የአዳይቱ ካንፓስ የፓራ-ሚሊተሪ አመራሮችና ኦፊሰሮች ስልጠና በመመሪያና በህግ መሰረት አገልግሎት ለመስጠት አቅም የፈጠረ መሆኑ ተገለፀ
ህዳር 29/2018 ዓ.ም
**አፋር አዳይቱ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ አዳይቱ ካምፓስ ለክፍለ ከተማ የፓራ-ሚሊተሪ አመራሮችና ኦፊሰሮች ስልጠና ሰልጣኞች በመመሪያና በህግ መሰረት አገልግሎት ለመስጠት አቅም የፈጠረ መሆኑ የስልጠናው አስተባባሪ ኮሎኔል አያሌው ሽፈራው ገልፀዋል።
ኮሎኔል አያሌ አክለውም ለሰልጣኞቹ የተሰጠው የንድፈ ሀሳብና የአካል ብቃት ስልጠና ሰልጣኞች ወደ ስራ ገበታቸውም ሲመለሱ በስነ ምግባር እና በመመሪያ መሰረት ማህበረሰብን ማገልገል እንዲችሉ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
በስልጠናው ህገ-መንግስት፣የሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የግጭት አፈታት፣ ተግባቦት፣ ስነ- ምግባር ፣ አገልግሎት አሰጣጥና የሳይኮሎጂ ንድፈ ሀሳብ ትምርቶችና የአካል ብቃትን የሚያጎለብቱ ስፖርታዊና የፖሊስ ስልጠናዎችን እንደወሰዱ ተጠቅሷል።
በስልጠናው ሽፍት አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎች፣ ሽፍት መሪዎች እና ኦፊሰሮች እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጿል።
ስልጠናውን እየተከታተሉ ያሉ ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናው ጥሩ እንደሆነና ተጨማሪ አቅምና እውቀት እንዳገኙ ገልፀው የተሰጣቸውን ስልጠና በተግባራዊ በማድረግ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ ማህበረሰብን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ስልጠናው እስከ አርብ እደሚቀጥልና ከ1200 በላይ ሰልጣኞች በስልጠናው እየተሳተፉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍8❤3🙏3