የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
992 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ልምዱን እና ተሞክሮውን ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ልዑካን ቡድን አባላት አጋራ

ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በተቋም አደረጃጀት፣በኮሪደር ልማት አሰራር፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ አጋርቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል-ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ንጉሴ በልምድ ማጋራቱ ወቅት የተቋሙ አደረጃጀት እና ያጋጠሙ ችግሮች ከሚመለከተው አካል በመነጋገር የተፈታበት ሂደት እና ተቋሙ በማጠናከር የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ሂደት በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገልፀዋል።

በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እንደየስራ ክፍላቸው አሰራሮች እና የተቋሙ ተሞክሮዎች የገለጹ ሲሆን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት አስረድተዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ የተደራጀበት እና ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ ጠቃሚ እና ልምዱን በከተማቸው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።