ባለስልጣኑ በተሰሩ የልማት የደንብ መተላለፍ በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ የሚወስደው እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ገለፀ
ትናንት ሀምሌ 19/2016 በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች በደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ክትትልና ህዝቡ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በደንብ ጥሰት ተቀጥተዋል።
በዚህም መሰረት ፦
1.ቦሌ ክ/ከተማ
የኮቨርስቶን መንገድ የሠበረ አንድ ተሽከርካሪ 5,000 ብር ተቀጥቷል። እንዲሁም በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ተረፈ ምርት (ቆሻሻ) በዋና መንገድ ላይ ያወረደ ተሽከርካሪ 50,000 ብር ተቀጥቷል።
2. ቂርቆስ ክ/ከተማ
ሞተር ሳይክል በእግረኛ መንገድ ላይ ያቆመ ግለሰብ 3,000 ብር ተቀጥቷል።
አካባቢያቸዉን ያቆሸሹ ሁለት ሱቆች በአጠቃላይ 20,000 ብር ሲቀጡ፣ አከባቢውን ያቆሸሸ አንድ የፅዳት ማህበር 20,000 ብር ተቀጥቷል።
3. ልደታ ክ/ከተማ ደግሞ አንድ ተሽከርካሪ መንገድ የማበላሸት ተግባር በመፈፀሙ 50,000 ብር ተቀጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልማት ስራም ሆነ በመሰረተ ልማት ጥበቃ ዙሪያ ከከተማው ነዋሪ ጋር እጅና ጓንት በመሆን ፅዱ፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች አዲስ አበባን እውን ለማድረግ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

👍14👏3