የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች የ2018 በጀት አመት ካስኬዲንግ እቅድ የመፈራረም ስነ-ስርዓት አካሄደ

ነሀሴ 14/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበበ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ካስኬዲንግ ከማዕከል ደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች ጋር የመፈራረም ስነ-ስርዓት አካሄደ ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የድጋፍ ሰጭ ዳይሬክትሬቶቹ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም በመተባበር ሚናውን በመወጣት ባለስልጣኑን የገፅታና ግንባታና ውጤታማነት ከፍ ማድረግ እንደሚገባ መልክት አስተላልፈዋል።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ በባለስልጣኑ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰቶችን ከመቆጣጠር ከመከላከል በተጨማሪ በተቋም ግንባታው የተሞክሮ ማዕከል እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

በ2017 በጀት የስመወገበውን ውጤት በ2018 በጀትም ለማስቀጠል እቅድ ዋና በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን በመወጣት ውጤቱን ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የባለስልጣኑ የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀደም ሲል ካስኬዲንጉን ለክፍለ ከተሞች እና ለዘርፎች ማውረዱን ጠቁመው በዛሬው ቀን ደግሞ ለደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች እቅድ እንደሚያወርዱ ገልፀዋል ።

ከዚህ በፊት የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ በስሩ ከሚገመተው ከስልጠናና ቅድመ መከላከል ዳይሬክቶሬቶች ጋር ካስኬዲንግ እቅድ የተፈራረሙ መሆኑ ተገልጿል።

የካስኬዲንእቅዱ በሂደት ለቡድኖች እና ለባለሙያ ድረስ በማውረድ እያንዳንዱ የወረደለትን ተግባራት በማከናወን በየጊዜው በድጋፍና በግብረ-መልስ መታየት እንዳለበት ተመላክቷል።

በመጨረሻም ደጋፊ ዳይሬክቶሬቶቹ ከባለስልኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ጋር የ2018 በጀት ካስኬዲንግ እቅድ የወረደላቸውን ተፈራርመዋል።

መረጃው ፦የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/

የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid

የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement

የዩቱብ ቻናላችን
https://www.youtube.com/@AACODEENFORCEMENT

https://linktr.ee/aacodeenforcement

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ
👍41