የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የሶስተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናውኗል ።

07- 11- 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የሶስተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናወነ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የቂርቆስ፣ የአራዳ እና የልደታ ክ/ከተሞች ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አመራሮችና ኦፊሰሮች ተገኝተዋል።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ደንብ ጥሰትን ከመከላከል ከመቆጣጠርና እርምጃ ከመውሰድ ጎን ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ የሰው ተኮር ተግባራት ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል ።

ዘንድሮ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር "በመትከል ማንሰራራት " በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ባለስልጣኑ ለተከታታይ 3 ቀናት በዛሬው ዕለትም በደማቅ ሁኔታ ያካሄደ ሲሆን በቀጣይም የደም ልገሳ መርሐ ግብርና የተጀመረውን የቤት ዕድሳት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ዋና ሰራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

በችግኝ ተከላ መርኃ ግብሩ የተገኙት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር እንደሀገር ያለንን አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ ተጠናክሮ በዛሬው ዕለትም በባለስልጣኑ ቀጥሏል በማለት ሁሉም አካል በአግባቡ በተዘጋጀው ቦታ በመትከልና አሻራውን በማሳረፍ ኃላፊነቱን መወጣትና በቀጣይም መንከባከብ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍2
ባለስልጣናኑ ከጎንደር ከተማ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የስራ ልምዱና ተሞክሮውን አጋራ

07/11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከጎንደር ከተማ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት ስለ ተቋሙ አጠቃላይ አደረጃጀትና የስራ እንቅስቃሴዎችን የተመለከተ ልምድና ተሞክሮ አጋራ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በተሞክሮ ማጋራቱ ወቅት እንተገለጹት ተቋሙ የከተማችን ፈጣን እድገት በመገንዘብ በተከናወነው የልማት ስራዎች የራሱን ድርሻ ለመወጣት 24/7 የስራ ባህል አድርጎ ቀን ከለሊት ሳይል በርካታ ስራዎች ማከናወኑንና በዚህም የሚታዩ ውጤት መገኘቱንና ልዕኳን ቡድኑ የተሻሉ አሰራሮችን ወደ ራስ በማምጣት ከዚህ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ አደረጃጀት መፍጠር እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

የተቋም ግንባታ ስራዎችን በማጠናከርና ስትራቴጂካዊ የሆነ የአመራር ስልትን በመንደፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ስራዎችን በቅንጅት መምራት በመቻሉ በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰትን ለመቀነስ ማስቻሉንና ከተማችንን ጽዱ ውብ ለነዋሪዎች ምቹ እንድትሆን የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

የጎንደር ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ኮለኔል አስማረ ደምለው ልምምድ ልውውጥ ማድረጉ የተሻሉ አሰራሮችን ተሞክሮዎችን ወስደን ወደ ከተማችን በማምጣት እና በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ በመሆኑ በትጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

ለልምድ ልውውጥ ለመጡ አካላት የተዘጋጀው መነሻ ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል።

በተቋም አደረጃጀት፣በአሰራር፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ በሰነዱ አጋርቷል፡፡

ለልምድ ልውውጥ የመጡት ቡድኖች ያገኙትን ልምድና ግብዓት መነሻነት በማድረግ ተቋማቸውን በማጠናከር ውጤታማ ስራዎችን መስራት የሚያስችለን ነው ያሉ ሲሆን ስለ ተደረገላቸው መልካም አቀባበል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከልብ አመስግነዋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍51