የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ለባለስልጣኑ አመራር እና ኦፊሰሮች በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩኒቨርስቲ ስልጠና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ውይይት ተካሄደ

15/12/ 2017 ዓ.ም
ሰንዳፋ

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ-አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸዉ የተመራው የልዑካን ቡድን በቀጣይ ለባለስልጣኑ አመራሮች እና ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ውይይት ተካሄደ፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸዉ በዉይይቱ ላይ በቀጣይ ለአመራሩ እና ለነባር ኦፊሰሩ የሚሰጠው ስልጠና በስነ_ ምግባር ፣ በህግ ፣ ከኮምንኬሽንና ተግባቦት ዙሪያ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅና የወንዝ ዳር ብክለትን በመከለከልና በመቆጣጠር ሂደት አዲስ አበባን ከተማ ያማከለ ስልጠና እንደሚሆን ገልፀዋል።

በፓሊስ ዩኒቨርሲቲው ለሰልጣኝ አመራሮቹና ነባር ኦፊሰሮቹ የሚሰጠዉ ስልጠና ለስራቸው አጋዥ ብሎም አበረታች እንደሚሆን በማንሳት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎቹ ለአመራሮቹ እና ፈጻሚ አካላት የመፈጸም አቅማቸውን ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚረዳ እንዲሁም በቀጣይ ለሚሰጡ ተልእኮዎች ዝግጁ እንደሚያደርጋቸዉ በውይይቱ ላይ ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ምክትል ፕሬዝዳት ረዳት ኮሚሽነር ደረጄ ተስፋዬ ለአባላቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ፖሊስ ዩኒቨርሲቲው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር አብሮ የመስራት ልምዱን ከበፊቱ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

አክለውም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ስራቸዉን በአግባቡ እንዲያከናውኑ የሚችሉበትን በቂ ዕውቀት የሚያገኙበት ስልጠና ልምድና እውቀቱ ባላቸው አሰልጣኞች እንደሚያዘጋጁ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአመራር ስልጠና አቅም ግንባታ ማዕከል መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው በውይይቱ ወቅት ከራሱ በላይ ህዝብን ጥቅም የሚያስቀድም ከህዝቡ በፊት እሞታለሁ ብሎ ተጨንቆ ለሀገሩና ለህዝቡ የሚሰራ ሰራተኛ ለመፍጠር እንሰራለን ብለዋል ።

በዉይይቱ የባለስልጣኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት የሆኑት ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ በስልጠና አሰጣጥ እና በሚሰጡ የስልጠና ሰነዶች ርዕሶች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
9👍3
ባለስልጣኑ በተሻሻለው የመንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ስልጠና ሰጠ

15/ 11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ለማዕከል ሰራተኞችና ለክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ሰራተኛው አዲስ ተሻሽሎ የወጣውን የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ላይ በቂ ግንዛቤ ኖሮት መብትና ግዴታውን በማወቅ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ስራውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያከናውን ስልጠናው መዘጋጀቱ ገልፀው ሰልጣኞች በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል ።

ስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ክትትል፣ድጋፍና ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን በዝርዝር ከነ ማብራሪያው ሰጥተዋል።

በስልጠናው የአዋጁ መሻሻል በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰጡ አገልገሎቶችን ለማዘመን፣ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደርን ለማሻሻልና ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት መሆኑ አስረድተዋል።

የመንግስት ሰራተኛው በምዘና ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ እውቀትና ብቃት ባለው ሲቪል ሰርቫንት በከተማዋ ውስጥ እየተመዘገበ ያለውን እድገት ለማስቀጠል እንደሚሰራ በስልጠናው ተገልጿል ።

በመጨረሻም በቀረበው የስልጠና ሰነድ ዙሪያ ከሰልጣኞች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
8👍6
"ሙስና ስጋት የማይሆንባት ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እንፍጠር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ ተካሄደ

16/ 11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ከ11 ክ/ከተማ እና ከ119 ወረዳዎች ለተመለመሉ ተባባሪ አካላት/Focal person/ በ2018 እቅድ እና በቀጣይ ትኩረት በማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ የውይይት መድረከ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት በመፈጸም በከተማችን የደንብ ጥሰት እንዲቀንስ በማድረግ ሂደት ውስጥ የስነምግባር ብልሹ አሰራር እንዳይፈጸም ተባባሪ አካላት በአግባቡ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በቀጣይ ውጤታማ ተግበር ለማከናወን ውይይቱ አስፈለጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

የስነ ምግባር ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተዋቀሩ ተባባሪ አካላት /Focal person/ የ2018 ዓ.ም እቅድ እና የመወያያ ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ቀርቧል።

በሰነዱ የ2017 አፈጻጸም ፣ የ2018 በጀት ዓመት ግቦችና ዝርዝር ተግባራት፣ በየደረጃው ያሉ ተባባሪ አካላት ሊያተኩሩባቸው የሚገቡ የስነምግባር ችግሮችን የመፍታት እና ሙስና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ማከናወን የሚገባቸው ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል።

የውይይቱ ዓላማ ከክ/ከተማና ከወረዳ የተወጣጡ ተባባሪ አካላት በየደረጃው ያለው መዋቅር ውስጥ የስነ ምግባርና ብልሹ አሰራር እንዳይከሰት ቀድሞ ለመከላከል መሆኑን አቶ እዮብ ገልፀዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ብልሹ አሰራርን ለመታገልና በስነ ምግባር የታነጸ ኦፊሰር ለመገንባት የበኩላቸውን በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍6