የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.1K subscribers
1.81K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በመልካም አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ለወረዳ አመራሮች ስልጠና ሰጠ።

ነሀሴ 08 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ለወረዳ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የስልጠና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ከ8ሺህ በላይ የባለስልጣኑን የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የሚመሩት በወረዳ አመራሩ በመሆኑ አመራሩ በመልካም አሰተዳደር የተቃኘ መሆን እንዳለበት በማሰብ ስልጠናው መዘጋጀቱ ገልፀዋል።

ምክትል ስራ አስኪያጁ የወረዳ አመራሩ የተቋሙን ራዕይ እና ተልዕኮ ተረድቶ በጥብቅ ስነምግባር የመሪነት ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ በመጠቆም ከስልጠናው የሚገኘውን አቅም ተጠቅሞ በሚመራው አካባቢ መልካም አስተዳደር ሊያሰፍን እነደሚገባ አስገንዝበዋል።

ስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደር ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ ወረታ ተሰጥቷል።

በስልጠናው በመልካም አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብ፣ መልካም አስተዳደር በኢትዮጵያ ፣አለም አቀፋ ትርጓሜዎች፣ በመልካም አስተዳደር መርሆች ፣መልካም አስተዳደር ማስፈን እና በመልካም አስተዳደር መለያ መስፈርቶች ዙርያ ስልጠናው ተሰጥቷል።

ሰልጣኞች በተሰጠው ስልጠና ከስልጠና በፊት እና ከስልጠና በኋላ በለመልካም አስተዳደር ስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ለመለካት ፈተና ተሰጥቷል።

በስልጠናው በቂ ግንዛቤና እውቀት እንዳገኙ እና በቀጣይ በስራቸው መልካም አስተዳደር ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

መረጃው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
8👏4👍3

👍31
በ2017 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ህገ-ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር፣ በመከላከል እንዲሁም እርምጃ በመዉሰድ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ

8/11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት በማድረግ በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው አካላት እውቅና ሰጥቷል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ እንደገለፁት ተቋሙ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት በ2017 በጀት አመት በርካታ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር፣ በመከላከል እንዲሁም እርምጃ በመዉሰድ ከተማችን ብሎም ክፍለ ከተማችን ከደንብ ጥሰት የፀዳች እንደትሆን ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

በ2018 በጀት ዓመትም ህገ-ወጥነትን የመከላከል ስራ ተጥናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ደሳለኝ ጠቁመው ለሚሰሩ ስራዎችም ሁሉም የባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀው በ2017 በጀት አመት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በመያዝ ከነበሩ ክፍተቶች ትምህርት ወስዶ በማረም በ2018 የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የደንብ ጥሰትን ከመከላከል እና ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ተገልጿል።

በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት በተካሄደው ምዘና የተሻለ ዉጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎች እና ባለሙያዎች እውቅና የተሰጠ ሲሆን ወረዳ 11, 1ኛ ፣ ወረዳ 1, 2ኛ ፣ ወረዳ 10 3ኛ ደረጃ በመውጣት እውቅና ተሰጥቷቸዋል ።
👍41
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኦፊሰሮች ከሰላም ሰራዊት አባላትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት የህገወጥ መከላከልና የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ

8/12/ 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት እና ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት "እኔ ለከተማዬ ሰላም ባለቤት እና ጠባቂ እሆናለሁ" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት ህገወጥነት የመከላከልና የፀጥታ ስምሪት የመስጠት ፕሮግራም በአበበ በቂላ ስታዲየም አካሂደዋል ።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ ከ/ ክፍለ ከተማ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ክ/ ከተማችን ከሁሉም የከተማችን አካባቢ እና ከመላው የሀገራችን ክልሎች የተወጣጡ ማህበረሰብና ሸማቾች አንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰፊ ግብይት  የሚፈጽሙበት እንደመሆኑ በተደራጀ የፀጥታ ስምሪትና  ዲሲፒሊን አስተማማኝ ሰላሟ የሰፈነ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ጠንክረን መሥራት ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የክፍለ ከተማችን የፀጥታ አካላት ፣የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና የሰላም ሠራዊት ሰላምና ፀጥታን እንዲሰፍን በቅንጅት በመስራታቸው ህብረተሰቡ በሰላም ወቶ እንዲገባ እንዲሰራና የፈለገውን እንዲገበያይ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል ።
በቀጣይም ለሚከበሩት ሀይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት ባህላዊ እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም ተከብረው እንዲጠነቀቁ ሁሉም አካላት የቅንጅት ስራቸውን በማጠናከር የበኩላችንን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
👍4