የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የከተማ አስተዳደሩ የ2018 በጀት ዓመት በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ለምክር ቤት ቀርቦ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በሁለተኛው ቀን ወሎ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ለ2018 በጀት ዓመት 350 ቢሊዮን ብር በእቅድ መያዙን አቅርበዋል::

ከተመደበው በጀት ውስጥ ለካፒታል በጀት 249.9 ቢሊዮን ብር እና ለመደበኛ ወጪ 100.1 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

ባቀረቡት የበጅት ድልድል የ2018 በጀቱ በዋናነት ለደህነት ቅነሳ፣ ለዘላቂ ልማት፣ የስራ እድል ፈጠራ ለትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ከከተማው ነዋሪ በተለያዩ መንገድ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለሚሰጡ አገልግሎቶች ፣ ለአቅርቦት ድጎማዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁጠባን መሰረት ያደረገ ስራ ላይ የሚውል ነው ብለዋል፡፡
2
ባለስልጣኑ "በመትከል ማንሰራራት! " በሚል መሪ ቃል በችግኝ ተከላ መረሃ-ግብር አስጀመረ

ሀምሌ 5/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባስልጣን ከፍተኛ አመራሮች፣የለሚ ኩራ ፣የጉለሌ እና የቦሌ ክፍለ ከተማና የየካ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በጋር በመሆን የ2017/18 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ‘’በመትከል ማንሰራራት’’ በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፈረንሳይ ለጋሲዎን አካባቢ በተዘጋጀው ቦታ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰቶችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባሻገር የአቅመ ደካማ ቤት በማደስ ፣ ደጋፊ የሌላቸውን ህፃናት በመደገፍ ፣ ደም በመለገስ እና የችግኝ ተከላ በማካሄድ በበጎ ተግባራት በግንባር ቀደም መሳተፋቸው ገልጸዋል።

ሻለቃ ዘሪሁን አያይዘውም የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ ለተከታታይ 3 ቀናት እንደሚቀጥል በመግለፅ በከተማው የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ለማጠናከር እና ከተማዋን ውብ፣ ፅዱ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በማካሄድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተናግረዋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ከበደ ባለስልጣኑ ሀገራዊ ተልዕኮን በመቀበል ዘንድሮ የሚተከለውን ችግኝ ለመትከል ወደ ክፍለ ከተማችን በማጣቱ በማመስገን በቀጣይ የፅድቀት መጠኑን እንክባካቤ እንደሚያደርግ ከፍተኛ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ባለስልጣኑ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በአግባቡ እንክብካቤ በማድረግ ከዚህ በፊት ከነበረው በላቀ መንገድ እንዲፀድቅ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ የገለፁት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ናቸው ።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ከ3000/ከሶስት ሺህ/በላይ ችግኞችን የተተከለ ሲሆን የጥላ፣ የውበት እና የፍራፍሬ ዛፎች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

የችግኝ ተካላ መርሃ ግብሩን ያከናወኑት አመራርና ሰራተኞች ችግኙን በመትከል እንደተሳተፉ ሁሉ በቀጣይም በመንከባከብ ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን በመፍጠር ለትውልድ ለማስረከብ አሻራችዎን እንደሚያቆዩ ተናግረዋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
5
ባለስልጣኑ የሶስተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናውኗል ።

07- 11- 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የሶስተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናወነ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የቂርቆስ፣ የአራዳ እና የልደታ ክ/ከተሞች ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አመራሮችና ኦፊሰሮች ተገኝተዋል።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ደንብ ጥሰትን ከመከላከል ከመቆጣጠርና እርምጃ ከመውሰድ ጎን ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ የሰው ተኮር ተግባራት ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል ።

ዘንድሮ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር "በመትከል ማንሰራራት " በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ባለስልጣኑ ለተከታታይ 3 ቀናት በዛሬው ዕለትም በደማቅ ሁኔታ ያካሄደ ሲሆን በቀጣይም የደም ልገሳ መርሐ ግብርና የተጀመረውን የቤት ዕድሳት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ዋና ሰራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

በችግኝ ተከላ መርኃ ግብሩ የተገኙት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር እንደሀገር ያለንን አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ ተጠናክሮ በዛሬው ዕለትም በባለስልጣኑ ቀጥሏል በማለት ሁሉም አካል በአግባቡ በተዘጋጀው ቦታ በመትከልና አሻራውን በማሳረፍ ኃላፊነቱን መወጣትና በቀጣይም መንከባከብ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍2