የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በ2017 አፈፃፀሙ ያገኘውን የእውቅናና ሽልማት በ2018 በጀት አመት ለማስቀጠል ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ተወያየ

ሀምሌ 16/2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተካሄደ ምዘና ከተቋማት ( ካቢኔ አባል ካልሆኑ ) በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አንደኛ ደረጃ በማግኘቱ የመኪና ሽልማት መሸለሙን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ማኔጅመንት አባላት ደስታውን በመግለጽ ውጤቱ ለማስቀጠል ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ይህ የዕውቅናና ሽልማት መምጣት የቻለው ከላይ እስከታች የሚገኝ አመራርና ሰራተኛ በትጋት፣ በቅንጅት፣በትብብር በተለይም የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በአግባቡ በመወጣቱ በመሆኑ የክፍለ ለከተማ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል ።

አክለውም ውጤቱ ለቀጣይ ስራ አቅም የሚሆን ሲሆን ለውጤቱ መመዝገብ አስተዋጽዎ ላደረጋችሁ የክፍለ ከተማ ና የወረዳ የደንብ ጽ/ቤት ኃላፊዎቹ ሰራተኞችና ኦፊሰሮቻችን በሙሉ ምስጋና በማቅረብ እንኳን ደስ ያላችሁ የድካም ውጤት በመሆኑ ምስጋና ይገባችኋል በማለት ደስታቸውን አጋርተዋል።

የደስታው ተካፋይ የሆኑ የክፍለ ከተማ አመራሮች 2017 በጀት አመት ከፍተኛ ለውጥ የታየበት የከተማ አስተዳደሩን የልማት ስራዎች የተጠበቁበት እና የደንብ ጥሰቶች የቀነሱበት በመሆኑን ውጤቱን ይጠብቁት እንደነበር እና በቀጣይ አመትም ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍41
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የምሽት የንግድ ተቋማት ሰላማዊ ግብይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለፀ

16- 11- 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከከተማው ንግድ ቢሮ ጋር በመሆን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የንግድ ተቋማት የምሽት ስራዎች እንቅስቃሴ ምልከታ አካሂደዋል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ወቅት የደንብ ጥሰት እንዳይኖር የምሽት ምድብ በመመደብ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው እስካሁን የምሽት ስራው የሚያስተጓጉል የደንብ ጥሰትና የፀጥታ ችግር እንዳላጋጠመ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረትና የበርካታ ሃገራት ኢምባሲዎች መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን ይህንን የሚመጥን የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖራት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ይህም በከተማዋን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዘርፍ ይበልጥ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ህብረተሰቡን በባለቤትነት በማሳትፍ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለው የምሽት ግብይት ለንግዱ ማህበረሰብ እና በትራንስፖርት ለተሰማሩት ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ማህበራዊ መስተጋብር ከማሳደግ አንፃር ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

በተለያዩ ጊዜያት በሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በክፍለ ከተማው የሚገኙ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አቶ አድማሱ ገልፀው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችም ያለምንም ስጋት እንዲገበያዩ ጠይቀዋል።
👍51
ባለስልጣኑ የሽንት ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን የበከለ ግለሰብ 3 መቶ ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

ሐምሌ 17/2017
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አካባቢ የሚገኘው ክላሲክ ኮንሰልቲንግ እንጂነርስ ኃላፊነቱ የተረጋገጠ የግል ማህበር የሽንት ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን በመበከል ደንብ በመተላለፉ መቀጣቱ ተገለፀ።

ተቋሙ ከዚህ በፊት እንዲያስተካክል ግንዛቤ ቢሰጠውም ምንም አይነት የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ በደንብ ቁጥር 180 /2017 መሰረት 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር መቀጣቱን የወረዳው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ እስጢፋኖስ ገልፀዋል።

ባለስልጣን መረጃ በመስጠት ብክለት መከላከል እንዲቻል የጠቆሙትን የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም አሳስቧል::

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍12
ወንዝና አካባቢ የበከሉ ሁለት ተቋማት 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ) ብር ተቀጡ

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው ይርጋሀይሌ አካባቢ የሚገኘው ስኬት ህንፃ ኃላፊነቱ የተረጋገጠ የግል ማህበር የዝናብ ውሀ ሽፋን በማድረግ የሽንት ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን በመበከል ደንብ በመተላለፉ 300,000 (ሶትት መቶ ሺ ብር) መቀጣቱን ተገለፀ።

በተመሳሳይ በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ኖህ ሪል ሰቴት ወደ ወንዝ ቆሻሻ በመጣሉ 300,000 (ሶትት መቶ ሺ ብር) ተቀጥቷል።

ተቋማቶቹ ከዚህ በፊት ግንዛቤ የተፈጠረላቸው መሆኑና ቅጣቱ በደንብ ቁጥር 180 /2017 መሰረት እያንዳንዳቸው 300,000 (ሶትት መቶ ሺ ብር) በድምሩ 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ) ብር መቀጣታቸውን የወረዳው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊዎች ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ የክረምቱን የዝናብ ውሀ ሽፋን በማድረግ ቆሻሻ የሚለቁ ግለሰቦችና ተቋማት አካባቢውን ከመበከል በተጨማሪ የከተማው ማህበረሰብ የፍሳሽ ማስወገጃዎች በመድፈን ለጎርፍ አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቧል።

ባለስልጣን መረጃ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታቸው የሚወጡ ነዋሪዎችን እያመሰገነ መላው የከተማው ነዋሪ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ 9995 ነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቀሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍7