የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም የእውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ
19/11/ 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም የእውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ ።
በፕሮግራሙ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከማዕከል እስከ ወረዳ አመራሩና ኦፊሰሩ በመናበብ ቀን ከለሊት 7/24 በመስራቱ በአፈጻጸሙ በከተማ ደረጃ አንደኛ በመውጣት የዘመናዊ መኪና ተሸላሚ ሆነናል ሲሉ ገልጸዋል ።
ተቋማችን ለዚህ ስኬት ያበቃው የከተማችን ፈጣን እድገት ያማከለ እቅድ አቅዶ ከክ/ከተማና ወረዳዎች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ በማድረግ በየጊዜው መገመገም መቻሉ በተጨማሪም ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ደንብ ጥሰትን የሚጸየፍ ለኦፊሰሩም አጋዥ ሆኖ በጋራ በመስራቱ ነው ብለዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቦጋላ ዓለሙ በክፍለ ከተማ የሚታዪ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል በመቆጣጠርና ለህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት ህገወጥነትንና ደንብ ጥሰቶችን እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የክ/ከተማው አፈ ጉባኤ አቶ ወጋየሁ ኃይሉ ደንብ ማስከበር የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ከመወጣት ጎን ለጎን የተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎች ላይ በመሳተፍ የአቅመ ደካማ ቤት በማደስ፣ ማዕድ በማጋራት አረንጓዴ አሻራ ላይ በመሳተፍ በአይን የሚታይ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ በህብረተሰቡም ተቀባይነቱ እየሰፋ እየሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
አክለውም ተቋሙ በከተማ አስተዳደር በተደረገው ምዘና በአፈጻጸሙ አንደኛ መውጣቱ የጥንካሬው ውጤት መሆኑን ገልፀዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የክ/ከተማው የብልጽግና ፖርቲ ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ደንብ ማስከበር ህገወጥነትን የሚከላከል ሰላምና ጸጥታን የሚያስከብር በከተማዋ እድገት የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በመወጣት የተሰሩ ፕሮጀክቶችና ኮሪደር ልማቶችን ውብ ጽዱ ሆነው እንዲቆዩና ለተገልጋዮች ምቹ በማድረግ በርካታ ተግባር አከናውኗል ሲሉ ገልጸዋል ።
በመጨረሻም ለወረዳው አመራሮች ፣ ከ1 - 3 ለወጡ ኦፊሰሮች፣ ለባለድርሻ አካላት፣ ለጸጥታ አካላት እንዲሁም ከጽ/ቤቱ ጎን ለስራው መሳካት ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምስጋናና የእውቅና ሽልማት ተሰጥቷል ።
በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ወረዳዎች የእውቅናና ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን
1ኛ ወረዳ 13
2ኛ ወረዳ 05
3ኛ ወረዳ 10 እና 2 የዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸለሚ ሆነዋል።
እንዲሁም በህጉና መመሪያው መሠረት አድርጎ እርምጃ የወሰዱና ቅጣቱን ገቢ ማድረግ ወረዳ 13 እና 11 የሞተር ሳይክል ተሸላሚ ሆነዋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

❤8