ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራዎችን ጉብኝት አደረገ
02 - 05 - 2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ዳይሬክተሮች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት የተቋሙ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መታገዝ የሚከናወኑ ሥራዎችን ተሞክሮዎች ወደ በተቋሙ ለመተግበር ጉብኝት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለወንጀል መከላከልና ለወንጀል ምርመራ ሥራ የታጠቃቸውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅሞችን በመጠቀም ስራዎችን ክትትል የሚደረግበት ስረዓት መመልከት ተችሏል ።
የፌደራል ፖሊስ ሪፎርም ተከትሎ በርካታ ተግባራትን በዲጂታል መንገድ እያከናወነ ይገኛል ከነዚህም ውስጥ የዜጎች ተሳትፎ ማረጋገጫ(EFP App) በተለያዩ የቋንቋ አማራጭ የቀረበ ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ የተለያዩ መረጃዎችን ህብረተሰቡ መጠቆም ሲፈልግ ባለበት ቦታ ሆኖ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት አዲስ በተከፈተው አፕሊኬሽን በመጠቀም የፎቶ፣ የቪዲዮ፣ የድምፅ መልእክቶችን በመላክ ለተቋሙ ተደራሽ ማድረግ የሚችልበት መንገድ ገለፃ ተደርጓል።
በተጨማሪም ህብረተሰቡ በ991 ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም ጥቆማዎችን መሰጥት እንደሚችል የፌደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ኮ/ር ደምስ ገልጸዋል ።
የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተጠናከረ ኃይል ለመገንባት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተፈጠረው ሁለንተናዊ አቅም በተለይም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በሎጂስቲክስ አቅም ግንባታ ላይ እየታየ ያለው ከፍተኛ ለውጥ ለሌሎች ተቋማትም ሞዴል ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል።
አክለውም ከልምምድ ልውውጡ ያገኘነውን ተሞክሮና እውቀት ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሚያስፈልጉትን ተግባራዊ ተናግረዋል ።
ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው።

ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን የቅድመ መከላከል ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሚሰራ ገለፀ
ጥር 09/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያ 6 ወራት የተሰሩ የደንብ መተላለፍ የቅድመ መከላከል ስራዎች፣ የተወሰዱ እርምጃዎች፣የሰው ተኮርና የልማት ስራዎችን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ።
መድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት ባለስልጣኑ የተሰጡትን ተልዕኮዎችን በአግባቡ የተወጣበት፣የተቋሙን አሰራር ለማዘመን በርካታ ሰራዎች የተሰሩበትን ፣ በተለይም የጎዳና ላይ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰበት እና በሁሉም የደንብ ጥሰቶች ውጤታማ ስራዎች የተሰሩበትን መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
አክለውም በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች በመጠበቅ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምር ግብረ ሀይል ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል ።
ዋና ስራ-አስኪያጁ በቀጣይ የደንብ መተላለፎችን እርምጃ ከመውሰድና ባሻገር የቅድመ መከላከል ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሚሰራ ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ ስድስት ወራቱ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ የእቅድ በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
በሪፖርቱም ታቅደው የተፈጸሙ ተግባራት ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱ መፍትሔዎች ቀርበው የቀጣይ መፍትሄ ላይ ውይይትና የትኩረት አቅጣጫ ተሰቷል።
በሪፖርቱ ከተወረሱ ንብረቶችና ከጨረታ ሰነድ ሽያጭ ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማድረግ መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።
በዕለቱ ተቋምን ከማዘመንና ዲጅታልላይዝ በማድረግ እሰከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ሊተገበር እንደሚገባ ከተሳተፊዎች ተጠቁሟል።
በቀረቡት ሪፓርት ዙሪያ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች በርካታ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው በማዕከሉ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የእንኳን ለ2017 ዓ.ም የጥምቀትና በዓል በሰላመ አደረሳችሁ!
ጥር 10/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤በዓሉ የሠላም፣
የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱ ይገልፃል።
የጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እምነታቸውን በነፃነት በአደባባይ ወጥተው በጋራ የሚያከብሩበት ፣የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክሩበት ፣መንፈሳዊ እሴቶቻቸውን የሚያዳብሩበት እና ማህበረሰባችን ተቻችሎና ተከባብሮ በጋራ መኖርን ለመላው የዓለም ህዝቦች ተምሳሌትነቱን የሚያሳዩበት ታላቅ በዓል ነው።
በዓሉ የአብሮነትና የሰላም በመሆኑ በዓሉ ስናከብር በጋራ፣በመተሳሰብ፣ በአንድነት የበዓሉን ሀይማኖታዊ ይዘቱንና ኢትዮጵያዊ ዕሴቶቻችንን በጠበቀ መልኩ ሊናከብረው ይገባል።
በዓሉ ስናከብር በከተማው የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች እና ተያያዥ ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈጸሙ፣የኮሪደር ልማት ስራዎች እንዳይበላሹ እና በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ማለት እወዳለሁ፡፡
መልካም የጥምቀት በዓል !
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ሥራ-አስኪያጅ

ባለስልጣኑ በመጀመሪያው 6ወራት ከባለድርሻ ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከ27 ተቋማት ጋር የአፈፃፀም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሄደ።
13/05/2017 ዓ.ም
**አዳማ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ለመገምገም በዛሬው ዕለት የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣የተቋሙ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ የባለስለጣኑ አመራሮች በተገኙበት የአፈፃፀም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት ከተማችን አዲስ አበባ የበርካታ ዲፕሎማት ማረፊያ ናት፤ ተቋሙ ስሟ እና ተግባሯ ተመሳሳይ እንዲሆን እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የደንብ መተላለፎችን የሚጠየፍ ህብረተሰብ ከመፍጠር አንፃር ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ገልፀዋል።
ተቋሙ በህግ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን ለመስራት ጥረት እያደረገ እና የህግ ማስከበር ስራዎችን በማዘመን ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀው ሸስራው ዘላቂ እንዲሆን ተቋሙ ከተፈራረማቸው ተቋማት ጋር የተመዘገቡ እምርታዊ ውጤቶችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ሙሉነህ ደሳለኝ እንዳሉት የቅንጅት እና የትብብር አሰራር በድጋፍ ክትትል እንዲሁም በምዘና ወቅት ትኩረት እንዲሰጠው ማሳሰቢያዎችን እንሰጥ ነበር ሲሉ ተናግረው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመጀመሪያው ተቋም ነው ብለዋል።
አክለውም በመናበብ የከተማችንን ነዋሪዎች የምናገለግል ልንሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የእንኳን ደና መጣቹ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት በ 2017 ዓ.ም የ6ወራት የስራ አፈፃፀም በጋራ ከሰራናቸው 27 ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመሆን የምንገመግም ይሆናል ብለዋል።
በ6ወራት ውስጥ አብረን በሰራነው ልክ 56.8 የደንብ መተላለፎችን መቀነስ መቻሉን ገልፀው። በቅንጅት በመስራት በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገብን ሲሆን ለዚህም በጊዜው ተገናኝተን ውይይት ማድረግ በመቻላችን ነው ሲሉ ተናግረው። ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በመቀጠልም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በ6ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም በስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅትና አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዳንኤል ቀፀላ ቀርቧል።
በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የውይይት መድረኩን የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ሙሉነህ ደሳለኝ እና የባስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከመድረኩ ለተነሱ ሀሳብ እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
በመጨረሻም ከተቋሙ ጋር በጣም ከፍተኛ እና ከፍተኛ አፈፃፀም ላላቸው ባለድርሻ አካላት የእውቀና ሽልማት በተቋሙ ተበርክቶላቸው መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።