ባለስልጣኑ ከሁለተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ
26/03/2018 ዓ.ም
** ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የቆየውን የአካልብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና የማጠቃለያ ውይይት የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት አካሂደዋል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋማችን በየጊዜው ራሱን የማዘመንና የማጠናከር ስራ የሚሰራው ከተማችን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ መዲና እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መቀመጫ በመሆኗ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ሰላምና ጸጥቷ የተጠበቀ ለነዋሪዎቿ እና ለእንግዶች ምቹ ጽዱ ማራኪ በማድረግ በስነምግባር የታነጸ ኦፊሰር በመገንባት የተሰጠንን ተልዕኮ በውጤት ለመወጣት መሆኑን ገልጸዋል ።
አቅማችንን በየጊዜው በማሻሻል ከባለድርሻና ከጸጥታ አካላት ጋር በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል እና ሰላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት የከተማውን እና የህብረተሰቡን ደህንነት የማስጠበቅ ከፍተኛ ስራ በደንብ ማስከበር መስራቱንና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
አክለውም ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን በሚገባ በማስተካከል ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ስነምግባር በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የከተማችን ፈጣን እድገት ያማከለ ወቅቱን ያዋጀ ስልጠናዎችን ለአመራሩና ኦፊሰሮች በመስጠት ተቋሙ በከተማው አስተዳደር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት በመፈጸም የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት እንዲቀንሱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይም አመራርና ኦፊሰሩን ለማብቃት በየጊዜው ወቅቱን የጠበቀ ስልጠናዎች እየተዘጋጁ የሚሰጥ መሆኑን የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች

❤14
ባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን የህዝግንኙነት ስራዎቹን ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር ተቋማት ተሞክሮዎች በማጋራቱን ለዘርፉ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆኑ ተገለፀ
ህዳር 26/2018 ዓ.ም
**አዲሰ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ከሰተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለአዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድሀኒት አስተዳደር ባለስልጣን፣ለትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፣ ለአዲስ አበባ የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬቶች የኮሙኒኬሽንና የህዝግንኙነት ስራዎቹን ያለውን ልምድና ተሞክሮ አጋራ ።
በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በዳይሬክቶሬት ከተዋቀረ አጭር አመታት ቢሆንም ከባለስልጣኑ አመራሮች ጋር በመግባባት መስራት በመቻሉ የተሻለ የሚዲያ ግንኙነትና የገፅታ ግንባታ ስራዎች መሰራት መቻሉ ገልፀዋል።
በልምድ ልውውጡ ለሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራዋች በአመራሩና በባለሙያው በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የድምፅና የምስል ስቱዲዮ በማስገንባት የደንብ መተላለፎችን ግንዛቤ በመፍጠር እንዲቀነሱ በሜንስትሪሚንግና በሶሻል ሚዲያዎች እየተሰራ መሆኑን ተገልፀዋል።
ልምድና ተሞክሮ ለመውሰድ የመጡት ዳይሬክቶሬቶች ከተቋቋመበት በአጭር ጊዜ የስራዎቹ ቁርጠኛ በመሆን ስቱዲዮዋች በማስገንባት የተሻለ ስራዎች በመስራቱ ተቋሙን መርጠው መምጣታቸው ገልፀው ለሌሎች ተቋማት የተሞክሮ መቅሰሚያ ማዕከል እንዲሆን ለሰሩ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች አመስግነዋል።
በልምድ ልውውጡ የስቱዲዮ ግንባታው ሂደት፣ የተለያዩ ሚዲያዎችን በማሳተፍ የተሰሩ ስራዎችን፣የሶሻል ሚዲያ ተከታይን አጠቃቀም ፣ የህትመት ውጤቶችን ዝግጅት፣ የህዝብ ግንኙነት ስራዎች፣ የግባቶች አጠቃቀም እና የሬዲዮና ቴለቪዥን ስራዎች በተመለከተ ያለውን ተሞክሮ አጋርቷል።
ለልምድ ልውውጥ የመጡት ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎች ለተደረገላቸ መልካም አቀባበል አመስግነው ልምድ ልውውጡ ተጠናቋል ።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

የባለስልጣኑ የሦስተኛ ዙር የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣኝ አመራሮች እና ኦፊሰሮች አቀባበል ተደረገ
27/03/2018 ዓ.ም
**ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ600 በላይ የሦስተኛ ዙር የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሰልጣኝ አመራሮች እና ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መድረሳቸው ተገለፀ።
ሰልጣኞቹ ወደ ማሰልጠኛው ሲደርሱ የባለስልጠኑ አመራሮ እና የስልጠና አስተባባሪዎች ከዩኒቨርስቲው አመራርና ማህበረሰብ ጋር በመሆን አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የአቅም ግንባታና የስልጠና ማዕከል መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸዉ ጋራ በመሆን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን አስጀምረዋል አስጀምረዋል።
በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ሥልጠናው ለ10 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይና በመግለፅ ሰልጣኞች ስልጠናው በዲሲፕሊን፣በንቃትና በብቃት እንዲከታተሉ መልዕክት ተላልፏል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍2
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ አካሄደ::
ኅዳር 29/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰኞ ማለዳ አመራሮችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት ልምድና ዕውቀት ሽግግር የሚካሄድበት የወረቃማ ሰኞ የአብሮነት መደረክ በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂድዋል።
በመድረኩ "የመደመር መንግስት እይታ; የዘርፎች እምርታ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ በእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮ/ል አድማሱ ተክሌ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ የወረደ የመንግስት ስራ ሰዓት ማክበር የተመለከተ መመሪያ ሰነድ በባለስልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂድዋል።
በውይይቱም እንደነዚህ ያሉ መድረኮች መዘጋጀታቸው ሰራተኞችን ከማንቃትና አጽኖት ከመስጠት ባሻገር መብትና ግዴታቸውን በማሳወቅና በማዋሀድ የአገልሎት አሰጣጡ የተሳለጠ እንዲሆን ያደርጋል ፣ እንደ ተቋም የወረዱ መመሪያዎች ወደ ዘርፍና ዳይሬክተር በማቅረብ እንደ ግለሰብ ወደተግባር የመግባቱ ሁኔታ ላይ ሊሰራበት ይገባል በሚሉና ሌሎች ሀሳቦች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል።
ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ነው።

👍3❤1