የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ለሰራተኞቹ የኤች አይቪ ኤድስ ሚኒስትሪሚንግ ስልጠና ሰጠ

10/01/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የማዕከል ሰራተኞች በኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት እና አጋላጭ ሁኔታዎች ዙሪያ በኤች አይቪ ሜን እስትሪሚንግ ፎካል ፕርሰኖች አማካኝነት በዛሬው ዕለት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ለስልጠናው የሰጡት የተቋሙ የኤች አይ ቪ ኤድስ ሚኒስትሪሚንግ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አባይነህ ጥጋቡ እንዳሉት የፖለቲካ አመራሩ፣ ማህበረሰቡ እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በኤች አይ ቪ ኤድስ ቅድመ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ የነበራቸውን ሚና አጠናክረው ሊያስቀጥሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ኤች አይ ቪ ኤድስ መከሰቱ ከታወቀበት እ.ኤ.አ 1981 ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ32.7 ሚልዮን በላይ ሰዎችን ህይወት የነጠቀ ገዳይ በሽታ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ አለመጠቀም፣ በቂ እውቀት አለመኖር እና መጤ ባህሎችና ድርጊቶች መስፋፋት ለበሽታው ተጋላጭነት እንዳሰፋው ተገልጿል።

ኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት በአዲስ አበባ ከተማ እንደ ሀገር 2ኛ ደረጃ ሲሆን፣ ይህም በወጣቶች አልባሌ ሥፍራ መዋል፣ሴተኛ አዳሪዎች እና ቱሪስቶች የሚገኙበት አከባዎች በስፋት ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሆኑ የሀይማኖት አባቶች፣ ሽማግሌዎች፣ሲቪል ማህበራት ከመንግስት ጋር በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ቢሰሩ የቫይረሱ ስርጭት ይቀንሰዋል ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል፡፡

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከብር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍3
203 የካሳንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ በዛሬው እለት አውጥተዋል፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የካዛንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓቱ እንደቀጠለ ነው፡፡

በአጠቃላይ በ3 ቀናት ውስጥ የዛሬውን ጨምሮ 428 የልማት ተነሺ የካሳንቺስ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ በማውጣት ቤታቸውን እየተረከቡ ይገኛሉ።

ባለ አንድ እና ባለ ሁለት መኝታ የመንግስት መኖሪያ ቤቶችን በአቃቂ፣ አራብሳ፣ገላን፣ ፈረንሳይ ጉራራ እና ጃርሶ ሳይት የመኖሪያ መንደሮች ለባለእድለኞች በእጣቸው መሰረት ተደራሽ እየተደረገ ነው።

የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ነገን ጨምሮ በቀጣይ ቀናትም እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የልማቱ ተነሺዎች ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካለቸው በክፍለ ከተማው አስተዳደር 10ኛ ፎቅ ወደተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ ወይም በ9065 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉም ተገልጿል።
👍4