እንኳን ደስ አላችሁ!!! እንኳን ደስ አለን!!!
ድርብ ደስታ!!! ድንቅ ስኬት!!!
ሁለቱም ተቋሞቻችን በ2017 በጀት ዓመት በላቀ አፈፃፀም ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከተቋማት 1ኛ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከከተማው ከቢሮዎች 2ኛ በመውጣት የመኪና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

👍24🏆8❤1😁1
"እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! ስኬቱ የሁሉም አመራርና፣ ሰራተኞችና ኦፊሰሮች የጥረት ውጤት ነው" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ
ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት በተካሄደው ምዘና ከተቋማት ( ካቢኔ አባል ካልሆኑ ) በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አንደኛ ደረጃ በመውጣት የመኪና ሽልማት ተበርክቶለታል ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት ይህ ዕውቅናና ሽልማት መምጣት የቻለው ከላይ እስከታች የሚገኝ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ በትጋት፣ በጥረት፣ በመደማመጥ፣ በቅንጅትና በትብብር ተግባብቶ በጋራ መስራት በመቻሉ ስለሆነ መላው የደንብ ማስከበር አመራሮች ፣ሰራተኞችና የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ልፋታችን ውጤታማ ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ።
በእለቱ የባለስልጣኑ አመራሮች በዘንድሮ አመት ለውጤት ያበቃንን ተግባብቶና ተናቦ የመስራት ባህል በቀጣዩ በጀት ዓመት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አስገንዝበዋል ።
አክለውም በ2018 በጀት አመትም ወርቃማ ድል ለማስመዝገብና የከተማችን የደንብ ጥሰት ለመቀነስ ከወዲሁ ዝግጁ መሆን ይገባናል ብለዋል።
በተጨማሪም የባለስልጣኑ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች በተገኘው ውጤት ደስተኞች መሆናቸውንና በቀጣይም የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍12❤1
ባለስልጣኑ ከሰላምና ፀጥታና ከንግድቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ አደረገ
ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም
*የአዲስ አበባ ****
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሰላምና ፀጥታና ከንግድቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የንግድ ተቋማት የምሽት ግብይት የወጣውን ደንብ ተግባራዊ መደረጉን የመስክ ምልከታ አካሄደ።
በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ በወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣በንግድ ቢሮ ሀላፊ በወ /ሮ ሀቢባ ሲራጅ እና የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና ሌሎች የክፍለ ከተማውና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በምልከታውም የከተማውና የክፍለ ከተማው የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር የገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል አባላትም ተገኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማ የንግድ ተቋማት በተቀመጠላቸው የሥራ ሰዓት ገደብ ክፍት ሆነው በአገልግሎት ላይ መሆናቸውንናየወጣውን ደንብ ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በጉብኝቱም የተቋማት የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ የከተማዋን ፈጣን ዕድገት ተከትሎ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴን ይበልጥ እንደሚያሳድግ ተብራርቷል።
የምሽት ንግድ አገልግሎት መስፋፋት የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ በማነቃቃት የዜጎችን ገቢ ከፍ ከማድረግ ባለፈ ለተጨማሪ የሥራ ዕድሎች መፈጠርና የስራ ባህልን እንደሚያሳድግም ተመላክቷል።
በምልከታው የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒእመተላህ ከበደ የተገኙ ሲሆን በክፍለ ከተማው የተቋማት የምሽት የስራ ሰዓት ገደብ አተገባበርን አስመልክቶ ለግብረ ሀይል አባላት ገለፃ አድርገዋል።

👍4❤1