የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣናኑ ከጎንደር ከተማ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የስራ ልምዱና ተሞክሮውን አጋራ

07/11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከጎንደር ከተማ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት ስለ ተቋሙ አጠቃላይ አደረጃጀትና የስራ እንቅስቃሴዎችን የተመለከተ ልምድና ተሞክሮ አጋራ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በተሞክሮ ማጋራቱ ወቅት እንተገለጹት ተቋሙ የከተማችን ፈጣን እድገት በመገንዘብ በተከናወነው የልማት ስራዎች የራሱን ድርሻ ለመወጣት 24/7 የስራ ባህል አድርጎ ቀን ከለሊት ሳይል በርካታ ስራዎች ማከናወኑንና በዚህም የሚታዩ ውጤት መገኘቱንና ልዕኳን ቡድኑ የተሻሉ አሰራሮችን ወደ ራስ በማምጣት ከዚህ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ አደረጃጀት መፍጠር እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

የተቋም ግንባታ ስራዎችን በማጠናከርና ስትራቴጂካዊ የሆነ የአመራር ስልትን በመንደፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ስራዎችን በቅንጅት መምራት በመቻሉ በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰትን ለመቀነስ ማስቻሉንና ከተማችንን ጽዱ ውብ ለነዋሪዎች ምቹ እንድትሆን የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

የጎንደር ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ኮለኔል አስማረ ደምለው ልምምድ ልውውጥ ማድረጉ የተሻሉ አሰራሮችን ተሞክሮዎችን ወስደን ወደ ከተማችን በማምጣት እና በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ በመሆኑ በትጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

ለልምድ ልውውጥ ለመጡ አካላት የተዘጋጀው መነሻ ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል።

በተቋም አደረጃጀት፣በአሰራር፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ በሰነዱ አጋርቷል፡፡

ለልምድ ልውውጥ የመጡት ቡድኖች ያገኙትን ልምድና ግብዓት መነሻነት በማድረግ ተቋማቸውን በማጠናከር ውጤታማ ስራዎችን መስራት የሚያስችለን ነው ያሉ ሲሆን ስለ ተደረገላቸው መልካም አቀባበል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከልብ አመስግነዋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍51
ከ1100 በላይ የሚሆኑ የባለስልጣኑ የአመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ

ሐምሌ 11- 2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር በመተባበር "ደም መስጠት ህይወት መስጠት ነው " በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሐ ግብር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አከናወነ።

የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በክረምት በጎ ፍቃድ ከዘጠና ቀናት እቅድ አንዱ የሆነውን የደም የመለገስ መርሃ-ግብር አመራሩና ኦፍሰሩ በጋራ በመሆን በራስ ተነሳሽነት ደም ለመስጠት መገኘቱ የህሊና እርካታ የሚሰጥና ደም በመስጠት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ለመታደግ መሆኑ ተናግረዋል።

አክለውም ደም ልገሳ የሁሉንም ህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ የሚጠይቅ ታላቅ ሰብዓዊ አገልግሎት ሱሆን በተለያየ ምክንያትና አደጋ በደም እጦት የሚሞቱ ወገኖቻችንን ደም በመስጠት ህይወት የማዳን ስራ ለመስራት የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ ከስጦታዎች ሁሉ ዉዱ ስጦታ የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት የሚያድነውን ደም ለመለገስ ፍቃደኛ ሆነው የተገኙ ከ1100 በላይ የሚሆኑ የደንብ ማስከበር አመራሮችና ኦፊሰሮች ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል ሱሉ ተናግረዋል ።

በቀጣይም በቋሚነት አባል ሆነን በየሶስት ወሩ ደም በመለገስ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በደም ልገሳ መርሐ ግብር የባለስልጣኑ የክፍለ ከተማና የወረዳ ጽ/ቤት አመራሮች፣ የማዕከል ሰራተኞች፣ከ11 ክፍለ ከተማ እና ከ119 ወረዳዎች በጎ-ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ኦፊሰሮች ተሳትፈዋል ።

በመርሀ ግብሩ ባለስልጣኑ በከተማዋ የደንብ መተላለፎች ከመከላከልና ከመቆጣጠር በተጨማሪ በርካታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በመሳተፍ የሀገር አለኝታ መሆኑ ተገልጿል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍4
504 ዩኒት ደም 3ሰዓት ባልሞላ ጊዜ መለገሱን ተገለፀ

ባስልጣኑ ''ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት እንታደግ'' በሚል መሪ ቃል ባደረገው የደም ልገሳ መርሀ-ግብር ከ1100 በላይ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ አመራሮቹና ሰራተኞቹ በማሳተፍ ከ504 ዩኒት ደም መለገሱን ብሄራዊ ደም ባንክ ገለፀ።

የደም ልገሳው እጅግ ውጤታማና የተቀናጀ በመሆኑ ስራው መሳካቱ የተገለፀ ሲሆን ለዚህም የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች ላደረጉት መልካም ተግባር በብሄራዊ ደም ባንክ ተመስግነዋል።

"ደም መስጠት ህይወት መስጠት ነው"

መረጃው፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍148