የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣናኑ የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነውን በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት አስጀመረ

4/11/2017 ዓ.ም
አ አ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነውን የቤት እድሳት በ ወረዳ 05 እና የኮልፌ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት በወረዳ 06 እንዲሁም የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል ።

የቤት እድሳት መርኃ ግብሩን የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የወረዳ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት አስጀምረዋል።

የቤት እድሳቱን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ም/ ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የደንብ ጥሰትን ከመላከል ጎን ለጎን የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነውን በሰው ተኮር ተግባር የአቅመ ደካማ የቤት እድሳት ስራው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ፡፡

በተመሳሳይ የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ መርሐግብር በወረዳ 10 አካሂዷል ።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ ደንብ ማስከበር ህገወጥነት መከላከል እና ከፀጥታው ጋር የተያያዘ ስራ የሚሰራ ቢሆንም ማህበራዊ ሀላፊነትን ለመወጣት የልማትና ሰው ተኮር ሰራዎች ላይ በመሳተፍ በዛሬው ዕለት የአረንጓዴ አሻራ በማሳረፍ እንዲሁም የቤት እድሳት በማስጀመር ሀላፊነታቸው እየተወጡ እንየደሚገኙ ገልፀዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የ11ዱም ወረዳዎች የደንብ ማስከበር ሀላፊዎችና ኦፊሰሮች እንዲሁም የክ/ከተማው የወረዳ 10 አመራሮች ተገኝተዋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
👍3
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የደም ልገሳ እና የፎቶ አውደ ርዕይ ፕሮግራም አካሄደ

04- 11- 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በበጀት አመቱ ለ3ተኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮገራም እና ዓመታዊ ስራዎች በከፊል የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ ፕሮግራም አካሂደዋል ።

በፕሮግራሙ መክፈቻ ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፖርቲ ኃላፊ ሙሉጌታ ጉልማ ፣የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ ፣ የክ/ከተማው የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ያሲን መሐመድ ፣ የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ኦፊሰሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው የሚታዩ የደንብ ጥሰቶችንና ህገወጥ ተግባራት በመከላከል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸዉን ስራዎችንም ለህብረተሰቡ ለማሳየት የፎቶ አውደ ርዕይ አዘጋጅቶ ለተመልካች ክፍት ማድረጉ ሊበረታታ የሚገባ ተግባር መሆኑን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፖርቲ ኃላፊ ሙሉጌታ ጉልማ ተናግረዋል ።

በፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የኮልፌ ቀራንዬ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ የፎቶ አውደ ርዕዩ በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ መደበኛ ስራዎችና ዋና ዋና ተግባራት ፣ የበጎ ፍቃድና ሰው ተኮር ተግባራት፣ የቅንጅት ስራዎች እንዲሁም በርካታ ተግባራትን የተካተቱበት ሲሆን ማህበረሰቡ እየተመለከተ ሀሳብና አስተያየት እንዲሰጥበት ዝግጅት መደረጉ ገልጸዋል ።

በእለቱ "ደሜን ለወገኔ " በሚል መሪ ቃል በክ/ከተማው የሚገኙ ሰራተኞችን እና ኦፊሰሮችን በማስተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም በበጀት አመቱ ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍2