጣኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማተሸን ለመሠዘመን ባስቀመጠው አቅጣጫን መሰረት ለተገልጋይ እና ለአገልጋይ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር ተቋሙን ከዘመኑ ጋር ለማራመድ ስራዎቸሸ መጀመራጀው የባለሥልጣኑ ዋና ስራአስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልፀዋል::

አክለውም ተቋሙ የእቅዱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ግልፅ አሰራር ለመዘርጋት፣ ከወረቀት ነፃ አገልግሎት ለመስጠት፣ የመረጃ አያያዝ በማዘመን ደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን በአንድ ማዕከል ለመቆጣጠር እንዲሁም ብልሹ አሰራርን በመቀነሰ የተገልጋይን እርካታ ለመጨመር የሚረዳ አሰራር ስርአት ቴክኖሎጂ ለመዘርጋት መታቀዱ ጠቁመዋል::

ማስፈፀሚያ እቅዱን ያቀረቡት የባለስልጣኑ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በተቋሙ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትን ለመገንባት በካሜራና በሶፍትዌር የታገሰ የአገልግሎትና የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት የማስፈፀሚያ እቅዱ መዘጋጀቱን ገልፀዋል::

በቀረበው እቅድ ላይ ተሳታፊዎች ስራዎችን በቴክኖሎጂ ከማዘመን እና ከማቀላጠፍ አኳያ አዳዲስ በሚያስፈልጉ እና ሌሎች ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጓል::

በመጨረሻም የባለሥልጣኑ ዋና ስራአስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሌሎች ተቋማት በደረሱበት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የዕድገት ደረጃ መድረስ ያስችለው ዘንድ የባለድርሻ አካላትን በዘርፍ ያላቸውን እውቅት፣ ልምድና ተሞክሮ በመወሰድ የሚጀመርበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

01 - 05 - 2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸሙን የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ተገመገመ ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከባለስልጣኑ ጋር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባከናወናቸው ውጤታማ ስራዎች በከተማዋ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ማስፈን አና በከተማው የሚታዪ የደንብ ጥሰትን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ስራዎች መሠራታቸው ገልፀዋል።

አክለውም ደንብ ማስከበር ራሱን በማዘመን ቢሮውን ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ ማድረግ መቻሉ የሚበረታታ መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል ።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ውጤታማ የሆኑ አፈፃፀሞች የተገኙት ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋቱ ስራዎችን በዕቅድ መሠረት ማከናወን በመቻሉ ነው።

አክለውም በግማሽ ዓመቱ ሳይከወኑ የቀሩና በክፍተት የታዩ ጉዳዮችን ዕቅድ በመከለስ የተሻለ ስራ ለማከናውን ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ በዝርዝር ቀርቧል።

ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ እስከአሁን ባለው ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማስገባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮን የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል።

በሪፖርቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ ሠላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት እና የተፈጸሙ ድርጊቶችን ሳይባባሱ በቅንጅት በመከላከል የከተማውን እና የህብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በእለቱ ከሁለቱም ተቋማት ማኔጅመንት አባላት በቀረቡት ሪፓርት ዙሪያ በርካታ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው የተንሸራሸሩ ሲሆን ስራዎችን ማዘመን ዲጅታል ማድረግ እና በቅንጅት የሚሰሩ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል የሚለው ሀሳብ ተነስቷል።

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በግማሽ ዓመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር ክፍተቶችን ደግሞ በመሙላትና በማረም ለተሻለ ውጤት ሁሉም አመራርና ፈፃሚዎችን በማስተባበር ለለውጥ እንዲተጋ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው።