ለህገ-ወጥ እርድ የተዘጋጁ 62 የቁም እንስሳት ተያዙ
01_10 2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የደንብ ማስከበር አባላት ከወረዳው የፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በተደረገው ክትትል መሰረት እጅ ከፍንጭ በመያዝ የድርጊቱ ፈፃሚዎች በህግ ተጠያቂ በማድረግ በቦታው የተገኙት የቁም እንስሳቶች ለመንግስት ገቢ መደረጋቸው ተገለፀ።
የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የቁጥጥርና ኢንስፔክሽን አስተባባሪ አቶ ሙሉሰው ድልነሳ እንደገለፁት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ጥናት ተካሂዶ በተደረገው ኦፕሬሽን የተገኙ የታረዱ በጎች ብዛት 12 ፤ የታረደ በሬ ብዛት 1 ፤ ያልታረዱ የቁም እንስሳት ብዛት 62 መያዛቸው ገልፀዋል።
በቦታው የተገኙ 62 የቁም እንስሳት ለጠፍ በረትና ገቢ የተደረገ ሲሆን የተያዘው ስጋ እንዲወገድ ለቄራዎች ድርጅት ማስረከቡ ለህገ-ወጥ እርድ ሲያከናውን የተያዘው ግለሰብ 15 ሺህ ብር በመቅጣት በህግ እንዲጠየቅ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ተገልጿል።
ባለስልጣኑ ህገወጥ ተግባራት በሚሰሩ አካላት ላይ የሚወስደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለፅ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ከቅጣት በዘለለ ለህግ እንዲቀርቡ እንደሚደረግ አስታውቋል።
ተቋሙ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማና መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

❤10👍6👏4
ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት በቅንጅት ለሰሩ ተቋማት እውቅና ሰጠ
ሐምሌ 03/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች የእቅድ አፈጻጸም በመገምገም እውቅና በመስጠት በ2018 በጀት ዓመት በቅንጅት ለሚሰሩ ስራዎች የስምምነት ፊርማ ፕሮግራም አካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በ2017 በጀት ዓመት እቅዶችን በማቀድ በከተማዋ ከሚገኙ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የስምምነት ፊርማ በመፈራረም በቅንጅት አብሮ በመሰራት እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያቶች ሰራዎች በመገምገም የተሻለ ስራዎችን ማከናወን መቻሉ ገልፀዋል ።
ተቋሙ ባሳለፈው በጀት ዓመት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የተቋም ግንባታ ሰራውን ማጠናከር ፣ የተቋሙን ተግባራት ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ከተማችንን ውብና ጽዱ እንድትሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ከፍተኛ ሰራ መሰራቱ ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮና ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት በከተማችን የሚስተዋሉ ደንብ ጥሰቶች በ69.8% እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን ዋና ሰራ አስኪያጁ ገልፀዋል ።
የአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ በከተማችን እየታየ ያለው ፈጣን እድገት፣ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችና የተሰሩ የኮሪደር ልማቶች የቅንጅት ስራዎችን በማጠናከር 7/24 በመስራት የተገኙ ውጤቶች መሆናቸው ተናግረዋል ።
አክለውም የደንብ ማስከበር በፊት የነበረው ገጽታ ለማስተካከልና በከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት ለማድረጉ በየጊዜው የሚያከናውነው የቅንጅት ስራዎች ጉልህ ሚና እንዳለቸው በመግለፅ በቀጣይ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የደንብ ማስከበር በ2017 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና በ2018 በጀት ዓመት በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎች የእቅድ ሰነድ በባለስልጣኑ የስታንዳርድዜሽንና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል።
በሰነዱ በበጀት ዓመት ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተፈፀሙ ዋና ዋና ተግባራትና የነበሩ ውስንነቶች እና የተወሰዱ መፍትሄዎችን በዝርዝር ቀርበዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ የተቋሙ ባለድርሻ አካላት የቅንጅት ስራዎችን በጋራ ማቀድ እና መገምገም ይበል የሚያሰኝና በቀጣይም ይህን የቅንጅት ተግባር በማጎልበትና በማጠናከር በበጀት ዓመቱ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት በጋራ በርብርብ እንደሚሰሩ አስተያየት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት በጋራ አብረው ለሰሩ ባለድርሻ አካላት በየደረጃቸው የእውቅና ሽልማት በማበርከትና በመድረኩ ከተገኙ የባለድርሻ አካላት ጋር በ2018 በጀት ዓመት በጋራ ለመስራት የትስስር ሰነድ ተፈራርሟል ።

👍4❤1