በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ኢትዮጵያውያን የጀመሩት ስራ ማሳካት እንደምንችል የሚያረጋጥ መሆኑ ተገለፀ
ነሀሴ 17/2016 ዓ.ም
*አዲስ አበባ*
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል በተያዘው መርሀ-ግብርን መሰረት «የምትተከል ሃገር፣ የሚያፀና ትውልድ » በሚል መሪቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ፡፡
የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታው የካ ጣፎ ገብርኤል ቤተ ክርስቱያን አካባቢ በተዘጋጀው የችግኝ ቦታዎች ላይ ከጠዋት 12:00 በመገኘት የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የባለስልጣኑ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች እና ኦፊሰሮች ከጠዋት 12:00 ሰዓት ጀምሮ በየክፍለ ከተማቸው በልዩ ልዩ በተዘጋጁ አካባቢዎች ችግኝ ተክለዋል፡፡
በፕሮግራሙ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በጠቅላይ ሚ/ር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለከተማውና ለአካባቢ ውበት ከፍተኛ ጠቀሜታ ከመኖሩ በላይ ኢትዮጵያውያን የጀመሩት ስራ ማሳካት እንደምንችል ያረጋገጥንበት መሆኑ ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቀደም ብሎ 15000/አስራ አምስት ሺህ/ ችግኝኞች መትከሉ ይታወቃል፡፡
ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

❤1