ባለስልጣኑ እስከ ምሽቱ አራት ስዓት ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር ሰላማዊ ግብይት እንዲኖር እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና ከንግድ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የንግድ ተቋማት የምሽት ንግድ ስራዎችና ግብይት ላይ የወጣውን ደንብ ተግባራዊ መደረጉን የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የስራ ባህልን እንደ ሀገር ለማሳደግ የንግድ ሱቆች ስራዎች በምሽት እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን አንዳንድ የደንብ ጥሰቶችና ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ለመከላከል ደንብ ማስከበር ሽፍቱን አጥፎ እስከ ምሽቱ አራት ስዓት በመስራት የህገወጥ ንግድ ቁጥጥርና የገበያ ማረጋጋት ስራዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።
በከተማችን የሚገኙ የንግድ ሱቆች እስከ ምሽት 4:00 ሰዓት እየሰሩ እንደሚገኙ በተደረገው ምልከታ ሰላማዊ የሆነና ምንም አይነት የጸጥታ ችግር ሳይኖር የንግድ እንቅሰቃሴው በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ በምልከታው ተረጋግጧል።
በምልከታው በአንዳንድ አካባቢዎችዎ ይታያሉ ተብለው ከነጋዴዎች የተሰጡ የትራንስፖርት ችግር አስተያየቶችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ እንዲሰጥና እንደሚስተካከል የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ተናግረዋል ።
አክለውም ምሽት ላይ የጸጥታ ችግር ይኖራል የሚል ስጋት እንዳይኖር በ7/24 የስራ ባህል የጸጥታ መዋቅሩ ከተማዋን እየጠበቀ የሚገኝ ሲሆን የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ የከተማዋን ፈጣን ዕድገት ተከትሎ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴን ይበልጥ አንደሚያሳድግ ገልጸዋል ።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደተናገሩት ከተማችን ሶስተኛ የዲፕሎማሲ መቀመጫና ትልቅ ከተማ እንደመሆኗ የምሽት ንግድ መኖሩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ መነቃቃት የሚፈጥርና የስራ ባህልን የሚያሳድግ ነው።
በምልከታውም የባለስልጣኑ፣የሰላምና ጸጥታና የንግድ ቢሮ የከተማውና የክፍለ ከተማው አመራሮች ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ኦፊሰሮችና የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል ፡፡
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍7
የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በወረዳ 05 የአቅመ ደካማ እናት የቤት እድሳት አስጀመረ
16/11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራና ምክትል ስራ አስኪያጆች በተገኙበት በወረዳ 05 ነዋሪ የሆኑ አቅመ ደካማ ወ/ሮ አስታጥቃ ቢሻው ቤት በ90 ቀን እቅድ ውስጥ አድሶ ለማስረከብ አስጀምረዋል።
ተቋሙ በ90 ቀናት እቅድ ውስጥ የችግኝ ተከላ፣ የማዕድ ማጋራት፣ የደም ልገሳና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የማድረግ ስራዎችን አጠናክሮ እየሠራ እንደሚገኝ ሻለቃ ዘሪሁን አስታውሰው፤ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአቅ ደካማ እናት ቤትን በአጭር ቀናት ውስጥ አድሶ ለማስረከብ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመትእቅድ አፈፃፀም በላቀ ውጤት በማጠናቀቅ ከከተማው አስተዳደር ሴክተር ተቋማት ጋር ተወዳድሮ 1ኛ በመውጣት የመኪና ሽልማት በማግኘቱ ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የህብረተሰብ ክፍሎችና አጠቃላይ የተቋሙ አመራሮች፣ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮችና ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍7❤4👎1👏1
ባለስልጣኑ በ2017 አፈፃፀሙ ያገኘውን የእውቅናና ሽልማት በ2018 በጀት አመት ለማስቀጠል ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ተወያየ
ሀምሌ 16/2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተካሄደ ምዘና ከተቋማት ( ካቢኔ አባል ካልሆኑ ) በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አንደኛ ደረጃ በማግኘቱ የመኪና ሽልማት መሸለሙን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ማኔጅመንት አባላት ደስታውን በመግለጽ ውጤቱ ለማስቀጠል ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ይህ የዕውቅናና ሽልማት መምጣት የቻለው ከላይ እስከታች የሚገኝ አመራርና ሰራተኛ በትጋት፣ በቅንጅት፣በትብብር በተለይም የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በአግባቡ በመወጣቱ በመሆኑ የክፍለ ለከተማ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል ።
አክለውም ውጤቱ ለቀጣይ ስራ አቅም የሚሆን ሲሆን ለውጤቱ መመዝገብ አስተዋጽዎ ላደረጋችሁ የክፍለ ከተማ ና የወረዳ የደንብ ጽ/ቤት ኃላፊዎቹ ሰራተኞችና ኦፊሰሮቻችን በሙሉ ምስጋና በማቅረብ እንኳን ደስ ያላችሁ የድካም ውጤት በመሆኑ ምስጋና ይገባችኋል በማለት ደስታቸውን አጋርተዋል።
የደስታው ተካፋይ የሆኑ የክፍለ ከተማ አመራሮች 2017 በጀት አመት ከፍተኛ ለውጥ የታየበት የከተማ አስተዳደሩን የልማት ስራዎች የተጠበቁበት እና የደንብ ጥሰቶች የቀነሱበት በመሆኑን ውጤቱን ይጠብቁት እንደነበር እና በቀጣይ አመትም ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

👍4❤1